Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ለተሻለ ኑሮና ፣ለነጻነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚደረገው ትግል አይቀለበስም

$
0
0

Posted By issa Abdusemed
ለሃያ ሁለት ዓመታት የተንሰራፋውን በአምባ ገነኑ ቡድን በወያኔ የሚመራውን የኢሕዴግ መንግስት ለማሶገድ የሚያስችለውን ዕድል የተቃዋሚ ድርጅቶች በእርስ በርስ የስልጣን ንትርክና ሽኩቻ ሊያጡት አይገባም።…መከፋፈል በቃን ብለው ተባብረው በመነሳት ሕዝቡን በጋራ ለመምራት አላፊነቱን መውስድ አለባቸው። በአሁኑ ጊዜ ከዳር እሰከዳር በመስፋፋት ላይ ያለውንና የተነሳው የኢትዮጵያኑ የለውጥ ሱናሚ በወያኔና በደጋፊዎቹ ሊቆምና ሊገደብ አይችልም።በባዶ የኤኮኖሚ እድገት ሰበካና ጫጫታ፣በከፋፍለህ ግዛ ስልትና በመንግስታዊ ሽብር
የሰማንያ ሚሊዮን ሕዝብ አንድነት አይፈታም።ለተሻለ ኑሮና ፣ለነጻነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚደረገው ትግል አይቀለበስም ።ወደ ለውጥ የሚወስደው በር ተዘግቶ አይቀርም፤በሕዝብ የተባበረ ሃይል ተበርግዶ ይከፈታል። የምንልበት ጊዜው አሁን ነው።ኢትዮጵያውያን በአንድነት ተነስተን የወደፊት እጣ ፈንታችንንና ህልውናችንን የምናረጋግጥበት ፤ከገጠር እስከ ከተማ፣በውስጥም በውጭም የምንኖረው የአንድ አገር ልጆች ተባብረን ለአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ተንሰራፍቶ የቆየውን በሙስናና በዘረፋ የተጨማለቀውን፣እጁ በንጹሃን ዜጎች ደም የጨቀየውን፣ በባዕዳን ዘራፊ ሃይሎች የሚደገፈውን፣በወያኔ ቡድን የሚመራውን የግፍ አስተዳደር ለማሶገድ ጊዜው አሁን በመሆኑ በቃ ብለን እንነሳ።የአርባ ዓመት በፊት የየካቲትን ሕዝበ ንቅናቄ በተሻለ ዝግጅትና ቅንጅት ዳግመኛ እንዘክረው። የግንቦት ወርም እንዲሁ አያሌ ታሪካዊ ገጾችን ያመላከተና የብዙ የትግል ድሎች የተወለዱበት ወርና የታሪክ ምዕራፎች የሰፈሩበት የጊዜ መዝገብ ነው።የጣሊያን ፋሽሽት ወራሪ ሃይል በኢትዮጵያውያን በአደዋ ጦር ሜዳ የተሽነፈውና ለተቀረው የቅኝ ግዛት አገሮችሕዝብ የነጻነት ቀንዲላ የተለኮሰው በግንቦት ወር ነው።የደርግ ጨካኝና አምባ ገነን መንግስት ተወግዶ በተመሳሳይ አምባ ገነንና ጨካኝ መንግስት የተተካው በዚሁ በግንቦት ወር ውስጥ ነው።ብዙሃኑ በምርጫ ያሸነፈበት የግንቦት ወር ነው። ድምጹ የተዘረፈውና የታፈነው ፣አምባ ገነኑ መለስ ዜናዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀበት፣የፖሊስ ሃይሉ ሕዝቡን አልጨፈጨፈም በማለቱ ትጥቁን እንዲፈታ የተገደደበት፣በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በአጋዚ ሰው በላ መርሲነሪ የታጠቀ ሃይል ሽብር የተለቀቀበት፣በመቶ የሚቆጠሩ የተገደሉበት፣በሽህ የሚቆጠሩ በላይ ታፍሰው በየእስር ቤቱ ለተወረወሩበት የበቀል ዱላ የተመዘዘበት በዚሁ ም በተገኘው የድል ማግስት ነው።የግንቦት ወር ብዙ መልካምና ጥቂት መጥፎ ነገሮችን ያየንበት
ወር ነው። በላይ ድምጽ አገኝቸ ተመርጫለሁ ብሎ መለስ ዜናዊ በምርጫ ታሪክ ውስጥ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ይሉኝታ ቢስ ውሸት የነዛበትና ተከታዩን ቀርቶ የውጭ ደጋፊውን የሃፍረት ካባ ያከናነበበት ወቅት ይኸው የግንቦት ወር ነው። አሁን የወያኔ አገዛዝ ውስጡን ብል እንደበላው እንጨት ተቦርቡሮ ለይምሰል ቆሞ የሚታይበት ወቅት ነው።የተባበረ ሕዝባዊ ሃይል ገርስሶ ሊጥለው የሚችልበት ሁኔታ ጎልቶ ይታያል።ስርዓቱ በቀውስ ላይ ቀውስ እየተደራረበበት
ብረትን ይባላልና የሕዝቡ ስሜት ሳይበርድና ሳይቀዘቅዝ መነሳሳቱን በአግባቡ መጠቀምና አገራችን ወደባሰ የቀውስ ባህር ውስጥ እንዳትገባ አስቸኳይ መፍትሄ መፈጠር አለበት።ያም መፍትሔ የተበታተነው የተቃዋሚ ጎራ በአንድነት ግንባር ሕዝቡን ለመምራት ሲወስንና በተግባር ሲገልጸው ነው። ለብቻ ለስልጣን የሚቋምጡበት፣በነጠላ ጉዞና ትግል አገርና ሕዝብ አድናለሁ፣የሌለ ሃይልና ጥበብ እኔ ብቻ አለኝ የሚሉበት፣የሕዝብን መከራና ችግር ለድርጅታዊ ዝናና ፕሮፓጋንዳ የሚጠቀሙበት ጊዜ አይደለም። ምንም እንኳን ወያኔ በውጥረት ላይ ቢገኝም መዘንጋት የለለብንና ማመን ያለብን ተቃዋሚው ጎራ የተዳከመ መሆኑንና በያዘው የተዝረከረከ አካሄድ ከቀጠለበት የሚያረካ ስራ ሳይሰራ፣ይህን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ተንገጫግጮ እንደሚቆምና ወያኔ የገጠመውን ችግር አሶግዶ መልሶ መቋቋም  እንደሚችል ነው።በገንዘብ፣ በወታደራዊ ሃይሉ፣በጸጥታው ሰንሰለቱ አሁንም ከተቃዋሚው የተሻለ ነው።ያንን ሃይሉን
ሰብሮ ለመጣል የሚቻለው በገሃድ በሚታይ በተባባረ ክንድ እንጂ ከፕሮፓጋንዳ መድረክ ከማያልፍ በነጠላ ድርጅት ነጭ ወሬ ዙሪያ ተጭበርብሮ በማጨብጨብ አይደለም። አልፎ አልፎም እንደ መስከረም ወፍ በአደባባይ ብቅ እያሉ



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>