Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ወጣቱ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ

$
0
0

ዛሬ በምሳ ሰዓት አካባቢ፤ በሱፍቃድ በጋሻው የተባለ ዕድሜው በሃያዎቹ ውስጥ የሚገመት ወጣት በቦሌ መንገድ ላይ ከአራት ጊዜ በላይ በተከታታይ ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን አጠፋ። ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ”ኑሮ መሮኛል” ሲል ተሰምቷል…

በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው
 ቦሌ መንገድ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኝ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የነበረው ወጣቱ በሱፍቃድ ለምሳ ተቀይሮ ሲገባ ከሥራ ባልደረባው ላይ የተቀበለውን የጥበቃ መሣሪያ ተቀብሎ ለጊዜው ምን እንደኾነ ያልታወቀ (እስካሁን እኔ ያላወኩት) ነገር እየተናገረ እየሮጠ ወደ ሰማይ አራት ጊዜ ያህል ከተኮሰ በኋላ አገጩ ላይ አስደግፎ ወደ ጭንቅላቱ በመተኮስ ራሱን አጥፍቷል።
በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው
በአሁኑ ሰዓት አስክሬኑን ሰማያዊ የሚበዛበት ዥንጉርጉር ጨርቅ ሸፍነውት መንገድ ላይ ተኝቷል። የደንብ ልብሱን እደለበሰ ሲኾን፤ አጠገቡ በጥይቱ የተበሳ ኮፍያው ወድቋል። የጭንቅላቱ ስጋ እና አጥንቶቹ ተበታትነዋል።
በሱፍቃድ አጋር የተባለው የጥበቃ ሥራ የሚሠራ ኤጀንሲ ተቀጣሪ መኾኑን እና ሕብረት ባንክ ከመጣ ሁለት ወር አካባቢ እንደኾነው የሥራ ባልደረቦቹ ነግረውኛል። አሁን በተገኘ መረጃ ”ኑሮ መኖኛል” ሲል ተሰምቷል። እዛ አካባቢ ያሉ ፖሊሶች ደግሞ በምን እንዳወቁ አላውቅም ከቤተሰቡ ተጣልቶ ነው ብለዋል። አሁን አስክሬኑኑን የፖሊስ መኪና አንስቶታል።
በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው
ምንጭ ኢትዮጵያ ዛሬ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>