የባህር ዳር ከተማ አንድነት ወጣቶቹ በሰልፉ ላይ ከተገኙ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተነግሯቸው የነበረ ቢሆንም ‹‹አገር ያቀናው አባቴ ተሰድቦ ዝም ማለት አልችልም››ብለው ፍርሃትን ሰብረው ሰልፉን ተቀላቅለዋል…
በከተማይቱ የባጃጅ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎችን ትናንት በማህበራቸው አማካኝነት በመሰብሰብ ሰልፉን የሚያጅቡ ከሆነ ባጃጆችን ከከተማ እንደሚያስወጡ ቢዝቱባቸውም‹‹ባጃጆቻችንን ጥለን በእግራችን ሰልፉን እንቀላቀላለን እንዳሉት ቃላቸውን ጠብቀው ተገኝተዋል፡፡ በጎጃም ክፍለሃገር ዋና ከተማ የሆነችው የባህር ዳር ከተማ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የሚከተለውን የዘር ማጥፋት ፖሊሲ መሰረት በማድረግ በፈጠረው የጎሳ ፈደራሊዝም መሰረት ያደራጃቸው ሆዳም የአከባቢው ተወላጆች የተሰጣቸውን ፍርፋሪ በመለቃቀም የአማራውን ህዝብ እየሰደቡት እንደሚገኙ የተመለከተው ኢቶጵያዊ ህዝብ በአንድነት በከተማው አደባባይ ወጥቶ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል በሚል መሪ ቃል የአማራን ህዝብ የሚያዋርዱ እና የሚሰድቡ መሪዎች እና ቅጥረኞቻቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ በአንድ ድምጽ በሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠይቋል።
ከ20ሺህ በላይ ህዝብ በተሰተፈበት በዚህ ሰልፍ ላይ የተለያዩ መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን ሃገራዊ ዘማዎች ተዚመዋል።የህዝብ አንድነት ታይቶበታል ለመንግስት ባለስልጣናት ነን ባዮች ከፍተኛ የሆነ እፍረት አልብሷቸዋል። ሰላማዊ ሰልፉ ከታዘለ ሕጻን ጀምሮ እስከ አዛውንቶች የተሳተፉበት እና የወጣቱ ተሳትፎ የጎላበት ነው። በሰልፍ ላይ የተገኘው ህዝብ ሰላማዊ ተቃውሞ ያሰማ ሲሆን በሰልፉ ላይ አቶ አለምነው በአማራ ህዝብ ላይ የተናገሩት የጥላቻ ንግግር በሞንታርቦ ለሰልፈኛው ተለቋል፤ ሰልፈኛውም በቁጭት በብአዴን ላይ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ “ክብራችንን የደፈሩት የብአዴን አባላት ለፍርድ ይቅረቡ” “ነፃነታችን በእጃችን ነው”
በሰላማዊ ሰልፉ እንዳይታደሙ ከአጎራባች ወረዳዎች የተንቀሳቀሱ ዜጎች እንዳይታደሙ የታገቱ ሲሆን “መተማ የኛ ነው፣ ቋራ የኛ ነው” በሰልፉ ላይ ከተስተጋቡ መፈክሮች መሀከል ይገኝበታል፡፡ ሰልፉ በህዝብ እንደታጀበ ቀትሏል፡፡ አብዛኛው ሰልፈኛ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል በሚለው መፈክር ባዶ እግሩን ከሰላማዊ ሰልፉ ተቀላቅሏል። የጸሐዩ ግለት አናት ይተረትራል፣እለቱም ኪዳነ ምህረትና የጾም መግቢያ ነው፡፡አንድ ዲያቆን ‹‹ኪዳነ ምህረት የዛሬ ወርም ትከበራለች ይህ መድረክ ግን በስንት አንዴ የሚገኝ በመሆኑ ሰልፉን አስቀድሚያለሁ ብሏል፡፡ ከባህር ዳር አጎራባች ከተሞች በተለያዮ የትራንስፖርት አቅርቦቶች በመሳፈር ወደ ሰላማዊ ሰልፉ ለመምጣት የተንቀሳቀሱ ሰዎች በሚሊሻዎች መታገታቸውን የሚገልጹ መረጃዎች እየደረሱን ነው።
የባህር ዳሩን የተቃውሞ ሰልፍ የአንድነት ፕሪዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከፊት መርተውታል። “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል፡፡” “ብአዴን የአማራን ህዝብ ለመምራት የሞራል ልዕልና የለውም” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተደምጠዋል ፡፡ድል የህዝብ ነው!! ድል የህዝብ ነው!! ድል የህዝብ ነው!! ድል የህዝብ ነው! ! ድል የህዝብ ነው!! ድል የህዝብ ነው!! ድል የህዝብ ነው!! ድል የህዝብ ነው! ! በማለት ህዝቡ በጋራ ዘምሯል።
በመጨረሻም የመኢአድ የትብብር ለዲሞክራሲ እና የአንድነት ፓርቲዎች መሪዎቻቸው ንግግር ያደረጉ ሲሆን አቶ አበባው መሃሪ የመኢኣድ ፓርቲ መሪ 1,አቶ አለምነው መኮንን በህግ እንዲጠየቅ 2፣ ብአዴን የአማራ ህዝባ ወኪል ነኝ ማለቱን እንዲያቆም 3,አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ አሳስበዋል፡፡
የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ በንግግራቸው የአቶ አለምነው እንዲህ እንዲናገሩ ያደረገውን አንባገነን ስርአት እንቀይር እንስራ ብለዋል፡፡ እንዲሁም የሰላማዊ ሰልፉን የመዝጊያ ንግግር የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዘዳንት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው አድርገዋል፡፡ኢንጂነሩ የመግቢያ ንግግራቸውን የከፈቱት ‹‹በዛሬው እለት እጅግ ደስ ካሰኙኝ መፈክሮች ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል የሚለው ነው በማለት ነበር፡፡
ግዛቸው ‹‹ፓርቲዎች የብቻ ሩጫቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አደርጋለሁ››የአንድነቱ ፕሬዘዳንት ኢንጂነር ግዛቸው በንግግራቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለየብቻ የሚያደርጉትን ሩጫና መጠላለፍ በማቆም ጠንካራ ፓርቲ በመመስረት ኢህአዴግን በአንድነት መታገል እንዲቻል ጠይቀዋል ፡፡ይህ ካልሆነ ግን የገዢዎችን እድሜ እኛው ራሳችን ለማርዘም እየሰራን እንደሆነ መታወቅ ይኖርብናል ፡፡ብለዋል፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ በድል ተጠናቋል።

posted by issa abdusemed