በተመሳሳይ በገርጂ የሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው በተቀመጡበት የሳሎን ወንበር በክራቫታቸው ታንቀው የተገደሉት የመገናኛ እና ትራንስፖርት ሚንስቴር ምኒስትር አቶ አየነው ቢተውልኝ ይገኙበታል። ባለስልጣናቱ የግፍ ጽዋ እንዲጎነጩ የተደረገው ከአቶ መለስ አመራር ጋር በፈጠሩት የሃሳብ (አመለካከት)ልዩነት ብቻ እንደነበር ሊሰመርበት ይገባል። በሌላም በኩል የፓርቲው አባል የነበረው እና በስቪል ሰርቪስ ኮሌጅ የ5ኛ አመት የህግ ትምህርት ሲከታተል የቆየው ጥላሁን መስፍን ሃምሌ 1996 አ.ም በበርካታ ጥይት የራስ ቅሉ ተቦዳድሶ ሞቶአል ።ግንቦት 1993 አ.ም. ኮሎኔል እሌኒ መለስ ለ11 ወራት በአንድ ክፍል ውስጥ ለብቻዋ ታስራ ተሰቃይታለች ።በዚያው ወቅት ወደ ታጠቅ ተወስደው ለ9 ወራት በእስር የተሰቃዩት የመከላከያ መረጃ ክፍል ሃላፊዎች ኮሎኔል ጎልያድ እና ኮሎኔል ኩህለን ሲጠቀሱ በታሰሩበት ወቅት ጎልያድ አእምሮው ተነክቶ ነበር ።ለረጅም አመታት ለእስር የተዳረገው ኮሎኔል አታክልቲ በርሄም የት እንደ ደረሰ አይታወቅም ።ይህ መኮንን በተስነይ ግንባር ከፍተኛ ጅግንነት የፈጸመ ኢትዮጵያዊ ነው ። ኢትዮ ሚድያ
