Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

እስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ አዲሱን የአንድነት አመራር «ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት» አላቸው፤

$
0
0

የ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማትን ያገኘውና በእድሜ ልክ እስራት በገዢው መንግስት ተበይኖበት ቃሊቲ የሚገኘው አንዷለም አራጌ ትላንትና ጠዋት ሊጠይቁት የሄዱትን አዳዲሶቹን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች «ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት፤.. ሕዝቡ መብቱን አውቆ ለመብቱ እንዲነሳ በማንቃት ለውጥ ለማምጣት ጠንክራችሁ ሥሩ፤ እንደምታደርጉትም ተስፋ አለኝ» ማለቱ ተገልጿል።

ባሳለፍነው ሳምንት የፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳን እና ካቢኔያቸውን በምርጫ አሰናብቶ በአዲስ የሾመው አንድነት ፓርቲ፤ አዳዲሶቹ ተሿሚዎች ስልጣናቸውን ከተቀበሉ በኋላ የመጀመሪያ ሥራቸውን ያደረጉት በእስር ቤት የሚገኙትን የፓርቲዎቻቸውን አባላት መጠየቅ ነበር። በዚህም መሠረት አዳዲሱ አመራር እስርቤት ከሚገኙት የድርጅቱ አመራሮችና አባላት የሚያበረታቱ ምክሮችን መቀበሉን ለመረዳት ተችሏል።

አንዷለም አራጌ በአዲሱና በወጣት በተገነባው የአንድነት ፓርቲ አመራር ደስተኛ መሆኑን ገልጾ «ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት፤ ሕዝቡ መብቱን አውቆ ለመብቱ እንዲነሳ በማንቃት ለውጥ ለማምጣት ጠንክራችሁ ሥሩ፤ እንደምታደርጉትም ተስፋ አለኝ» ብሏቸዋል። ይኸው የአንድነት ፓርቲ አመራር እዛው ቃሊቲ የሚገኙትን እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የሕሊና እስረኞችን ለመጠየቅ ጠይቆ መከልከሉ የታወቀ ሲሆን ወደ ዘዋይ ያመራው የአንድነት ፓርቲ ቡድን እዛው እስር ቤት የሚገኙትን የአንድነት የብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል መኮንንና በዚያ የሚገኙ ሌሎች እስረኞችን መጎብኘታቸውም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በሕወሓት/ ኢሕአዴግ አስተዳደር «በሽብርተኝነት ወንጀል» ተከሷል፤ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ ደግሞ የሕሊና እስረኛ ነው የሚባለው አንዷለም አራጌ ከዚህ ቀደም ከእስር ቤት ተቃዋሚዎች የእኔን እስር ቤት መማቀቅ ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም፤ ሕዝቡን ለማታገል ልትጠቀሙበት ትችሉ ነበር ሲሉ የነበረውን ድክመት መግለጹ አይዘነጋም።



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>