Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ፍርድ ቤቱ በአቶ መላኩ ፈንታ ያለመከሰስ መብት ላይ እልባት ሰጠ

$
0
0

አዲስ አበባ ግንቦት  9  2005 – ዛሬ  የዋለው የፌደራሉ ከፍተኛ  ፍርድ ቤት ሁለተኛ  ወንጀል  ችሎት በሙስና  ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉትን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር… አቶ መላኩ ፈንታን  ያመለከሰስ  መብት ጉዳይ  ተመልክቷል ።

 

ፍርድ ቤቱ ባለፈው ማክሰኞ  በዋለው ችሎት  የተጠርጣሪው ጠበቃ ደንበኛቸው የአዲስ አበባ  ከተማ  ምክር ቤት አባል ናቸውና ያለመከሰስ መብታቸው ተጥሷል  የሚል አቤቱታ  አቅርበው ነበር ።

ፍርድ ቤቱም  አቶ መላኩ  ፈንታ  ያለመከሰስ መብታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ  ይዘው  ለዛሬ እንዲቀርቡ  አዞ ነበር ።

በዚህም መሰረት  አቶ መላኩ ፈንታ  ሚያዚያ 16 ቀን 2000 ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ  የምክር ቤት አባል  ሆነው መመረጣቸውን የሚገልፅ  መታወቂያ  አቅርበው ነበር ።

የፌደራል  የስነ ምግባርና  ፀረ ሙስና  ኮሚሽን የመርማሪ ቡድን  በጉዳዩ ላይ  ምላሹን እንዲሰጥ  ተደርጓል ።

በዚህም  መሰረት  የመርማሪ ቡድኑ  እንዳስረዳው በኢትዮጵያ የምርጫ  ቦርድ አሰራር  መሰረት የአቶ መላኩ ፈንታ  ያለመከሰስ መብት  የቆይታ ጊዜ አብቅቷል ።

ግንቦት 2005 ዓመተ ምህረት የምርጫ ሂደት ያሸነፉ የከተማዋ ምክር ቤት አዲስ አባላት ስም ዝርዝርን  የምርጫ ቦርድ ይፋ በማድረጉ ጥቂት የሽግግር ቀናት ካልሆነ በስተቀር አቶ መላኩ ፈንታ ያለመከሰስ መብት አላቸው የሚል አሰራር የለም ብሏል ።

ፍርድ ቤቱም ግራና ቀኙን ተመልክቶ የአቶ መላኩ ፈንታ  ጉዳይ በመዝገቡ በተጠረጠሩ ሌሎች ስድስት ግለሰቦች ላይ የተጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፀንቶ ለግንቦት 19 ቀን 2005 ዓመተ  ምህረት እንዲቀርቡ ወስኗል ።

በጥላሁን ካሳ

source shegar



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>