የሲዳማ ዞን አስተዳደር ‹‹ የመልካም አስተዳደር ችግርንና ሙሰኝነትን ለመዋጋት ›› በሚል ርዕስ በአለታ ወንዶ ከነዋሪዎችር ለመወያየት በማሰብ በአደባባይ የጥሪ ወረቀት ይለጥፋል፡…. ነገር ግን የስብሰባው ሰዓት እየተቃረበ በመጣበት ሰዓት በአደባባይ የተለጠፈው የጥሪ ወረቀት እንዲነሳ ይደረግና የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑ ሰዎች የጥሪ ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡ የተለጠፈው ወረቀት መነሳቱን ያላወቁና ስለ ከተማቸው መልካም አስተዳደር ችግርና ስለ ሰፈነው ሙሰኝነት የዞኑን አመራሮች ለማነጋገር የተዘጋጁት የአለታ ወንዶ ነዋሪዎች ስብሰባው የሚደረግበትን የሚሊኒየም አዳራሽ ከአፍ እስከ ገደፉ ይሞሉታል፡፡
Image may be NSFW.
Clik here to view.
Shiferaw Shigute, Head of SNNP
ከስብሰባው መሪዎች አንዱ የሆኑት የሲዳማ ዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሚልዮን ማቲያስ በድንገት የድምጽ መነጋገሪያ መሳሪያውን በመጠቀም ‹‹በስብሰባው እንድትሳተፉ የጥሪ ደብዳቤ ከደረሳችሁ ሰዎች ውጪ ያላችሁ በሙሉ አዳራሹን ለቅቃችሁ እንድትወጡ ይህንን ባታደርጉ ግን ሁከት ለመፍጠር እንዳሴራችሁ በመንገር በፌደራል ፖሊስ በኃይል አዳራሹን
ለቅቃችሁ እንድትወጡ አደርጋለሁ›› በማለቱ ህዝቡ ግርግር ከመፈጠሩ በፊት አዳራሹን ለቅቆ ወጥቷል፡፡ በአዳራሹ የቀሩት ጥቂት ሰዎች ዞኑ ምንም አይነት የመልካም አስተዳደርና የሙሰኝነት ችግር እንደሌለበት በመነጋገር ስብሰባውን ማጠናቀቁን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገልጸዋል፡፡
Related articles
- ኦባንግ ለኬሪ የጥሪ ደብዳቤ ላኩ! (yourfreedomvoice.wordpress.com)
- Ethiopian Youth Initiative: Nurturing the Culture of Giving Back (kweschn.wordpress.com)
Image may be NSFW.
Clik here to view.

Clik here to view.
