Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 938

የዛሬው የሸዋበር መስጂድ ደማቅ ተቃውሞ ውሎ!

$
0
0

ዛሬ የደሴ ሙስሊም በመንግስት ከፍተኛ የሆነ በደል ቢፈፀምበትም የበላይነቱን አሳይቷል፡፡ የመንግስት ተላላኪ የሆኑት ኢማሞች በጊዜ አሰግደው ተቃውሞውን እንዳያኮላሹት በወጣው መርሀ ግብር መሰረት ሙስሊሙ በጊዜ መስጂዱን ሞላው… ኹጥባ ከመደረጉ በፊት በመንግስት ኃይል የመስጂድ ኮሚቴ ተደርገው የተሾሙት ግለሰብ መንግስትን ማሞካሸት እና ሙስሊሙን ለማስፈራራት ሲሞክሩ ውስጡ የተቃጠለው የደሴ ሙስሊም በተክቢራ ያስቆማቸዋል፡፡ ለትንሽ ጊዜ ንግግራቸው በተክቢራ ቢቋረጥም መልሰው ‹እኛ ረብሻ አንፈልግም፡፡ ረብሻለሁ የምትሉ ከሆነ ግን ይሄው በውጨኛው ማይክ ነው የምንናገረው ፖሊሶች እርምጃ እንዲወስዱ እንፈቅድላቸዋለን› የሚል አሳፋሪ ንግግራቸውን በአላህ ቤት ውስጥ ተናግረው ጨረሱ፡፡ … ኢማሙ የመጀመሪያውን ኹጥባ አድርገው ሁለተኛውን ኹጥባቸውን ሲጀምሩ ሙስሊሙ የዝሁርን ሶላት መስገድ ይጀምራል፡፡ ኹጥባው አልቆ ሶላት ተቆመ፡፡ የሙስሊሙም ልብ ተክቢራ ለማሰማት ይደልቅ ጀመር፡፡ በመጨረሻም የብሶት ማሰሚያ ሰዓቱ እንደደረሰ ኢማሙ አሰላምተው ሲጨርሱ የጌታችንን ታላቅነት በምንመሰክርበት ቃል ተክቢራ ሁሉም በአንድ ላይ ‹አላሁ አክበር!› በማለት የሸኽ ያቁት መስጂድን አናወጡት፡፡ ከመስጂዱ ውስጥና ከመስጂዱ የውጭ ክፍል የብሶት ድምፆች ተስተጋቡ! ከባድና አስፈሪ የሆነው የደሴ ሙስሊሞች ድምፅ መስጂዱን አናወጠው፡፡ ይህ የተቃውሞ ድምፅ ኃይሉ በጨመረ ጊዜ ሰላም የማይወዱት የእነ ‹እሾህ ኑሩ› ቡድኖች ከውስጠኛው መስጂድ ከመንግስት የተሰጣቸውን ዱላ በመያዝ በሰላማዊው ሙስሊም ላይ እጃቸውን አነሱ! ዱላ አንስተው ሙስሊሙን መማታት የጀመሩት አቶ አሊ እና አቶ እሸቱ የሚባሉ የመንግሰት ቅጥረኞች ነበሩ፡፡ ረብሻ አንፈልግም በሚል ሰበብ ራሳቸውን ረብሻውን ቀሰቀሱት! ሙስሊሙ የሚደርስበትን በደል በውስጡ እንደያዘ የተክቢራ ድምፁን ማሰማቱን ቀጠለ፡፡ ተቃውሞው በበረታባቸው ጊዜ ዲንጋይ መወርወር ጀመሩ፡፡ በደሉ ከልክ ባለፈ ጊዜ ፍርሀት እንዳይመስል ሙስሊሙ ራሱን መከላከል ጀመረ! ዱላቸውን በመቀማት ባዶ እጃቸውን አስቀሯቸው፡፡ ይህን ተከትሎ ‹እሾህ ኑሩ› የድረሱልን ጥሪውን አስተላለፈና ፖሊሶች መስጂዱን ጥሰው ገቡ፡፡ ይህን ጊዜ የአላህ ቤት ነውና የደሴ ሙስሊም መስጂዱን ለቆ በመውጣት በሸዋበር አደባባይ ላይ መፈክሩን ከፍ አድርጎ ያሰማ ጀመር፡፡ ‹ባገራችን ሰላም አጣን! በቤታችን መስገጃ አጣን! በሱቃችን መስገጃ አጣን!› የሚሉትን መፈክሮች አስተጋባ፡፡ የአድማ በታኞች በቦታው ደርሰው ሙስሊሙን ይማቱ ጀመር! የደሴ ሙስሊም እየተደበደበም፣ ደሙ እየፈሰሰም ተቃውሞውን ቀጠለ፤ ጥንካሬውንም አስመሰከረ! ደም የጠማቸው የመንግስት ውሾች በሙስሊሙ ላይ ድብደባቸውን ሲፈፅሙ ሁሉም ወደ ቤቱ መሄድ ጀመረ፡፡ ለውሻ መልስ አይሰጥምና ጀርባውን ሰጥቷቸው ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ይህ ጊዜ “ለምን ተሸነፍኩ?” በሚል ይመስላል እየተከተሉ መደብደብ የጀመሩት፡፡ የጥይት ቃታቸውንም ሳቡ፡፡ ነገር ግን የደሴ ሙስሊም ሌላም ቀን አለና ቀጠሮ ሰጥቷቸው ይህ የመጨረሻ አለመሆኑን አሳይቶ የቤቱን በራፍ ፊታቸው ላይ ዘጋባቸው! በሙስሊሙ የተናቁትም የመንግስት ውሾች በየቤቱ እየዞሩ አንዳንድ ወንድሞቻችንን አፍሰው ወሰዱ! የዚህ ዓይነት የመንግሰት ትንኮሳና ህግ ጥሰት የነበረ ቢሆንም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ግን የዛሬውን ተቃው በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ኢንሻአላህ ዛሬ በድል እንደተወጣነው ሁሉ ነገም እንደግመዋለን! “ጅራፍ እራሱን ገርፎ እራሱ ይጮኻል” እንደሚሉት ድብደባ የደረሰባቸው ወንድሞቻችንን ደሴ ሆስፒታል ለህክምና የሄዱትን እዛው በፖሊሶች በመክበብ አስታማሚውንም ሆነ ሊጠይቃቸው የሚመጣውን ሰው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን በመሳሪያ በማስፈራራት እየመለሱ ይገኛሉ፡፡ መቼም ቢሆን ተሸንፈን አናውቅም! ወደፊትም ኢንሻአላህ አንሸነፍም! ድል ለተጨቆነው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች! አላሁ አክበር!See more



Viewing all articles
Browse latest Browse all 938

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>