
ከዚሁ የተነሳ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች ሁሉ ይህንኑ በመቃወም ርዕዮት ዓለሙን ጨምሮ ሌሎችም በግፍ ታስረው በእስር ቤት እየተሰቃዩ ናቸው ያላቸው እስረኖች ይፈቱ ዘንድ እንዲተባበሩ ዓለም ዓቀፍ ጥሪ ኣቅርበዋል። ርዕዮት አለሙ በዘመናችን ወደር በሌለው ጀግንነት ከሚወደሱት ጥቂት ኢትዮጵያን መካከል ትጠቀሳለች ያለው ድርጅቱ ለመፃፍ ነፃነቱዋ እና በኣጠቃላይ በመብት ተሟዋጋችነቱዋ በምትከፍለው መስዋትነት ሁሉ ድጋፋችን እንደማይለያት እናረጋግጣለን ብለዋል።
CPJ የተሰነው የጋዜጠኖች መብት ተሟጋች ድርጅትም እንዲሁ የእስር ቤቱ ኣያያዝ እንዲሻሻል ከመጠየቁም ባሻገር ርዕዮት ዓለሙን ጨምሮ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ያለኣንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ኣሳስበዋል። ያም ሆኖ በእስር ቤቱ የእስረኖች ኣያያዝ እየተባባሰ እንጂ እየተሻሻለ ኣለመሆኑን ነው ዘገባዎች የሚጠቁሙት በተለይም ርእዮት አለሙን የሚጎበኑ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን በመቃወም ከመስከረም 1 – 5 ድረስ የረሃብ አድማ ማድረጉዋን ወላጅ አባትዋ እና ጠበቃዋ አቶ ዓለሙ ጎቤቦ ዛሬ ለዶቸቤሌ ኣስረድተዋል።
የጋዜጠና ርዕዮት አለሙ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ መሆኑን እና ሞራልዋም ቢሆን ብርቱ መሆኑን የገለጹት አቶ አለሙ የኣመክሮ መብትዋን ተጠቅማ ከወህኒ ቤቱ እንዳትፈታም በለስልጣናቱ ከወዲሁ በሰበብ ኣስባቡ ሴራ እየጠነሰሱ ነው በማለት ይወቅሳሉ።
ጋዜጠና ርዕዮት አለሙ በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር ህግ ተከሳ የታሰረችው በሰኔ ወር 2003 ዓ ም ሲሆን በተያዘባት የወንጀል ጭብጥ የ14 ዓመት እስራት ከተበየነባት በሁዋላ በይግባን ወደ 5 ዓመት ዝቅ ብሎላታል ከዚህ ሁሉ ሂደት ጋርም ጋዜጠና ርእዮት ዓለሙ ባለፈው ዓመት የ2013 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠና ተብላ በ ዓለም ዓቀፉ የትምህርት እና የባህል ተቐም UNESCO ኣማካንነት ዓለም ዓቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ማሸነፍዋ ይታወሳል።
Related articles
- ርዕዮትና እስክንድር የአውሮፓ ህብረት በሚያዘጋጀው “ሻካሮቭ የነጻነት ሽልማት” የ2013 ተሸላሚ ለመሆን ከሰባቱ እጩዎች ውስጥ ገቡ፡፡ (ethioandinet.wordpress.com)
- ርዕዮትና እስክንድር የአውሮፓ ህብረት በሚያዘጋጀው “ሻካሮቭ የነጻነት ሽልማት” የ2013 ተሸላሚ ለመሆን ከሰባቱ እጩዎች ውስጥ ገቡ፡፡ (gettg83.wordpress.com)
