ነሃሴ ወር አጋማሽ ሶርያ መንግስት በመርዘኛ ጋዝ ተጠቅሞአል ለተባለበት ወንጀል፤ ምዕራባዉያን አሳድ ላይ የአየር ጥቃት ለማካሄድ እቅዳቸዉ ላይ በሁለት ወገን የተከፈሉ ይመስላል። ሶርያ መንግስት በበኩሉ የኬሚካዊ መሳርያ ጥቃትን እንዳልፈጸመ እየገለፀ ነዉ…
ዋሽንግተን ፣ ሶሪያና የመርዘኛ ጋዝ ጦር ማሳሪያ ጉዳይ፤
ዩናይትድ እስቴትስ ፣ የሶሪያው ፕሬዚዳንት በሺር ኧል አሰድ፣ ያላቸውን የመርዘኛ ጦር መሳሪያ ሁሉ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካስረከቡ ፣የጦር እርምጃ አይወሰድባቸውም ስትል የማስጠንቀቂያ ጊዜ መስጠቷ ተነገረ። አሰድ መሣሪያ ማስረከብ የሚለውን ትእዛዝ ሆነ ጥያቄ እስካሁን አልተቀበሉትም። ዩናይትድ እስቴትስ ፣ የበሺር ኧል አሰድ ወታደሮች፤ ነሐሴ 15 ቀን 2005 ፤ የመርዘኛ ጋዝ ጦር መሣሪያ በመተኮስ፤ ከ 1,400 በላይ ሲቭሎችን ገድለዋል ስትል ተጠያቂ አድርጋለች።
በአሁኑ ጊዜ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፤ በሶሪያ ላይ የጦር እርምጃ ይወሰድ ዘንድ፣ ምክር ቤቱ እንዲስማማ ለማግባባት በመጣር ላይ ናቸው። ሩሲያ ግን፤ ከሶሪያ መንግሥት ጎን በመቆም፤ ዩናይትድ እስቴትስ በጦር ኃይል ለመደብደብ ያላትን ሐሳብ ውድቅ እንድታደርግ ጠይቃለች። የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ፣ ከሶሪያው አቻቸው ዋሊድ ኧል ሙዓለም ጋር ሞስኮ ውስጥ ባደረጉት ውይይት፤ ማንኛውም ጥረት መደረግ ያለበት የሰላም ጉባዔ እንዲካሄድ ማብቃት መሆኑን ገልጸዋል። ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የሚያስከትለው ቢኖር የተስፋፋ አሸባሪነትን ይሆናል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ትናንት ፓሪስ ውስጥ ፣ ከዐረብ መንግሥታት ማኅበር ተወካዮች ጋር የተወያዩት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ እንዲህ ብለዋል።
« ዩናይትድ እስቴትስ የምትሻው ፣ብቻዋን ሳይሆን ፣ ከሌሎች ጋር፤ ቁጥራቸው በዛ ካለ አጋሮች ጋር፣ በማበር የመርዘኛ ቅመማትን ጦር መሣሪያ በተመለከተ ደንቡ እንዲከበር ማስገደድ ነው። በሶርያ ጣልቃ ለመግባት ፣ ከአንደኛዉ ቡድን ለመወገን ፣ ወይም የሶርያዉን የእርስ በርስ ጦርነት የራስዋ ጉዳይ አድርጋ ለመረከብ አይደለም»
የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር፤ ለሶሪያ መፍትኄ ይሆናል ስላሉት የአገራቸውን አቋም እንዲህ ነበረ ያስረዱት–
« የሶርያ ተቃዋሚ ወገን መሪዎች ባለፈዉ ዓመት ሰኔ 23 ጄኔቭ ስምምነት የተደረሰበትን የመፍትሄ ሃሳብ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ይቻል ዘንድ የሰላሙን ጉባዔ ያላንዳች ቅድመ ግዴታ የሚደግፉ ስለመሆናቸዉ ግልጽና የማያዳግም ፈቃደኝነታቸዉን ያረጋግጡ ዘንድ ከመጠየቅ አንቦዝንም»
ይህ በአንዲህ እንዳለ፣ አሜሪካ ሶሪያን ብትደበድብ ፣ለፈጠር የሚችለውን የኑክልየር አደጋ የተባበሩት መንግሥታት የአቶም ኃይል መ/ቤት ይመርምር ስትል ሩሲያ አሳሰበች። አሜሪካ ፤ ይህ ከመ/ቤቱ ኀላፊነትም ሆነ። ሥልጣን ውጭ ነው በማለት አልተቀበለችውም።
ያ ወዳጅ ሩስያም ዩኤስ አሜዪካ በሶርያ ላይ ጦርነት ከማንሳት ይልቅ ለሰላም ስምምነቱ ጥረት ብታደርግ ይሻላል ስትል ዛሪ አስታዉቃለች። የዩኤስ ኤዉ ዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ በበኩላቸዉ ሶርያ ያላትን የኬሚካል መሳርያ በሳምንት ግዜ ዉስጥ ካስረከበች የአየር ጥቃቱ እንደሚነሳ ተናግረዋል። የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ዩናይትድ ስቴትስ በሶርያ ላይ ጦር ከማንሳት ይልቅ የሰላም ድርድር ጥረት ብታደርግ ይሻላል በሚለዉ ሃሳብ ላይ ሀገራቸዉ ከሶርያ ጋር መስማማቷን ገልጸዋል። እንደ ሰርጌ ላቭሮቭ አሜሪካ በሶርያ ላይ ያቀደችዉ የአየር ጥቃት ሽብርተኛነት እንዲስፋፋ ምክንያት ይሆናል።
« በሶርያ ጣልቃ ለመግባት ከአንደኛዉ ቡድን ለመወገን ወይም የሶርያዉን የእርስ በርስ ጦርነት የራስዋ ጉዳይ አድርጋ ለመረከብ አይደለም» የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ በሶርያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት እንዲደረግ በሚለዉ አቋም ከአስር የማያንሱ የአሜሪካንን አቋም የሚከተሉ ደጋፊዎች እንዳላት ትናንት ፓሪስ ላይ መናገራቸዉ ይታወቃል። ዛሪ ለስድስት የቴሌዥን ጣንያ ቃለ ምልስ እንደሚሰጡ የተነገረዉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሶርያ ላይ ይደረግ ያሉትን ወታደራዊ ቅጣት ለማካሄድ አሜሪካዉያን እና የኮንግረስ አባላትን ለማሳመን የተቻላቸዉን ሁሉ እንደሚያደርጉ ነዉ የገለፁት። በሌላ በኩል የሶርያ ወዳጅ የሆነችዉ ሩስያ ዩናይትድ ስቴትስ በሶርያ ላይ ጥቃት እንዳትጥል እየታገለች ትገኛለች። የሶርያ ፕሬዚዳንት ባሽር አልአሳድ ጅምላ ጨራሽ መሳርያን እንዳልተጠቀሙ በተደጋጋሚ መግለፃቸዉ ይታወቃል። የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭና የሶርያዉ አቻቸዉ አል ሞአላም፤ ዛሪ ሞስኮ ላይ ተገናኝተዉ የተመድ የኬሚካል መሳርያ መርማሪ ቡድን ሶርያ ዉስጥ ዳግም ተመልሶ እንዲያጣራ ግፊት በማድረግ ዩናይትድ ስቴትስ በሶርያ ላይ የሰነዘረችዉን እጇን እንዳታነሳ አስጠንቅቀዋል። የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቭሮቭ ከጦርነቱ ይልቅ ለሰላም ዉይይት ለመድረስ ጥረት ማድረግ ይገባል ይላሉ፤
አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደነገገን ቀይ መስመር የሶርያ መንግስት መጣሱን የምትከሰዉ፤ ሶርያ ዉስጥ ነሃሴ ወር አጋማሽ የተቃዋሚ ደጋፊዎች በሚገኙባቸዉ ከደማስቆ ወጣ ባለ አካባቢ በተተኮሰ ጅምላ ጨራሽ መሳርያ 426 ህፃናትን ጨምሮ ከአንድ ሽህ በላይ ሰዎች መገደላቸዉን ተከትሎ መሆኑ ይታወቃል።
አሁን በደረሰን ዘገባ መሰረት ደግሞ ሩስያ፤ ሶርያ ያላትን የኬሚካል ጦር መሳርያ በዓለማቀፉ ማሕበረሰብ ቁጥጥር ስር በማድረግ ከዩናይትድ ስቴትስ የአየር ድብደባና ዉድመት እንድትድን ጠይቃለች። ይህን የገለፁት የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ናቸዉ።
አዜብ ታደሰ ተክሌ የኋላ
Related articles
- አዛውንቷ፣ ሾላውና ዋርካው (The Elderly Lady and Two Trees) (kweschn.wordpress.com)
- የመለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ ሰመሃል መለስ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ 5 ቢሊዮን ዶላር በ2011 ኣስገብታለች። (ethioandinet.wordpress.com)
