Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

አንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለው የሰላሚዊ ሰልፍ ትግል ዛሬ በአዳማ ከተማ በሰላም ተጠናቀቀ :;

$
0
0

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል በጎንደር፣ ደሴ፣ ባህር ዳር፣ ጂንካ፣ ወላይታ ፣ባሌ ሮቢ፣ ፍቼና አርባ ምንጭ ተካሂዶ የነበረው የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ደግሞ በአዳማ ከተማ ተደርጎ በሰላም መጠናቀቁን የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከስፍራው ዘገበ…

UDJ-Dr-hailu-Areaya

እንደ ጋዜጠኛው ዘገባ በዛሬው የአዳማ ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት ፌደራል ፖሊሶችን በማሰማራት፣ የሰልፉን መንገድ በማስቀየርና በኢቲቪ በኩል ድራማ ለማሠራት ቢሞርክም እንዳልተሳካለትና ከምንም በላይ ሰልፉ በሰላም ተጠናቆ ሕዝቡ ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማበት ነው።

በአዳማ ከተማ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የአንድነት የምዕራብ ቀጠና ሃላፊ አቶ አስናቀ ሸንገማ በኦሮምኛ ቋንቋ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስዮም መንገሻ እንዲሁም ዶክተር ሃይሉ አርአያ ንግግር ማድረጋቸውን የገለጸው ጋዜጠኛው ስልፈኛው በመፍክሩ መንግስትን የተለያዩ ጥያቄዎችን ጠየቋል፡ ከነዚህም መካከል፦ – ውሸት ሰልችቶናል – የኢቴቪ የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም ከአሸባሪነት አይለይም – ድህነት በፕሮፓጋንዳ ብዛት አይጠፋም – ሰብዓዊ ልማት ለሁሉም – ስራ ማግኘት የዜግነት መብት ነው – አምባገነኖች ባሉበት የአንዷለም ቤት እስር ቤት ነው – ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለችም – ድሌ ዛሬ ነው! ድሌ ዛሬ ነው ድሌ ድሌ ድሌ የሚሉ መፍክሮችን እነዚሁ ከፍርሃት የተላቀቁ ኢትዮጵያውያን አሰምተዋል።

አንድነትየሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል ላለፉት 3 ወራት በመላው ኢትዮጵያ በመዘዋወር ሕዝቡን በሰላማዊ ሰልፍ በማደራጀትና ፊርማ በማሰባሰብ ሲያደርገው የቆየውን ሰላማዊ ትግል በመቀጠል የፊታችን እሁድ ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በመስቀል አደባባይ ት ዕይንተ ሕዝብ መጥራቱን ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት መዘገቧ ይታወሳል።



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>