የአንድነት ፓርቲ አመራሮች መንግስት በባሌ ሮቤ ያሰበውን የደም ማፋሰስ ሴራ አክሽፈዋል አንድነት ፓርቲ ዛሬ በባሌ ሮቤ የሚያደርገውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በኦህዴድ ባለስልጣናትና በደህንነት ሀይሎች አፈና ተፈፀመበት…. ሰልፉን ለማደናቀፍ የአካባቢው ባለስልጣናት ትላንት ምሽት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ካረፉበት ታይታኒክ ሆቴል ንብረታቸውን ሳይዙ በግዳጅ እንዲወጡ ከመደረጉም በላይ አብዛኞቹ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ታግተዋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና የቅስቀሳ ቡድን አባላት ደህንነት አደጋ ላይ እንደሆነም ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ በባሌ ሮቤው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ መንግስት ያደራጃቸው ሀይሎች ሁከት ለመፍጠር መዘጋጀታቸው በመታወቁ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ሰልፉ እንዲሰረዝ ወስኗል፡፡ – See more
የአንድነት ፓርቲ አመራሮች መንግስት በባሌ ሮቤ ያሰበውን የደም ማፋሰስ ሴራ አክሽፈዋል፡፡የአከባቢው ባለስልጣናት ያደራጇቸው ሀይሎች ሰልፉ በሚካሄድበት ወቅት ግጭት ለፈጥሩ ተዘጋጅተው እንደነበር ታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ አመራሮች በሳል ውሳኔና ሀገር ወዳድ የባሌ ዞን የፖሊስ አካላት ለፓርቲው በሰጡት መረጃ መንግስስታዊ ውንብድና ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ -
በሌላ ዜና
አንድነት ፓርቲ በፍቼ ከተማ እያካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በአማርኛ በኦሮሚኛ መፈክሮች እየተስተጋቡ ነው ፡፡
Image may be NSFW.
Clik here to view.

Clik here to view.
