Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ሰበር ዜና በአንዋር መስጂድ የጁምአ ሰላት ይሰግዱ የነበሩ ሙስሊምቸ ተደበደቡ፡፡

$
0
0

በዛሬው የጁምአ ሶላት ላይ በአንዋር መስጅድ በተገኙ እናቶችና እህቶች ላይ የዱላ ናዳ አውርዷል :የኢህዴግ ታጣቂዎች በሙስሊም እህቶቻችን ላይ ይህን አይነት ጥቃት የፈፀመበት ምክንያት ከመስጅዱ ግቢ ውጭ መስገድ አይቻልም በሚል ያልተለመደ ሰበብ መሆኑ መንግስት ሙስሊሙን ለመጨፍለቅ ቆርጦ መነሳቱን በግልፅ የሚያረጋግጥ ተግባር ነው:

የጁምአ ሶላት በሚሰገድባቸው ሁሉም መስጅዶች የሰጋጆች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ከመስጅዱ ቅጥር ግቢ ውጭ ወጥቶ መስገዱ ለአመታት የተለመደ መሆኑ የማይታበል ሆኖ እያለ ዛሬ ወያኔ ህዝበ ሙስሊሙን በተለይም እህቶቻችን ለማጥቃትና አሸማቆ ከመስጅድ ለማስቀረት እንደ ጮማ ምክንያት ተጠቅሞበታል:

በጭቆና ብዛት የሚጠነክር አቋም እንጅ በዱላና በማሸማቀቅ የሚደበዝዝ አላማ ይዘን እንዳልተነሳን ወያኔ መገንዘብ ተስኖታል ።



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>