በሀገራችን ከቀን ወደ ቀን እያደጉና አየገዘፉየመጡትን የህዝብን የለውጥ ጥያቄዎችኢህአዴግ አጥጋቢ መልስ ሊሰጥ አልቻለም፡፡እነዚህ የለውጥ ጥያቄዎች መልስ ሊያገኙያልቻሉበት ዋንኛ ጉዳይ፣ የሀገሪቱ ተቋማትለህዝቡ ጥያቄ የሚመጥን መልስ መስጠትየማይችሉ በመሆናቸው ነው…
በአጭሩየተቋማቱ ውድቀት እንደሆነ ያለምንም ብዥታእንረዳለን በሃይማኖት ተቋማት ላይ ተነሱ የሕዝብጥያቄዎች ብንመለከት፡፡ ኢህአዴግ አገሪቱንከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እጁን በቀጥታበሃይማኖቶች ውስጥ ማስገባቱን እንረዳለን፡፡በነጋ በመሸ ቁጥር ብዙ የሚባልለትህገ-መንግስት “መንግስት በሃይማኖት፣ሃይማኖት በመንግስት ጉዳይ ጣልቃአይገባም” ቢልም፣ በተግባር ግን ሕዝብየሃይማኖት መሪዎቹና በመንግስት ካድሬዎችመካከል ያለውን ልዩነት መለየት የተቸገረበትወቅት ላይ ነው የደረሰው፡፡
የሙስሊሙህብረተሰብ ላለፉት ዓመታት ጠንካራየሃይማኖት ተቋም እንዲኖረው ያለማሰለስጠይቋል፡፡ በ1997 ዓ.ም. መደረግየነበረበትን የሃይማኖቱ መሪዎች ምርጫ እስካሁን ባለመደረጉ
በተለያዩ አጋጣሚዎች ቅሬታውን ሲገልጽ ሰንብቷል፡፡
መጅሊሱከኢህአዴግ ተላላኪነት ራሱን አውጥቶ፣ ሕዝበ ሙስሊሙን እንዲመራ ያለመሰልቸት ጠይቋል፡፡ እነዚህን የሕዝበ ሙስሊሙጥያቄዎች፣ መጅሊሱ መፍትሄ ሊያበጅለት አልቻለም፡፡
ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች በእንዲህ እንዳሉ፣ መንግስት በግልጽ የአንድ ሃይማኖት አስተሳሰብ በሙስሊሙ ላይ ለመጫንተነሳ፡፡
ይህን አስተሳሰብ ለማስረፅ በተዘጋጁ ስልጠናዎች ላይ መንግስት በግልጽ የዚህ አስተሳሰብ ደጋፊነቱን ማወጁ፣ብዙዎችን አስደነገጠ፤ አስቆጣም፡፡ ዘወትር የሚምልበትን ሕገ-መንግስት በግላጭ ጣሰ፡፡ ሰልጣኞቹ በካድሬዎች እየተመለመሉሥልጠና እንዲወስዱ ዋንኛ ስራ አድርጐት ቀጠለ፡፡ ይህን ድርጊቱን የተቃወሙ ሙስሊሞችን “አክራሪዎች” የሚል ተለጣፊስም
በመስጠት ልዩነቶችንና አለመግባባቶችን ይበልጥ እንዲሰፉ አደረገ፡፡ በዚህ መሃል መጅሊሲ የመፍትሄው አካል መሆንሲገባው፣ የችግሩ አካል ሆኖ በግልጽ ወጣ፡፡
የሙስሊሙን ህብረተሰብ መሠረታዊ የመብት ጥያቄዎች ኢህአዴግ አጥጋቢ በሆነ መልኩ ሊቀርፋቸው ሲገባ፤ የህዝበሙስሊሙን ወኪሎች እንደለመደው ለቁጥር የሚያዳግት ታፔላ ለጠፈባቸው፤ በህገ-ወጥነት፣ በተላላኪነት፣ በአሸባሪነት፣በሃይማኖት ጽንፈኛነት /አክራሪነት/፣ በፀረ-ሰላምና ፀረ-አንድነት፣ በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካ አጀንዳ የሚያራምዱ፣ የነውጥኃይል ወደሚል ፍረጃ ገባ፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ ግን እጅግ ጨዋነት በተሞላበት፣ ከስሜት በወጣና ብዙዎቻችን ባስደመመመልኩ፣
ፍጹም ሰላማዊ የሆነ ተቃውሞውን ቀጠለ፡፡
በዚህ ሰላማዊ እንቅስቃሴ የተበሳጨው ኢህአዴግ፣ የጸጥታ ኃይሎችን ወታደሮችንእና ፌደራል ፖሊስን በማሰማራትሙሰሊሙ ላይ ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ ወስዷል በዚህም ጥቂት የማይባሉ ወንድሞቻችን ና ወገኖቻችንን ገድሏል፤መስጂድ ሰብሮ በመግባት የተከበሩ የእምነት ተቋማትን ክብር ደፍሯል፡፡ በመጨረሽያም በህዝበ ሙሲሊሙ የተመረጡ የኮሚቴአባለትን ና ጋዜጠኞችን በጅምላ አስሯል፡፡
በቅርቡ አምኒስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በታሰሩትየሙስሊም ተወካዮች ላይ የሰባዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ዘግቧል በአፋጣኝ እንዲያቆምም ጠይቋል፡፡ በተለይ የሙስሊሙመሪዎች ላይ ድብደባና ቶርቸር መፈጸሙን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
የሃማኖት ተቋም ነጻነት ጥያቄ አንግበው የተነሱ ወገኖችን ላይ የደረሰውን የሰባዓዊ መብት ገፈፋን አጥብቀን እናወግዛለን፤ በዚህተግባር የተሳተፉ አካላትም የፈጸሙት የሰባዓዊ መብት ጥሰት
በኃላፊነት እንደሚያስጠይቃቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ በዱላ፣ በጠመንጃና በእስር መፈፀሙ አይፈታም ብለን እናምናለን፡፡ የህዝበ ሙሰሊሙ ጥያቄሊፈታ የሚችለው የኔ የሚለው፣ ሊወክለው የሚችል፣
ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የፀዳ ነጻና ጠንካራ ተቋም ሲመሰርት ብቻነው፡፡
በክርስትና የሃይማኖት ተቋማት (በተለይም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ) ውስጥ የሚታየው ጉድ፣ ከሙስሊሙ ተቋማ ከሚታየውችግር ከአስር እጥፍ በላይ የገዘፈ ነው የሚል እምነት አለን፡፡
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ከእስር ከተፈቱ በኃላከአሜሪካ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር ያደረጉትን ወይይት ዊኪሊክስ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
በዚህ ውይይት ላይ አቶ ታምራትእንደገለጹት “የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስን በእኔ ፊርማ ከቦታቸዉ እንዲነሱ አድርጌ፣ ለእኛስርዓት ይሰሩልናል ያልነዉን እንዲሾሙ አድርገናል”
ብለዋል፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ውስጥ ተቋማዊ አሰራር ብሎ ነገር የለም፡፡ ሲኖዶሱ ትርጉም ያለው አካል መሆን አልቻለም፤ተሰብስቦ የሚወስነው ውሳኔ ተግባራዊ አይሆንም፡፡ በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የመንግሰት ከፍተኛ ባለስጣናት እየተገኙየሚፈልጉትን ውሳኔ እያስወሰኑ ወንጀል ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡፡ “
ለምን? እንዴት?” በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ጳጳሳትመስቀላቸውን እያስቀመጡ ቤተመንግሥት እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ ዛቻና ማስፈራሪያ ተፈጽሞባቸዋል፤ በመኖሪያቸውውስጥም የተደበደቡ አባቶች አሉ፡፡
መንግሥት ካላጣው መሬት በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ታላቅ የቅድስና ቦታ ተደርጎ የሚቆጠረውን ዋልድባ ገዳምበእብሪትና በማን አለብኝነት በልማት ስም ደፍሯል፡፡
የዋልድባ ገዳም መጋቢና የገዳሙ ምሰሶ ሆነው በዙሪያው የሚገኙ ሶስትቤተክርስቲያናትን አፈራርሶል፡፡ በገዳሙ ውስጥ ለረጅም ዓመታት በምንኩስና የሚኖሩ አረጋዊያንና ገዳሙን
የሚያገለግሉ“አትንኩብን፤ የእምነት ነፃነታችን ይከበር” ብለው ቢጮሁ “ፀረ-ልማት፤ ሽብርተኞች”እያለ አሸማቋቸዋል፡፡
ኢህአዴግ ከአፈጣጠሩ ስናየው ሁሉን የመቆጣጠር አቅጣጫ የሚከተል ኃይል ነው፤ ቀጥተኛ የሆነውን የሙስሊሞችን የተቋምነጻነት ጥያቄ እንኳን መፍቀድ የማይፈልግ አምባገነን ነው፡፡
በመሠረቱ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍልስፍና በኢኮኖሚ በፖለቲካም ሆነ በማህበራዊ ዘርፍ ከሱ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ተቋማትን በሀገራችን እንዲያብቡ በፍፁም አይፈቅድም፡፡
ያለፉት21 ዓመታት ሂደቱ በግልጽ የሚያሳየው ይህንኑ ነው፡፡
ነጻ ተቋማት ሊኖሩ የሚችሉት ዴሞክራሲና ነጻነት በተከበረበት ሀገር ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም ሁላችንም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓትምስረታና ለሰባዓዊ መብቶች መከበር ለሚደረገ ትግል የድርሻችንን ልናበረክት ይገባል፡፡
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
Related articles
- በጥሩነሽ መሪነት ኢትዮጵያ ፓሪስ ላይ ‘ወረራ’ ፈጸመች። ከ1ኛ እስከ 5ኛ አግኝተናል። (sebhatamare.wordpress.com)
- አዛውንቷ፣ ሾላውና ዋርካው (The Elderly Lady and Two Trees) (kweschn.wordpress.com)
