Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 937

አያት አክሲዮን ማህበር ላይ የ90 ሚልየን 81 ሺህ 270 ብር ቅጣት – አመራሮቹ ከ10 እስከ 12 አመት እስራትና እስከ 90 ሚልየን ብር ተቀጡ

$
0
0

በ21 ክሶች የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈበት የአያት አክስዮን ማህበርና አመራሮቹ ዛሬ ከ10 እስከ 12 አመት በሚደርስ ጸኑ እስራትና እስከ 90 ሚልየን ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ተጣለባቸው።

ከዛሬ ሶሰት ዓመት በፊት የተከሰሱት 1ኛ ተከሳሽ አያት አክስዮን ማህበር ፣ የማህበሩ ስራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢው አቶ አያሌው ተሰማ ፣… ዶክተር መኮንን አካሉ እና አቶ ጌታቸው አጎናፍር ናቸው የተቀጡት። ከክሶቹ መካከል የገንዘብና የባንኮችን አዋጅ መጣስ የሚለው ቀዳሚው ነው ።

ማህበሩ ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማትን በተደራጀ መልኩ በመተካት የዱቤ ቤት ሽያጭ አገልግሎት አከናውኗል የሚለው በክስ መዝገባቸው በዝርዝር ቀርቧል። በመሆኑም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርደ ቤት 8ኛው የወንጀል ችሎት በእነዚህና በሌሎች ጥፋቶች ፥ አያት አክሲዮን ማህበር ላይ የ90 ሚልየን 81 ሺህ 270 ብር ቅጣት ወስኖበታል።

እንዲሁም የማህበሩ ስራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ አያሌው ተሰማ ደግሞ ፥ በ12 አመት ጽኑ እስራተ እና ከ3 ሚልየን ብር በላይ የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

ዶክተር መኮንን አካሉ በ12 አመት ጽኑ እስራትና ከ436 ሺህ ብር በላይ ፥ እንዲሁም አቶ ጌታቸው አጎናፍር ላይ ፍርድ ቤቱ የ10 ዓመት ፅኑ እስራት እና የ411 ሺህ 969 ብር ቅጣት ወሰኗል።

ችሎቱ ድርጅቱ ያለአግባብ ሰብስቦ ከአከማቸው ገንዘብ ከ86 ሚልየን ብር የሚበልጠው እንዲወረስም ወስኗል።

አክስዮን ማህበሩና ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አያሌው በ21 ክሶች ያካበቷቸው 15 የሚሆኑ የተለያ አገልግሎት የሚሰጡ የግንባታ መሳሪያዎች እንዲወረሱ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል። አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ)



Viewing all articles
Browse latest Browse all 937

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>