1, የመቀሌው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲተላለፍ ተወሰነ መንግስት አንድነት ፓርቲ በመቀሌ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በኃይል አደናቀፈ… የመቀሌ ከተማ አስተዳደር በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አመራሮችን በህገወጥ ሁኔታ በማሰር፣ከመቀሌ ለቅቀው እንዲወጡ በማስጠንቀቅ እንዲሁም ቅስቀሳ ሲደረግባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችን በአደባባይ በመንጠቅ በመቀሌ በቂ ቅስቀሳ እንዳይደረግ በማድረግ ሰላማዊ ሰልፉን በኃይል አደናቅፏል፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ኮማንድ ፖስት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ መንግስት በመቀሌ የወሰደውን ህገወጥ እርምጃ በመገምገም በነገው እለት የተጠራውን ሳላማዊ ሰልፍ እንዲተላለፍ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በቅርቡም በመቀሌ ከተማ በተጠናከረ ሁኔታ ዳግም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ በመወሰን ሰልፉ የሚያደርግበትን ቀን በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ጀግናው የመቀሌ አዋሪ የመንግስትን ህገወጥ እርምጃ በማውገዝ ለአንድነት ፓርቲ አመራሮች ያሳየውን አጋርነት በማድነቅ በመቀሌ ከተማ በቅርቡ የሚጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በንቃት እንዲጠባበቅ ጥሪን አስተላልፏል፡፡
2, እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው የኢህአዴግ መልስ በጉጉት ይጠበቃል
አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስበው የነበሩት ኮንግረንስ ማን ክሪስ ስሚዝና ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተጠቆመ።
3, የፌደራል ፖሊስ አባላት በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ በከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን የኢሳት ዘጋቢዎች ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘወትር አርብ የሚደረገውን የጁመአ ስግደት አስታኮ የተቃውሞ ድምጹን የሚያሰማ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ መዛቱ ይታወቃል።
4, የቀድሞ የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በኮበለሉ በአንድ ወራቸው ተያዙ
ያለመከሰሰ መብታቸው በፓርላማ እንዳይነሳ ከተወሰነ በኋላ እንደገና ፓርላማው ውሳኔውን በማጠፍ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳውና ወዲያውኑ ባልታወቀ ሁኔታ ከአገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩት የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ በትላንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡:
5, የሞጋቤ ፓርቲ በከፍተኛ ድምፅ ማሸነፉ ተገለፀ
ዚምባብዌ ውስጥ በተደረገ ምርጫ አገሪቱን ለበርካታ ዓመታት በተከታታይ በፕሬዚዳንትነት የመሩት አንጋፋው ሮበርት ሙጋቤ በከፍተኛ ድምፅ ማሸነፋቸውን የአገሪቱ የምርጫ ቦርድ አስታወቀ። እንደ ዚምባብዌ የምርጫ ቦርድ መግለጫ ከሆነ የ89 ዓመቱ አንጋፋ ሮበርት ሙጋቤና ፓርቲያቸው ዛኑ ፒ ኤፍ ከሁለት ሶስተኛ በላይ የምክር ቤት ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው ታውቋል። ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ ንቅናቄ MDC የተሰኘው ተፎካካሪ ድርጅት የምርጫውን ውጤት መቼም ቢሆን ዕውቅና እንደማይሰጠው አስታውቋል። የሮበርት ሙጋቤ ወነኛ ተፎካካሪ የዚምባብዌ ጠቅላይ ሚንስትር ሞርጋን ሻንጋራይ ምርጫውን «ቧልት» ሲሉ ውጤቱን ደግሞ «ባዶና እርባና ቢስ» በማለት ክፉኛ ተችተውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተመድ ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን በዚምባብዌ ተከስተዋል የተባሉት የምርጫ ህፀፆች ዘገባ ላይ ምርመራ እንዲደረግ አሳስበዋል።
ምንጭ:- ኢሳት, ዶይቸ ቬለ, ፍኖተ ነፃነት, yihune88.wordpress.com
Related articles
- የግብጽ መከላኪያ ሚንስተር በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ግዜው ገና ነው አሉ (ethioandinet.wordpress.com)
- ‘አንድነት’ ፓርቲ፡- የሕዳሴ ግድብ ባለቤት አልተለየም (+video) (yasyasre.wordpress.com)
- ኢትዮጵያ ከቦትስዋናው በተጨማሪ ባለፈው በ አዲስ አበባ ስታዲየም ደበቡ አፍሪካን በያሸነፈችበት ነጥብ ሊቀነስባት ይገባል በማለት የደቡብ አፍሪካ ሚዲያዎች ጥያቄ እያቀረቡ ነው።Bafana on the brink as Ethiopia may lose more points (addis12.wordpress.com)
- ሙሴቪኒ ለግብፅ መንግስት ማስጠንቀቀያ ሰጡ…President Yoweri Museveni has sternly warned the Egyptian (addisuwond.wordpress.com)
