አምባገነኖች ሥልጣናቸውን ዘለዓለማዊ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም። በተለይ እንደ ትግራይ ፋሽስቶች በራስ የመተማመን ብቃት የሌላቸው በዘር ላይ የተመሰረቱ ውህዳን ጥላቸውን ሳይቀር ስለሚፈሩ የአፈና መዋቅራቸውን በቤተክርስቲያን፣በመስኪድና በትምህርት ቤቶች ሳይቀር ይዘረጋሉ,,,, ከዚህም በተጨማሪ አፋኝ ሕጎችን በየጊዜ ያወጣሉ። የሚወጡት ሁሉ ሕጎቹ አሻሚና እጅግ በጣም የተለጠጠ ትርጉም እንዲሰጡ ተደርገው ነው። ምክንያቱም ሕጎቹ የሚወጡት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታስቦ ሳይሆን የወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም ታቅዶ ብቻ በመሆኑ ከሕጋዊነት ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘትን ይላበሳሉ፤ሕብረተሰቡም የወያኔ እንጂ የኢትዮጵያ ሕጎች ብሎ አይቀበላቸውም።
በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ውስጥ አንድ የወያኔ አባል አምስት የወያኔ አባል ያልሆኑ ግለሰቦችን ይሰልላ። ከላይ እደተገለጸው ይህ ስለላው በሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ በዋናነት የወያኔ አባል ባልሆኑ መምህራንና ሰራተኞች እንድሁም ተማሪዎች ላይ ይካሄዳል። በተለይ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው በሚጠረጠሩ መምህራንና ሠራተኞች ላይ የጠነከረ ከመሆኑም ባሻገር በየዕለቱ በክፍል ውስጥ የሚናገሯቸው የትምህርት ይዘት ያላቸው ቃላትን እንደ ጸጉር እየተሰነጠቁ በየትምህርት ቤቶቹ ከተቋቋሙት የወያኔ ህዋሳት የሃይል መድረክ እስከ ከፍተኛው የወያኔ የፖለቲካ አመራር ድረስ ሪፖርት እየተደረገ በእያንዳንዱ መምህር ስም ባዘጋጁት የግል ማህደር መዝግበው በመያዝ የትምህርት፣ የሥራ፣ የሥልጠና የዕድገት ፣ … ወዘተ ዕድል ሲገኝ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዳይሆን ነጥሎ ለመምታት ይጠቀሙበታል።
በገጠርም አርሶ አደሩን አንድ ለአምስት በሚል በልማት ሥም በማደራጀት የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን አርሶ አደሮች ማዳበሪያ፣ምርጥ ዘርና ሌሎች የግብርና ግባቶችን በመከልከልና የይዞታ ማረጋገጫ ደብተራችሁ ትነጠቃላችሁ ብሎ በማስፈራራት የወያኔ ደጋፊና አገልጋይ ሆነ እንዲኖሩ ያስገድዳል።
Related articles
- ‘አንድነት’ ፓርቲ፡- የሕዳሴ ግድብ ባለቤት አልተለየም (+video) (yasyasre.wordpress.com)
