ብርበራው ቀኑን ሙሉ እንደሚደረግ ታውቋል በደቡብ ወሎ ዞን በሀይቅ ከተማ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ቤት ላይ ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ብርበራ እንደተጀመረ የዞኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ….
የአንድነት ፓርቲ የወረባቡ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ እድሪስ ሰኢድ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ “የጦር መሳሪያ ሰውራችኋል” በሚል ፖሊሶችና ሚኒሻዎች በሀይቅ ከተማ ባሉ ከ16 በላይ በሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት መኖሪያ ቤት ውስጥ ብርበራ አካሂደዋል፡፡ ብርበራው ከተካሄደባቸው አመራሮች መሀከል አንዱ የሆኑት የወረዳው የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ኃላፊ አቶ አራጌ ሑሴን ለሪፖርተራችን እንደገለፁት 5 ፖሊሶችና 1 ሚሊሻ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምረው መኖሪያ ቤታቸውን ፈትሸዋል፡፡ አቶ አራጌ ሁሴን አክለውም “እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ ምንም አታገኙም አልኳቸው፤እንዳልኩትም 2 ሰዓት የፈጀ ብርበራ አድርገውም አንዳች ሳያገኙ ወጥተዋል” በማለት ገልፀዋል፡፡
“ብርበራው መንግስት በአንድነት አባላት ቤት ውስጥ የጦር መሳሪያ አገኘሁ በሚል የተለመደ ድራማ ለመስራት እንደተዘጋጀ የሚያስረዳ ነው” ያሉት የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን ሰብሳቢ አቶ ብስራት አቢ ኢህአዴግ የደቡብ ወሎ ህዝብ በግዳጅ አንድነት ፓርቲን እንዲያወግዝ በተለያዩ ከተሞች ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፎችን እንደጠራ አስረድተዋል፡፡ በአንድነት አባላት ቤት የሚደረገው ብርበራ እስከ ምሽት ሊቀጥል እንደሚችልም ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡
Related articles
- የመለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ ሰመሃል መለስ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ 5 ቢሊዮን ዶላር በ2011 ኣስገብታለች። (ethioandinet.wordpress.com)
- ‘አንድነት’ ፓርቲ፡- የሕዳሴ ግድብ ባለቤት አልተለየም (+video) (yasyasre.wordpress.com)
- የሳውዲ መንግስት ከጁላይ 3 በኋላ ህገወጦችን ለማደን በየቤቱ አሰሳ እንደሚያካሂድ አሳሰበ ወገን ሁኔታችሁን አስተካክሉ (addisuwond.wordpress.com)
- ኢትዮጵያ ከቦትስዋናው በተጨማሪ ባለፈው በ አዲስ አበባ ስታዲየም ደበቡ አፍሪካን በያሸነፈችበት ነጥብ ሊቀነስባት ይገባል በማለት የደቡብ አፍሪካ ሚዲያዎች ጥያቄ እያቀረቡ ነው።Bafana on the brink as Ethiopia may lose more points (addis12.wordpress.com)
