Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

አንዲት ፀሎት፤ ጥቁር ለባሾችን ከነጭ ለባሾች ይጠብቅልን!

$
0
0
ግንቦት 17 የአፍሪካ መሪዎች በአዲስ አበባየአፍሪካ ህብረትን 50ኛ አመት በዓል ትንሽ ሰብሰብ ብለው ሊያከብሩ እና ትንሽ ሰብሰብ ብለው ሊያሸልቡ ተቀጣጥረዋል…

ብዙ ጊዜ የውጪ ሀገር እንግዶች ወደ ኢትዮጵያ ለስብሰባ መጥተው ሲወጡም ሆነ ሲገቡ መንገዱ ታጥሮ የሰው ዘር ዝር ብሎ አይተው ስለማያውቁ ሀገራቸው ሲሄዱ አዲሳባ የፌደራል ፖሊሶች እና የቤተመንግስቱ ጠባቂዎች መኖሪያ ብቻ ሳትመስላቸው አትቀርም፡፡

945335_581602011857560_385163152_n

የሰማያዊ ፓርቲ ልጆች  እንዳሰቡት ከተሳካላቸው፤ ለአፍሪካ መሪዎች እና ለሌሎቹም እንግዶች በሀገሪቷ ውስጥ ከፌደራል ፖሊስ እና ከቤተመንግስቱ ጠባቂዎች ሌላም ሰው መኖሩን እናሳያለን ብለዋል፡፡ ሰው ብቻም ሳይሆን በመንግስቱ ላይ ያዘነ ማቅ የለበሰ ሰው አለ የሚለውን ለማሳየት ጥቁር እንለብሳለን ሲሉም ጨምረዋል፡፡

በአንፃሩ ደግሞ የመንግስት ሰዎች ቢቻል ቢቻል በዕለቱ ጥቁር የለበሰ ሰው በአዲሳባ ከተማ እንዳይኖር፤ ይሄ ፈፅሞ የማይቻል ከሆነ ደግሞ ህዝቡ ጥቁር የለበሰው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀዘን እንደሆነ ለእንግዶቹ ገለፃ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሰሞኑን በውጪ ሀገር የሚገኝ አንድ ወዳጄ የፌስ ቡክ ስዕልህን ጥቁር በማድረግ ለጥሪው ያለህን ድጋፍ አሳይ ብሎ በውስጥ መስመር ነግሮኝ ነበር፡፡ እኔ ግን እንዲህ ያለውን እንቅስቃሴ በውጪ ያለ ሰው በሚደግፍ ጊዜ የሚባለውን ነገር ሳላደርገውም ብዙ ጊዜ ተብያለሁና ውጡም ሳልል ግቡም ሳልል ልበሱም ሳልል አውልቁም ሳልል በጥቅሉ ድጋፌ በቅስቀሳ ሳይሆን በፀሎት ቢሆን ይሻላል አልኩ፡፡

…እናንተ ውጪ ሆናችሁ ሀገር ውስጥ ያለውን ሰው ልታስጨርሱ… የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ፤ እርግጥ ነው እነዚህ ሰዎች “እናንተ ውጪ ሆናችሁ ሀገር ውስጥ ያለውን ሰው ታስጨርሳላችሁ…” ሲሉ ቢደመጡም እነርሱም ሲፋቁ… ሀገር ውስጥ ቁጭ ብለው ሀገር ውስጥ ያለውን ሰው የሚያስጨርሱ መሆናቸው ተደርሶበታል፡፡

የሆነው ሆኖ ግን እነርሱ የሚሉትን ለማሳጣት በሚል ስትራቴጂ እኔ እና ሌሎች በውጪ የምንገኝ ወዳጆቼ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ጥቁር ለብሶ የመዋል ቀን የምንደግፈው በፀሎት እንዲሆን ተስማምተናል… (በቅንፍም ከሁለት ወዳጆቼ ጋር ብቻ እኮ ነው የተስማማሁት… ሃሃ…)

ለማንኛውም ሰማያዊ ፓርቲ ከግንቦት 15 እስከ ግንቦት 17 ድረስ ሁሉም በያለበት ጥቁር ለብሶ በመንግስት ላይ ማዘኑን እንዲያመለክት ጥሪ አቅርቧል፡፡ እኛም  የሆነ ቀን ግር ብለን መጥተን ራሳችን ተሳታፊ የምንሆንበት ቀን እስኪመጣ ድረስ፤ ጥቁር ለባሾች በነጭ ለባሾች ጥቃት እንዳይደርስባቸው በፀሎት እንተጋለን…



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>