Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 945

የአገዛዙ ካድሬዎች የወረደ ተግባርን ይመልከቱ !

$
0
0

የአገዛዙ ካድሬዎች ላለፉት በርካታ ሳምንታት የአንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለዉን ሰላማዊና ሕዝባዊ ቅስቃሳ ከግቡ እንዳይደርስ ለማድረግ፣ በአለቆቻቸው ታዘው የተለያዩ የአፈና እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ እንደነበረ በሰፊት ተዘግቧል… በርካታ ታሰረዋል፤ ወከባና እንግልትም ደርሶባቸዋል። ነገር ግን የአንድነት አባላትን ደጋፊዎች እንደዉም ሕዝቡ እግዚአብሄር የሰጣቸውን የዜግነት መብት ለማረጋገጥ ቀርተዉ የተነሱ ይመስላል። አፈናዉ የበለጠ እየጨመረ በመጣ ቁጥር የሕዝቡን ድጋፍና መነሳሳትም ወደ ላይ ሄደ እንጂ አልቀነሰም።

ሕዝቡ እያሳየ ባለው ታላቅ ተነሳሽነት ተስፋ የቆረጡ የአገዛዙ ካድሬዎች የአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎች የሚለጥፋቸውን ፖስተሮችና መፈክሮች በማንሳትና በመቀዳደድ ጸረ-ዴሞክራሲያዊና ጸረ-ሕዝብነታቸውን እያሳዩ ነዉ። አንዳንድ ፖስተሮች አልቀደድ ሲላቸው ደግሞ፣ በላዩ ላይ ጭካ እስከመቀባት የደረሱበት ሁኔታም አለ።

በኢሕአዴግ ካድሬዎች ጭካ የተቀባ የአንድነት ፖሶተር ይመልከቱ !

dirty_work_of_cadresjpg



Viewing all articles
Browse latest Browse all 945

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>