Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

“ለሐገሬ ምን ሠራሁ እንጂ ሐገሬ ምን ሠራችልኝ አትበል፡፡”

0
0
By Umer Faruq (Ethio Al-Habeshi) ቅድመ ማሳሰቢያ፡ ይህንን ፅሁፍ እስከመጨረሻው ሳያነቡ እባክዎን አስተያየት ለመስጠት አይቸኩሉ፡፡ ትናንት በገባሁት ቃል መሠረት ፅሁፌን እነሆ ብያለሁ፤ መልካም ንባብ፡-
ይላል ዕውቁ የነፃነት ታጋይ እና 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብረሃም ሊንከን…. ይህን አባባል በጥልቅ የተረዱት አሜሪካውያን እንደተባለው ለሐገራቸው መስራትን አስቀደሙ፡፡ ሐገራቸውም እንደ ሐገር ጥቁር ነጭ እያለች የበደል ፅዋ ታፈራርቅባቸው የነበረውን ጎጂ ብሒሏን እርግፍ አድርጋ በመተው ልጆቿን አንዱን ካንዱ ሳትለይ አቀፈች፡፡ ጥቁር የበታች ነው፤ ይህ ጥቁሮች የማይማሩበት ት/ቤት ነው፤ እና የመሳሰሉ በርካታ በድብቅ ሳይሆን በገሃድ ትተገብራቸው የነበሩትን እኩይ ተግባራት፡ ተይ አይበጅሽም ሲሏት ከመሪር ትግል በኋላም ቢሆን ለዕድገቷ በማሠብ እንደ “አንዳንዶቹ” ተሳስተሻል አትበሉኝ ብላ እልህ ውስጥ ሳትገባ ስህተቷን አረመች፡፡ ሐገር እና ህዝብ ተጋግዘውም ከነበሩበት የበታችነት አዘቅት ውስጥ ወጥተው በነፃነት እና ኃያልነት ማማ ላይ ሲፈናጠጡ “ያልነቃው” የዓለም ክፍል እርስ በርሱ እየተናከሰ አጀባቸው፡፡ እንደ አትሌት ኃይሌ በዓይናቸው በብረቱ እየተመለከቱ አሜሪካ በጣጥሳቸው ወደፊት ገሠገሠች፡፡ ይህ ነው የህዝብ ሉአላዊነት ውጤት፡፡ አንባገነንነትን የፊጥኝ ያሉቱ እነ ሶቪየት ህብረት፡ የተመኩበት ኃይል ከመፈረካከስ አላዳናቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የኛው ሶሻሊስት አንባገነን መንግስቱ ኃ/ማሪያም ከአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው ጦር ቢያዘጋጅም ህዝብ እንጂ መሳሪያ ለጭንቅ ቀን አይሆንምና እያጨበጨበ ቀኑን ሲቆጥርለት የነበረው የገዛ ህዝቡ ምንነታቸውን ከማያውቃቸው ሽርጥ ለባሽ ጎፈሬ ታጋዩች ጋር ሆኖ ገረሠሠው፡፡ መንግስቱ ኃ/ማሪያም ላይ በዋነኛነት የህዝቡን ጥርስ ያስነከሰበት ምግባሩ ልማት ማጓደሉ ነበርን? ትምህርትን አለማስፋፋቱና መሐይምነትን አለማጥፋቱ ነበርን? በፍፁም!

ደርግን የተኩት ባለተራዎች በልማት ብቻ የህዝብ ልብ እንደሚገኝ በማሠብ ሌላ ነገር አትጠይቁን አሉ፡፡ ግንብ እና አስፋልት ላይ እኮ የሚንፈላሠሠው ስጋዬ ነው፡፡ ስጋዬ ውስጥ ደግሞ በነፃነት መኖርን ከምንም በላይ የሚሻ ህሊናና ሠብአዊ ማንነት አለኝ፡፡ የስጋዬ ደስታም ሆነ ሐዘን የሚገለፀው በዚያ መታፈንን በማይሻው ሠብአዊ ማንነቴ ውስጥ ነው፡፡ እንደውሻ አንገቴን አስረው መሮጥ ሲያምረኝ እያጠበቁ የምሮጠው እነርሱ ሲፈቅዱ እንጂ እኔ ሲያሻኝ እንዳልሆነ እያሳዩኝ በሚያምር አስፋልት ላይ ቢነዱኝ እና ጣፋጭ አጥንት ቢያስግጡኝ አንጀቴ ውስጥ ጠብ ሊል ይችላልን? ስለ ሠብዓዊ መብቴ መከበር ስጠይቅ “ግንብ እና አስፋልት ሠርተንልሃል” ብለው መመለሳቸው በራሱ ለኔ “ግንብ ውስጥ ከኖርክ ምን አነሰህ?” አይነት የንቀት ንቀት ነው፡፡ መናገር የፈለግኩትን ተናግሬ፤ ስጠይቅ ተሠምቼ፤ ስመርጥ ድምፄ ተከብሮ ቆሎ ቆርጥሜ፡ የሳር ቤት ውስጥ ያለፍርሃት እና ያለሠቀቀን መኖር ካሁን አሁን መጥተው በተቃዋሚነቴ / በሙስሊምነቴ አሠሩኝ፤ ገደሉኝ፤ ልጄን፡ ወንድሜን፡ እህቴን አልያም አባቴን ያለማንም ሃይ ባይ ጎትተው ወሠዱብኝ እያልኩ እየተሳቀቅኩ ቪላ ቤት ውስጥ ከመኖር (ያውም እድሉ ካለኝ) ሺህ ጊዜ ይበልጥብኛል፡፡ ኢህአዴግ ከደርግ እና ዓለም ካወቀቻቸው በርካታ አንባገነን መንግስታት ፍፃሜ ትምህርት ሊቀስም በፍፁም አልቻለም፡፡ ርዕሴን አልዘነጋሁም፤ በጥሞና ይከተሉኝ፡፡

በ “ዘመቻ ህዳሴ ግድብ” የመሳተፍ እና ያለመሳተፍ ጉዳይ የሐገር ጉዳይ ብቻ ነውን?

መግቢያዬ ላይ በጠቀስኩት ታሪካዊ ጥቅስ፡ አብረሃም ሊንከን “ሀገሬ ምን ሠራችልኝ አትበል” ሲል አንተ ያቅምህን ለሐገርህ ስትታገል የልብህን ለማድረስ ሃገርህ እጇ ቢያጥር አትውቀሳት ለማለት እንጂ አንተ ደፋ ቀና ስትልላት “የአይንህ ቀለም አላማረኝም” ብላ ብታስርህ እና ብትገርፍህ አሜን ብለህ ተቀጥቀጥ ለማለት እንዳልሆነ የሚያግባባን ይመስለኛል፤ እርሱም በጥቁርነቱ ሲጨቆን ያንን አላደረገምና፡፡ በዚህ አግባብ በአሁኑ ሠዓት እኔ ለሐገሬ የማበረክተውን እና ሐገሬ ለሠራሁት ሥራ ተገቢውን ክፍያ ያልከፈለችኝ “እጅ አጥሯት” ነው ብዬ በአብረሃም ሊንከንኛ ባቀነቅንም፡ መብቴን ባልኩ የተቀጠቀጥኩበት እና የገርባ እና የአሳሳ ወንድም እህቶቼ እንደሌላው ኢትዩጲያዊ ወገናቸው የተገደሉበት ማናለብኝነት እና ትምክህት ለአብረሃም ሊንከን ቢደርስ ቢያንስ ለዛሬዋ ሐገሬ (መንግስቴ) ባለዕዳ እንደማያደርገኝ አምናለሁ፡፡ ወዴት እያመራሁ እንደሆነ የተገነዘባችሁ ይመስለኛል፡፡ ኦዎን! በአሁኑ ሠዓት ሐገሬ ኢትዩጲያ “ህዳሴዋን” እንዳታበስር ጠላት ተሠድሮባታል፡፡ ክፉውን ያርቀውና አካባቢው ጦርነት ጦርነት መሽተት ጀምሯል፡፡ በሀገሬ ጥቅም የመጣ ማንኛውም (ማንኛውም ይሰመርበት) ጠላት ያው ጠላት ነው፡፡

በዚህ አቋማችን ባንለያይም ይህን ጠላት ለመፋለም የኢህአዴጓ ሐገሬ “በክፉ ቀኔ” ሳትደርስልኝ በክፉ ቀኗ ብትጠራኝ የሚኖረኝ ምላሽ ምክኒያቴን ላላገናዘበ ማንኛውም አንባቢ ላይዋጥለት ይችላል፡፡ በርግጥም ሐገሬ እንደስከዛሬው በኢህአዴግ እየተመራች ከየትኛውም ጠላት ጋር ለፍልሚያ ብትጠራኝ አልሰማትም፡፡ ይህን የምለው ፖለቲካን ከሐገር መለየት ተስኖኝ አልያም ሐገሬን ኢትዩጲያን ከማንም ያነሠ አፍቅሬ እንዳይመስላችሁ፡፡ እንዲያውም ጥሎብኝ ከልጅነቴ ጀምሮ የሐገሬ ነገር አይሆንልኝም፡፡ በኢትዩ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ዕድሜዬ ለአቅመ ጦርነት ባይደርስም ከተዋጉት ባልተናነሰ ትንፋሼ ቁርጥ እስኪል ሁለመናዬ አይንና ጆሮ ሆኖ የሐገሬን ድል በጉጉት የተጠባበቀው ማንነቴ አሁንም አለ፡፡ ኢትዩጲያዬ ላይ እንኳን ሠይፍ የመዘዘባትን ቀርቶ በሠላማዊው የእግር ኳስ ሜዳ የተገዳደራትን እንኳን በዙሪያዬ ኳሱን ከሚከታተለው ህዝብ በተለየ ብርድ እንደመታው ጥርሴ እየተንገጫገጨ ከውስጥ በሚንተገተግ የሐገር ፍቅር ስሜት ድሏን በጭንቀት እጠባበቅ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ከሐገሬ ውጪ እንደሌላው ለ አርሴና ማንቼ የማውሰው አይንም የኳስ ፍቅርም አልነበረኝም፡፡ ይህ የሐገር ፍቅር ከደም የተቀላቀለ የማንነት መገለጫ እንጂ ሲፈልጉ የሚገዙት ሲፈልጉ የሚሸጡት ሸቀጥ አይደለም፡፡ ዛሬም ወደፊትም ይኖራል፡፡ እንዲህ የሆንኩላት ሐገሬ ግን ሳትፈልግ መሪዋን በጨበጡ ሽፍቶች አገለለችኝ፡፡ እንኳን በአደባባይ፡ ሻሂ ቤት ቁጭ ብዬ ለምተነፍሳት ቃል ሁለት ጊዜ እንዳስብ አስገድዳ ያለጥፋቴ ስትፈልግ የምትገርፈኝ ስትፈልግ የምትዘርፈኝ ባሪያዋ አደረገችኝ፡፡ መብት የሚባል ነገር በፍፁም እንዳልጠይቅ ፤ አንገቴን ደፍቼ እንድገዛ ፈረደችብኝ፡፡ መንግስቴ የገዛ የሐይማኖት መሪዬን እራሴው ልምረጥ የሚለውን ሊያሳስር እና ሊያስገድል ቀርቶ ሊያስገለምጥ የማይገባውን ህገመንግስታዊ እና ሠብዓዊ መብቴ የሆነውን ጥያቄዬን ሳይቀበል ዛሬ አንተን ሲቀጠቅጡ የነበሩትን “ቀይ ለባሽ” ውሾቼን ሊመታብኝ የመጣ አካል አለና፡ ና ተከላከልልኝ ቢሎ ባንቺ ስም ቢጠራኝ እና ባልሠማው ሐገሬም አትታዘቢኝም፡፡

ሐገሬ የዘንድሮ በደልሽ መች ተቆጥሮ ያልቅና? ሌላው ቀርቶ ከምንም ነገር ጋር ሊገናኝ የማይችል፡ አውሮፓንና አሜሪካን ሳይቀር ያጥለቀለቀውን ወለድ አልባ ባንክ መስርቼ ዕምነቴም ይርጋልኝ፤ ሃገሬም ትልማልኝ ብል ያለ አንዲት የይስሙላ እንኳን ምላሽ በደፈናው “አይሆንም” ተባልኩኝ፡፡ ለምን አላልኩም፡፡ ምክኒያቱም የማለት መብት የለኝም፡፡ የሐገሬ ፌዴራሎች እና ወታደሮች በየመንገዱ ሳያቸው እኔን ሊጠብቁ ሳይሆን እኔን ሊጠባበቁና ሊያስፈራሩ እንደቆሙ ስለማውቅ ቢያንስ እንደ ወገን ይቆጥራቸው የነበረው ማንነቴ አሁን የለም፡፡ እኚያ ወታደሮችሽ ትላንት አባት፡ ወንድም፡ እህቶቼን ያለ አንዳች ጥፋት እስኪበቃቸው ቀጥቅጠዋል፤ አሁንም ከመቀጥቀጥ አልቦዘኑም፡፡ እኚያ እንደ አይኔ ብሌን የምሳሳላቸውን፡ ከሞቀ ቤታቸው ጎትቼ መርጬሃለውና መልዕክቴን ለመንግስት አድርስ ብዬ በሚሊዩን የሚቆጠር ህጋዊ ፊርማ አስጨብጬ የላኳቸውን ኮሚቴዎቼን አይሁድ እንኳን የማያደርገውን ግፍ ወታደሮችሽ ፈፀሙባቸው፡፡ በተሠባበረ ብርጭቆ ላይ እግራቸው እየደማ ነዷቸው፡፡ አልኮል ባደነዘዘው ርካሽ አንደበታቸው በዕምነታቸው ተሳለቁባቸው፡፡ የዘር ፍሬያቸው ላይ ሳይቀር ከባድ ዕቃ አንጠልጥለው አስለቀሷቸው፡፡ አንድ፡ ሁለት ብዬ መቁጠር የምችላቸው እህቶቼን፡ ሃፍረተ ገላቸውን ቀርቶ ሁለመናቸውን ከየትኛውም ወንድ ከልለው ተከብረው በኖሩበት ምድር ወንድም አባቶቻቸዉን ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ ብለው አስረው እየተፈራረቁ ደፈሯቸው፤ ተንከራተው ያፈሩትን ወርቅና ገንዘብም አይናቸው እያየ ዘረፏቸው፡፡ ይህ የተፈፀመው ጫካሽ ውስጥ እንዳይመስልሽ ሃገሬ፤ አልሙልኝ በምትዪን በመዲናሽ አዲስ አበባ አገር እያወቀ ነው፡፡ ቀና ብዬ ለማየት እንኳን የምሳቀቅላቸውን ኡለሞችና መምህሮቼን በየተገኙበት አዋረዷቸው፡፡ አስረው ገረፏቸው፤ ያለአንዳች ማስረጃና ክስ ወዳሻቸው እስር ቤት አጋዟቸው፡፡ ታዲያ ለየትኛው ኑሮዬ መሻሻል ብዬ ስለ አባይ ላስብ? በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ይብስ ብለው እኚህ ውሾችሽ መስጊዶችን ቀረጥ እንዳልከፈለ የንግድ ሱቅ “ታሽጓል” ብለው ፅፈው ከርችመው እፀልያለሁ ብሎ የመጣን አማኝ ይናከሱ ጀምረዋል፡፡ ኸረ ስንቱን በደልና ግፍ ዘርዝሬ እችለዋለሁ?!

ታዲያ ከነዚህ በላይ በዚች ምድር ላይ ጠላት ባይኖረኝ ይገርማልን? ከነዚህ አውሬዎች ጎን ተሠልፌ እና በነርሱ እየታዘዝኩ በስመ “የሐገር ጉዳይ” እራሴን ለመሰዋት ባልስማማ ትታዘቢኝ ይሆን? ይህን ሁሉ ችዬ ከሐገር አይበልጥም ብዬ ለውጊያ ብሰናዳስ ዛሬ በስም ጭምር እየጠቀስኩ እነ እገሌ እና እገሊት ለፓርቲህ ታማኝ ቢሆኑም ለኔና ለሐገሬ ግን ታማኝ አይደሉምና ለፍርድ ይቅረቡልኝ፤ የዳኞቹ አለቃ እራሱ ዳኝነት አስፈልጎታል፤ ስል ሌላው ቀርቶ እንደዜጋ ክስ የመመስረት መብት እንኳን መነፈጌ መች ተዘነጋ? እርሜን አደባባይ ወጥቼ ተው ስማኝ ብዬ ብለምነው መንግስትሽ መልስ ለመስጠት እንኳን እጅግ ንቆኝ “በሲጋራ አፉ” ያላገጠብኝ ሳይረሳ ነገ ከተሠዋሁለት ግድብ ቤሳቤስቲን አይደርስህም ብሎ በለመደው ሠፊ እጁ እየዘገነ “ምን ታፈጣለህ?” ቢለኝ የማን ያለህ ልል ነው? አሁን ኢኮኖሚያችን ስላደገ ደሞዝ ይጨመርልኝ፤ ታክስ ይቀነስልኝ ወዘተርፈ ጥያቄ ባነሳ እንደዛሬው አሸባሪ ብሎ ቃሊቲ እና ማዕከላዊ እንደማይልከኝ በዚህ አጣብቂኝ ጊዜ ውስጥ ሆኖ እንኳን መች ፍንጭ ሠጠኝ? ታዲያ የትኛውን ጥያቄ ሠሚ መንግስት አምኜ ልዋደቅልሽ? እመኚኝ ሐገሬ ይህ ባንዳነት አይደለም፡፡ ላንቺው ወግኜ የኔንም ያንቺንም ትልቅ ጠላት መወገድ ከትንሹ ጠላት ቅድሚያ ለመስጠት ስል የወሰንኩት ውሳኔ ነው፡፡ በዚህ ዘመቻ ብሳተፍ የማቆየው ግድብሽን ብቻ ሳይሆን ልጆችሽን ደም እያስለቀሰ ያለውን ሠይጣንሽንም ጭምር ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንቺንም ቢሆን ይጎዳሻል እንጂ አይጠቅምሽም፡፡

ሙስሊምነት እና የህዳሴው ግድብ/ ግብፅ

ይህን ንዑስ ርዕስ መጨመር ያስፈለገኝ ከላይ የገለፅኩት አቋሜ በአንዳንድ ትንሽ ነገር ሲጠብቁ በነበሩ ወገኖች በሙስሊምነቴ የያዝኩት አቋም እንዳይመስላቸው በመስጋት ነው፡፡ ኃይማኖት ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለምን እንደሚነሳ አይገባኝም፡፡ ኢትዩጲያዊያን ሙስሊሞች እኮ የሐገሪቱ ግማሽ ነን፡፡ ይህች ሃገር ከኛ በላይ የማንም አይደለችም፡፡ የሙስሊሞችን ብሔራዊ ስሜት ጥያቄ ውስጥ መክተት በራሱ እንደ ቀደምት አፄዎች የሙስሊሞችን ኢትዮጲያዊነት ከመጠራጠር ይመነጫል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከኢትዮጲያ ጋር የተፋጠጠችው ግብፅም እኮ የሙስሊም ብቻ ሳትሆን የክርስቲያንም (ለዚያውም ከአብዛኛው ክርስቲያን ዓለም በተለየ እንደ ሐገራችን ክርስቲያኖች የኦርቶዶክስ አማኞች የበዙባት) ሐገር ናት፡፡ ከኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጋርም ልዩ ታሪካዊ ቁርኝት ያላት ሐገር ናት፡፡ ግብፆችስ ይህን ስለተረዱ አይደል በግድቡ ዙሪያ ኢትዮጲያ ላይ ጫና ለማሳደር ከኢስላም ሊቃውንት በፊት የግብፅ ኮፕቲክ ቤ/ክ ጳጳሳትን እንደዋነኛ ተደራዳሪ ያዘጋጁት? ታዲያ ሙስሊሙን ለይቶ ከግብፅ ጋር የሚያስተሳስር ምን ልዩ ነገር ይመጣል ተብሎ ተጠረጠረ? ነገሩ የሐይማኖት ቢሆንማ ሱዳን ከግብፅ ኢትዮጲያን ትመርጥ ነበርን? ስለዚህ ጉዳዬ ከኢትዮጲያዊነቴ አልያም ከዕምነቴ ጋር ሳይሆን ከጭቁን ማንነቴ ጋር ብቻ የተሳሰረ መሆኑን እና ዕምነት ከምጥልበት መንግስት ጋር ብሠለፍ በሐገሬ የመጣን ማንንም እንደማልምር ይመዝገብልኝ፡፡

ማጠቃለያ

አይበለውና የተፈራው ጦርነት በግብፅ እና በኢህአዴግ ጦር መሐል ቢቀሰቀስ የትኛውም ወገን ቢያሸንፍ ድምፁ የታፈነው ጭቁኑ ህዝብ አትራፊ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ ኢህአዴግ አሸንፎ ግድቡ ቢያልቅ እና ዛሬ ላይ ሆነን “ፍትህ አዛብተውብናል፤ ዘርፈውናልና ለፍርድ ይቅረቡ” ስንል (መምህሩ እያለ ደቀመዝሙሩን በማሰር) ካላገጡብን ለማዳ ሌቦች ተርፎ ለሐገሪቱ ጠብ የሚል ሽርፍራፊ ከተገኘ ያው መስዋዕትነት ባይገባውም ጥቅም ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ቁሳዊ ጥቅም ነው፡፡ ግብፅ አሸንፋ ግድቡንም ወያኔንም ጠራርጋ “ማንኛውንም” ሌላ መሪ ብናገኝ በእርግጠኝነት በደርግ እና በኢህአዴግም ጭምር እንደታየው መጪው መንግስት ስራውን የሚጀምረው ያለፈውን መንግስት እና ህዝቡን ያጋጩ ነጥቦችን ለይቶ በማከም ነው፡፡ የህዝቡን ልብ የሰበሩ እና ከኢህአዴግ ጋር በዋነኛነት ያቃቃሩትን ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማክበር፤ እንዲሁም በአቋማቸው ብቻ አሸባሪ የተባሉ የህሊና እስረኞችን በመፍታት፤ አለም አቀፍ ውግዘት ያስከተሉትን አፋኝ ህጎች በማስተካከል እና በተለይ የፈለግነውን ዕምነት የመከተል መብት እንደተቀረው ዓለም በማክበር ነው፡፡ በዚህም ከካድሬዎቹ ተርፎ ግድቡ ሊያስገኝልን የሚችል የነበረን ምናባዊ “ዕድገት” እና “የተሻለ ኑሮ” ብናጣም የሚገኘው ህሊናዊ እረፍት እና የመንፈስ መረጋጋት በቁስ የማይመነዘር ነው፡፡ ይህ አባባሌ በኢትዩጲያዊ የአርበኝነት ስሜትም ሆነ በ“ሐገር እና ፖለቲካ ይለያያሉ” ድፍን ያለ አስተሳሰብ ያስከፋችሁ ወገኖቼን ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ የኔ የግሌ አቋም ነው፡፡ ከተጋረጡብኝ ሁለት ግዙፍ ጠላቶች (ግብፅና ወያኔ) ቀድሞ እንቅልፍ የነሳኝ ወያኔ ቢወገድ በዘረዘርኳቸው በርካታ በደሎች ምክኒያት እመርጣለሁ፡፡ ከዚያም ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ማንነቴን ካከበረልኝ እና ስልጣኑን ከፈቀድኩለት መጪ መንግስት ጋር በመሆን በንፁህ ህሊና ወገቤን አስሬ ሐገሬን አለማለሁ፡፡ ነፃነት ከልማት ይቀድማልና!!! አበቃሁ፡፡

ድምፃችን ሳይሠማ “ዘመቻ ህዳሴ ግድብ”?

By Umer Faruq (Ethio Al-Habeshi)

ቅድመ ማሳሰቢያ፡ ይህንን ፅሁፍ እስከመጨረሻው ሳያነቡ እባክዎን አስተያየት ለመስጠት አይቸኩሉ፡፡ ትናንት በገባሁት ቃል መሠረት ፅሁፌን እነሆ ብያለሁ፤ መልካም ንባብ፡-

“ለሐገሬ ምን ሠራሁ እንጂ ሐገሬ ምን ሠራችልኝ አትበል፡፡” ይላል ዕውቁ የነፃነት ታጋይ እና 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብረሃም ሊንከን፡፡ ይህን አባባል በጥልቅ የተረዱት አሜሪካውያን እንደተባለው ለሐገራቸው መስራትን አስቀደሙ፡፡ ሐገራቸውም እንደ ሐገር ጥቁር ነጭ እያለች የበደል ፅዋ ታፈራርቅባቸው የነበረውን ጎጂ ብሒሏን እርግፍ አድርጋ በመተው ልጆቿን አንዱን ካንዱ ሳትለይ አቀፈች፡፡ ጥቁር የበታች ነው፤ ይህ ጥቁሮች የማይማሩበት ት/ቤት ነው፤ እና የመሳሰሉ በርካታ በድብቅ ሳይሆን በገሃድ ትተገብራቸው የነበሩትን እኩይ ተግባራት፡ ተይ አይበጅሽም ሲሏት ከመሪር ትግል በኋላም ቢሆን ለዕድገቷ በማሠብ እንደ “አንዳንዶቹ” ተሳስተሻል አትበሉኝ ብላ እልህ ውስጥ ሳትገባ ስህተቷን አረመች፡፡ ሐገር እና ህዝብ ተጋግዘውም ከነበሩበት የበታችነት አዘቅት ውስጥ ወጥተው በነፃነት እና ኃያልነት ማማ ላይ ሲፈናጠጡ “ያልነቃው” የዓለም ክፍል እርስ በርሱ እየተናከሰ አጀባቸው፡፡ እንደ አትሌት ኃይሌ በዓይናቸው በብረቱ እየተመለከቱ አሜሪካ በጣጥሳቸው ወደፊት ገሠገሠች፡፡ ይህ ነው የህዝብ ሉአላዊነት ውጤት፡፡ አንባገነንነትን የፊጥኝ ያሉቱ እነ ሶቪየት ህብረት፡ የተመኩበት ኃይል ከመፈረካከስ አላዳናቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የኛው ሶሻሊስት አንባገነን መንግስቱ ኃ/ማሪያም ከአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው ጦር ቢያዘጋጅም ህዝብ እንጂ መሳሪያ ለጭንቅ ቀን አይሆንምና እያጨበጨበ ቀኑን ሲቆጥርለት የነበረው የገዛ ህዝቡ ምንነታቸውን ከማያውቃቸው ሽርጥ ለባሽ ጎፈሬ ታጋዩች ጋር ሆኖ ገረሠሠው፡፡ መንግስቱ ኃ/ማሪያም ላይ በዋነኛነት የህዝቡን ጥርስ ያስነከሰበት ምግባሩ ልማት ማጓደሉ ነበርን? ትምህርትን አለማስፋፋቱና መሐይምነትን አለማጥፋቱ ነበርን? በፍፁም!

ደርግን የተኩት ባለተራዎች በልማት ብቻ የህዝብ ልብ እንደሚገኝ በማሠብ ሌላ ነገር አትጠይቁን አሉ፡፡ ግንብ እና አስፋልት ላይ እኮ የሚንፈላሠሠው ስጋዬ ነው፡፡ ስጋዬ ውስጥ ደግሞ በነፃነት መኖርን ከምንም በላይ የሚሻ ህሊናና ሠብአዊ ማንነት አለኝ፡፡ የስጋዬ ደስታም ሆነ ሐዘን የሚገለፀው በዚያ መታፈንን በማይሻው ሠብአዊ ማንነቴ ውስጥ ነው፡፡ እንደውሻ አንገቴን አስረው መሮጥ ሲያምረኝ እያጠበቁ የምሮጠው እነርሱ ሲፈቅዱ እንጂ እኔ ሲያሻኝ እንዳልሆነ እያሳዩኝ በሚያምር አስፋልት ላይ ቢነዱኝ እና ጣፋጭ አጥንት ቢያስግጡኝ አንጀቴ ውስጥ ጠብ ሊል ይችላልን? ስለ ሠብዓዊ መብቴ መከበር ስጠይቅ “ግንብ እና አስፋልት ሠርተንልሃል” ብለው መመለሳቸው በራሱ ለኔ “ግንብ ውስጥ ከኖርክ ምን አነሰህ?” አይነት የንቀት ንቀት ነው፡፡ መናገር የፈለግኩትን ተናግሬ፤ ስጠይቅ ተሠምቼ፤ ስመርጥ ድምፄ ተከብሮ ቆሎ ቆርጥሜ፡ የሳር ቤት ውስጥ ያለፍርሃት እና ያለሠቀቀን መኖር ካሁን አሁን መጥተው በተቃዋሚነቴ / በሙስሊምነቴ አሠሩኝ፤ ገደሉኝ፤ ልጄን፡ ወንድሜን፡ እህቴን አልያም አባቴን ያለማንም ሃይ ባይ ጎትተው ወሠዱብኝ እያልኩ እየተሳቀቅኩ ቪላ ቤት ውስጥ ከመኖር (ያውም እድሉ ካለኝ) ሺህ ጊዜ ይበልጥብኛል፡፡ ኢህአዴግ ከደርግ እና ዓለም ካወቀቻቸው በርካታ አንባገነን መንግስታት ፍፃሜ ትምህርት ሊቀስም በፍፁም አልቻለም፡፡ ርዕሴን አልዘነጋሁም፤ በጥሞና ይከተሉኝ፡፡

በ “ዘመቻ ህዳሴ ግድብ” የመሳተፍ እና ያለመሳተፍ ጉዳይ የሐገር ጉዳይ ብቻ ነውን?

መግቢያዬ ላይ በጠቀስኩት ታሪካዊ ጥቅስ፡ አብረሃም ሊንከን “ሀገሬ ምን ሠራችልኝ አትበል” ሲል አንተ ያቅምህን ለሐገርህ ስትታገል የልብህን ለማድረስ ሃገርህ እጇ ቢያጥር አትውቀሳት ለማለት እንጂ አንተ ደፋ ቀና ስትልላት “የአይንህ ቀለም አላማረኝም” ብላ ብታስርህ እና ብትገርፍህ አሜን ብለህ ተቀጥቀጥ ለማለት እንዳልሆነ የሚያግባባን ይመስለኛል፤ እርሱም በጥቁርነቱ ሲጨቆን ያንን አላደረገምና፡፡ በዚህ አግባብ በአሁኑ ሠዓት እኔ ለሐገሬ የማበረክተውን እና ሐገሬ ለሠራሁት ሥራ ተገቢውን ክፍያ ያልከፈለችኝ “እጅ አጥሯት” ነው ብዬ በአብረሃም ሊንከንኛ ባቀነቅንም፡ መብቴን ባልኩ የተቀጠቀጥኩበት እና የገርባ እና የአሳሳ ወንድም እህቶቼ እንደሌላው ኢትዩጲያዊ ወገናቸው የተገደሉበት ማናለብኝነት እና ትምክህት ለአብረሃም ሊንከን ቢደርስ ቢያንስ ለዛሬዋ ሐገሬ (መንግስቴ) ባለዕዳ እንደማያደርገኝ አምናለሁ፡፡  ወዴት እያመራሁ እንደሆነ የተገነዘባችሁ ይመስለኛል፡፡ ኦዎን! በአሁኑ ሠዓት ሐገሬ ኢትዩጲያ “ህዳሴዋን” እንዳታበስር ጠላት ተሠድሮባታል፡፡ ክፉውን ያርቀውና አካባቢው ጦርነት ጦርነት መሽተት ጀምሯል፡፡ በሀገሬ ጥቅም የመጣ ማንኛውም (ማንኛውም ይሰመርበት) ጠላት ያው ጠላት ነው፡፡

በዚህ አቋማችን ባንለያይም ይህን ጠላት ለመፋለም የኢህአዴጓ ሐገሬ “በክፉ ቀኔ” ሳትደርስልኝ በክፉ ቀኗ ብትጠራኝ የሚኖረኝ ምላሽ ምክኒያቴን ላላገናዘበ ማንኛውም አንባቢ ላይዋጥለት ይችላል፡፡ በርግጥም ሐገሬ እንደስከዛሬው በኢህአዴግ እየተመራች ከየትኛውም ጠላት ጋር ለፍልሚያ ብትጠራኝ አልሰማትም፡፡ ይህን የምለው ፖለቲካን ከሐገር መለየት ተስኖኝ አልያም ሐገሬን ኢትዩጲያን ከማንም ያነሠ አፍቅሬ እንዳይመስላችሁ፡፡ እንዲያውም ጥሎብኝ ከልጅነቴ ጀምሮ የሐገሬ ነገር አይሆንልኝም፡፡ በኢትዩ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ዕድሜዬ ለአቅመ ጦርነት ባይደርስም ከተዋጉት ባልተናነሰ ትንፋሼ ቁርጥ እስኪል ሁለመናዬ አይንና ጆሮ ሆኖ የሐገሬን ድል በጉጉት የተጠባበቀው ማንነቴ አሁንም አለ፡፡ ኢትዩጲያዬ ላይ እንኳን ሠይፍ የመዘዘባትን ቀርቶ በሠላማዊው የእግር ኳስ ሜዳ የተገዳደራትን እንኳን በዙሪያዬ ኳሱን ከሚከታተለው ህዝብ በተለየ ብርድ እንደመታው ጥርሴ እየተንገጫገጨ ከውስጥ በሚንተገተግ የሐገር ፍቅር ስሜት ድሏን በጭንቀት እጠባበቅ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ከሐገሬ ውጪ እንደሌላው ለ አርሴና ማንቼ የማውሰው አይንም የኳስ ፍቅርም አልነበረኝም፡፡ ይህ የሐገር ፍቅር ከደም የተቀላቀለ የማንነት መገለጫ እንጂ ሲፈልጉ የሚገዙት ሲፈልጉ የሚሸጡት ሸቀጥ አይደለም፡፡ ዛሬም ወደፊትም ይኖራል፡፡ እንዲህ የሆንኩላት ሐገሬ ግን ሳትፈልግ መሪዋን በጨበጡ ሽፍቶች አገለለችኝ፡፡ እንኳን በአደባባይ፡ ሻሂ ቤት ቁጭ ብዬ ለምተነፍሳት ቃል ሁለት ጊዜ እንዳስብ አስገድዳ ያለጥፋቴ ስትፈልግ የምትገርፈኝ ስትፈልግ የምትዘርፈኝ ባሪያዋ አደረገችኝ፡፡ መብት የሚባል ነገር በፍፁም እንዳልጠይቅ ፤ አንገቴን ደፍቼ እንድገዛ ፈረደችብኝ፡፡ መንግስቴ የገዛ የሐይማኖት መሪዬን እራሴው ልምረጥ የሚለውን ሊያሳስር እና ሊያስገድል ቀርቶ ሊያስገለምጥ የማይገባውን ህገመንግስታዊ እና ሠብዓዊ መብቴ የሆነውን ጥያቄዬን ሳይቀበል ዛሬ አንተን ሲቀጠቅጡ የነበሩትን “ቀይ ለባሽ” ውሾቼን ሊመታብኝ የመጣ አካል አለና፡ ና ተከላከልልኝ ቢሎ ባንቺ ስም ቢጠራኝ  እና ባልሠማው ሐገሬም አትታዘቢኝም፡፡

ሐገሬ የዘንድሮ በደልሽ መች ተቆጥሮ ያልቅና? ሌላው ቀርቶ ከምንም ነገር ጋር ሊገናኝ የማይችል፡ አውሮፓንና አሜሪካን ሳይቀር ያጥለቀለቀውን ወለድ አልባ ባንክ መስርቼ ዕምነቴም ይርጋልኝ፤ ሃገሬም ትልማልኝ ብል ያለ አንዲት የይስሙላ እንኳን ምላሽ በደፈናው “አይሆንም” ተባልኩኝ፡፡ ለምን አላልኩም፡፡ ምክኒያቱም የማለት መብት የለኝም፡፡ የሐገሬ ፌዴራሎች እና ወታደሮች በየመንገዱ ሳያቸው እኔን ሊጠብቁ ሳይሆን እኔን ሊጠባበቁና ሊያስፈራሩ እንደቆሙ ስለማውቅ ቢያንስ እንደ ወገን ይቆጥራቸው የነበረው ማንነቴ አሁን የለም፡፡ እኚያ ወታደሮችሽ ትላንት አባት፡ ወንድም፡ እህቶቼን ያለ አንዳች ጥፋት እስኪበቃቸው ቀጥቅጠዋል፤ አሁንም ከመቀጥቀጥ አልቦዘኑም፡፡ እኚያ እንደ አይኔ ብሌን የምሳሳላቸውን፡ ከሞቀ ቤታቸው ጎትቼ መርጬሃለውና መልዕክቴን ለመንግስት አድርስ ብዬ በሚሊዩን የሚቆጠር ህጋዊ ፊርማ አስጨብጬ የላኳቸውን ኮሚቴዎቼን አይሁድ እንኳን የማያደርገውን ግፍ ወታደሮችሽ ፈፀሙባቸው፡፡ በተሠባበረ ብርጭቆ ላይ እግራቸው እየደማ ነዷቸው፡፡ አልኮል ባደነዘዘው ርካሽ አንደበታቸው በዕምነታቸው ተሳለቁባቸው፡፡ የዘር ፍሬያቸው ላይ ሳይቀር ከባድ ዕቃ አንጠልጥለው አስለቀሷቸው፡፡ አንድ፡ ሁለት ብዬ መቁጠር የምችላቸው እህቶቼን፡ ሃፍረተ ገላቸውን ቀርቶ ሁለመናቸውን ከየትኛውም ወንድ ከልለው ተከብረው በኖሩበት ምድር ወንድም አባቶቻቸዉን ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ ብለው አስረው እየተፈራረቁ ደፈሯቸው፤ ተንከራተው ያፈሩትን ወርቅና ገንዘብም አይናቸው እያየ ዘረፏቸው፡፡ ይህ የተፈፀመው ጫካሽ ውስጥ እንዳይመስልሽ ሃገሬ፤ አልሙልኝ በምትዪን በመዲናሽ አዲስ አበባ አገር እያወቀ ነው፡፡ ቀና ብዬ ለማየት እንኳን የምሳቀቅላቸውን ኡለሞችና መምህሮቼን በየተገኙበት አዋረዷቸው፡፡ አስረው ገረፏቸው፤ ያለአንዳች ማስረጃና ክስ ወዳሻቸው እስር ቤት አጋዟቸው፡፡ ታዲያ ለየትኛው ኑሮዬ መሻሻል ብዬ ስለ አባይ ላስብ? በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ይብስ ብለው እኚህ ውሾችሽ መስጊዶችን ቀረጥ እንዳልከፈለ የንግድ ሱቅ “ታሽጓል” ብለው ፅፈው ከርችመው እፀልያለሁ ብሎ የመጣን አማኝ ይናከሱ ጀምረዋል፡፡ ኸረ ስንቱን በደልና ግፍ ዘርዝሬ እችለዋለሁ?!

ታዲያ ከነዚህ በላይ በዚች ምድር ላይ ጠላት ባይኖረኝ ይገርማልን? ከነዚህ አውሬዎች ጎን ተሠልፌ እና በነርሱ እየታዘዝኩ በስመ “የሐገር ጉዳይ” እራሴን ለመሰዋት ባልስማማ ትታዘቢኝ ይሆን? ይህን ሁሉ ችዬ ከሐገር አይበልጥም ብዬ ለውጊያ ብሰናዳስ ዛሬ በስም ጭምር እየጠቀስኩ እነ እገሌ እና እገሊት ለፓርቲህ ታማኝ ቢሆኑም ለኔና ለሐገሬ ግን ታማኝ አይደሉምና ለፍርድ ይቅረቡልኝ፤ የዳኞቹ አለቃ እራሱ ዳኝነት አስፈልጎታል፤ ስል ሌላው ቀርቶ እንደዜጋ ክስ የመመስረት መብት እንኳን መነፈጌ መች ተዘነጋ? እርሜን አደባባይ ወጥቼ ተው ስማኝ ብዬ ብለምነው መንግስትሽ መልስ ለመስጠት እንኳን እጅግ ንቆኝ “በሲጋራ አፉ” ያላገጠብኝ ሳይረሳ ነገ ከተሠዋሁለት ግድብ ቤሳቤስቲን አይደርስህም ብሎ በለመደው ሠፊ እጁ እየዘገነ “ምን ታፈጣለህ?” ቢለኝ የማን ያለህ ልል ነው? አሁን ኢኮኖሚያችን ስላደገ ደሞዝ ይጨመርልኝ፤ ታክስ ይቀነስልኝ ወዘተርፈ ጥያቄ ባነሳ እንደዛሬው አሸባሪ ብሎ ቃሊቲ እና ማዕከላዊ እንደማይልከኝ በዚህ አጣብቂኝ ጊዜ ውስጥ ሆኖ እንኳን መች ፍንጭ ሠጠኝ? ታዲያ የትኛውን ጥያቄ ሠሚ መንግስት አምኜ ልዋደቅልሽ? እመኚኝ ሐገሬ ይህ ባንዳነት አይደለም፡፡ ላንቺው ወግኜ የኔንም ያንቺንም ትልቅ ጠላት መወገድ ከትንሹ ጠላት ቅድሚያ ለመስጠት ስል የወሰንኩት ውሳኔ ነው፡፡ በዚህ ዘመቻ ብሳተፍ የማቆየው ግድብሽን ብቻ ሳይሆን ልጆችሽን ደም እያስለቀሰ ያለውን ሠይጣንሽንም ጭምር ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንቺንም ቢሆን ይጎዳሻል እንጂ አይጠቅምሽም፡፡

ሙስሊምነት እና የህዳሴው ግድብ/ ግብፅ

ይህን ንዑስ ርዕስ መጨመር ያስፈለገኝ ከላይ የገለፅኩት አቋሜ በአንዳንድ ትንሽ ነገር ሲጠብቁ በነበሩ ወገኖች በሙስሊምነቴ የያዝኩት አቋም እንዳይመስላቸው በመስጋት ነው፡፡ ኃይማኖት ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለምን እንደሚነሳ አይገባኝም፡፡ ኢትዩጲያዊያን ሙስሊሞች እኮ የሐገሪቱ ግማሽ ነን፡፡ ይህች ሃገር ከኛ በላይ የማንም አይደለችም፡፡ የሙስሊሞችን ብሔራዊ ስሜት ጥያቄ ውስጥ መክተት በራሱ እንደ ቀደምት አፄዎች የሙስሊሞችን ኢትዮጲያዊነት ከመጠራጠር ይመነጫል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከኢትዮጲያ ጋር የተፋጠጠችው ግብፅም እኮ የሙስሊም ብቻ ሳትሆን የክርስቲያንም (ለዚያውም ከአብዛኛው ክርስቲያን ዓለም በተለየ እንደ ሐገራችን ክርስቲያኖች የኦርቶዶክስ አማኞች የበዙባት) ሐገር ናት፡፡ ከኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ጋርም ልዩ ታሪካዊ ቁርኝት ያላት ሐገር ናት፡፡ ግብፆችስ ይህን ስለተረዱ አይደል በግድቡ ዙሪያ ኢትዮጲያ ላይ ጫና ለማሳደር ከኢስላም ሊቃውንት በፊት የግብፅ ኮፕቲክ ቤ/ክ ጳጳሳትን እንደዋነኛ ተደራዳሪ ያዘጋጁት? ታዲያ ሙስሊሙን ለይቶ ከግብፅ ጋር የሚያስተሳስር ምን ልዩ ነገር ይመጣል ተብሎ ተጠረጠረ? ነገሩ የሐይማኖት ቢሆንማ ሱዳን ከግብፅ ኢትዮጲያን ትመርጥ ነበርን? ስለዚህ ጉዳዬ ከኢትዮጲያዊነቴ አልያም ከዕምነቴ ጋር ሳይሆን ከጭቁን ማንነቴ ጋር ብቻ የተሳሰረ መሆኑን እና ዕምነት ከምጥልበት መንግስት ጋር ብሠለፍ በሐገሬ የመጣን ማንንም እንደማልምር ይመዝገብልኝ፡፡

ማጠቃለያ

አይበለውና የተፈራው ጦርነት በግብፅ እና በኢህአዴግ ጦር መሐል ቢቀሰቀስ የትኛውም ወገን ቢያሸንፍ ድምፁ የታፈነው ጭቁኑ ህዝብ አትራፊ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ ኢህአዴግ አሸንፎ ግድቡ ቢያልቅ እና ዛሬ ላይ ሆነን “ፍትህ አዛብተውብናል፤ ዘርፈውናልና ለፍርድ ይቅረቡ” ስንል (መምህሩ እያለ ደቀመዝሙሩን በማሰር) ካላገጡብን ለማዳ ሌቦች ተርፎ ለሐገሪቱ ጠብ የሚል ሽርፍራፊ ከተገኘ ያው መስዋዕትነት ባይገባውም ጥቅም ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ቁሳዊ ጥቅም ነው፡፡ ግብፅ አሸንፋ ግድቡንም ወያኔንም ጠራርጋ “ማንኛውንም” ሌላ መሪ ብናገኝ በእርግጠኝነት በደርግ እና በኢህአዴግም ጭምር እንደታየው መጪው መንግስት ስራውን የሚጀምረው ያለፈውን መንግስት እና ህዝቡን ያጋጩ ነጥቦችን ለይቶ በማከም ነው፡፡ የህዝቡን ልብ የሰበሩ እና ከኢህአዴግ ጋር በዋነኛነት ያቃቃሩትን ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማክበር፤ እንዲሁም በአቋማቸው ብቻ አሸባሪ የተባሉ የህሊና እስረኞችን በመፍታት፤ አለም አቀፍ ውግዘት ያስከተሉትን አፋኝ ህጎች በማስተካከል እና በተለይ የፈለግነውን ዕምነት የመከተል መብት እንደተቀረው ዓለም በማክበር ነው፡፡ በዚህም ከካድሬዎቹ ተርፎ ግድቡ ሊያስገኝልን የሚችል የነበረን ምናባዊ “ዕድገት” እና “የተሻለ ኑሮ” ብናጣም የሚገኘው ህሊናዊ እረፍት እና የመንፈስ መረጋጋት በቁስ የማይመነዘር ነው፡፡ ይህ አባባሌ በኢትዩጲያዊ የአርበኝነት ስሜትም ሆነ በ“ሐገር እና ፖለቲካ ይለያያሉ” ድፍን ያለ አስተሳሰብ ያስከፋችሁ ወገኖቼን ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ የኔ የግሌ አቋም ነው፡፡ ከተጋረጡብኝ ሁለት ግዙፍ ጠላቶች (ግብፅና ወያኔ) ቀድሞ እንቅልፍ የነሳኝ ወያኔ ቢወገድ በዘረዘርኳቸው በርካታ በደሎች ምክኒያት እመርጣለሁ፡፡ ከዚያም ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ማንነቴን ካከበረልኝ እና ስልጣኑን ከፈቀድኩለት መጪ መንግስት ጋር በመሆን በንፁህ ህሊና ወገቤን አስሬ ሐገሬን አለማለሁ፡፡ ነፃነት ከልማት ይቀድማልና!!! አበቃሁ፡፡” src=”

Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles