Quantcast
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ነፃነት አምባገነንና ጨቋኝ መሪዎች

ሰዎችን እንደፈለጉ በመግዛት የነሱ አገልጋይ ለማድረግ በመጀመሪያ ሰዎች በራሳቸው ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያጡ በማድረግ፡ስሜታቸውን በመጉዳት፡መንፈሳቸውን በመግደል ይጀምራሉ፡፡ስሜታቸውን እና መንፈሳቸውን ከተቆጣጠሩ አካልን መግዛት እጅግ ቀላል ነውና…፡አካል የሚሰራው ሰሜት ሲኖር፡መንፈስ ሲጠነክር ነው፡፡ስሜቱና መንፈሱ የሞተ የሌሎች ባሪያ ነው፡፡ባሪያ ደግሞ በአሳዳሪዎቹ አንደ ዕቃ ነው የሚቆጠረው፡፡

Image may be NSFW.
Clik here to view.

እቃን ማሰተዳደር ደግሞ እጅገ ቀላል ነው፡፡አህጉራችን አፍሪካም የዚህ የሰነ-ልቦና ጦርነት ምርኮኛ ካደረጓት በኃላ ነበር እንደ አንባሻ ቆራርጠው ተፈጥሯዊ ሀብቷን የመዘበሩት፡ ህዝቦቿን በባሪያ ንግድ እንደ ሸቀጥ የተቸበቸቡት፡፡ህዝቦች ለራሳቸው ዋጋ መስጠት ሲያቆሙ፡አልችልም በሚል ወረርሽኝ ሲመቱ፡ተፈጥሯዊው ክብራቸውን አጥተው አንገት ሲደፋ ባሪያ ከመሆን ውጪ አማራጭ የላቸውም፡፡ለዛም ነው አምባገነኖች ፡ ውስጣቸው በክብር የተሞላ፡መንፈሳቸው ጠንካራ ፡”ለምን ?” “አይሆንም?”የሚል ጥያቄ የሚያነሱ፡ ለራሳቸው ክብር የሰጡ ግለሰቦች ሁሌም የለውጥ ሀይል እንደሆኑ በመገንዘብ፡እነዚህ ሰዎች እሰካሉ ያሰብነው አይሳካም በሚል መራራውን የጭካኔ በትራቸውን በማሳረፍ፡አካለቸውን በማንገላታት እራሳቸውን ዝቅ አድርገው እንዲኖሩ ለማሰገደድ የሚጥሩት፡፡
ከአህጉራችን አፍሪካ በግፍ በባርነት ወደ አሜሪካ
የወሰዷቸውን ሰዎች ፈተና ይፈትኗቸው ነበር፡፡ፈተናው ከባሪያዎቹ ውስጥ ማነው ለራሱ ክብርና ዋጋ የሚሰጥ ? ማን ነው “ለምን ? አይሆንም ?” የሚለውን ለመለየት ነበር የሚሰጠው፡፡እናም “ለምን ? አይሆንም ?” ያለ፡ለራሱ ክብርና ዋጋ በመስጠት እኔ ባሪያ አይደለሁም ሲል የሞገተ ኤዲ የሚባል ገራፊ ጋር ይወስዱትና አስቃቂ ግርፊያ ይፈፀምበት ነበር፡፡ ታዲያ ይህንን ፈተና ተፈትኖ እምቢተኛ ነው ተብሎ የታመነበት ፍሬድሪክ ዳግላስ የተባለ “ባሪያ” ወደ ኤዲ ወስደውት ለሰድስት ወር ቀን በቀን እንዲገረፍ አደረጉ፡፡ፍሬድሪክ ግን ውሰጡ ጠንካራ፡ለራሱ ክብርና ትልቅ ግምት የሚሰጥ በመሆኑ ግራፋቱ መንፈሱን ሊገድለው፡ክብሩን ሊገፈው አልቻለም፡፡እንደውም አንድ ቀን የማይደረገውን አደረገ፡፡ ኤዲ ሊገርፈው ሲገባ ተነሰቶ ተናነቀው፡ታገለው፡በመጨረሻም ክፉኛ ጉዳት አደረሰበት፡፡በወቅቱ ባሪያ አሳደሪውን ለመጉዳት ካሰበ ቅጣቱ ስቅላት ነው ፡፡ግና ፍሪድሪክ “በክብር መኖር ካልቻልክ በክብር የምትሞትበት ጊዜ ደርሷል “ የሚለውን መርህ በሚገባ ስለተረዳ የሚደርስበት ጉዳት አላሳሰበውም፡፡አሳዳሪዎቹ በካቴና ጠፍረውት እየጎተቱ ሲወስዱት ድምፁን ከፍ አድርጎ “ ዛሬ ክብሬንና ነጻነቴን አግኝቻለሁ፡፡ይህንን ማንም ሊነጥቀኝ አይችልም እራሴ
አሳልፌ ካልሰጠሁ በስተቀር፡፡ዛሬ የክብርንና የነፃነት ፅዋ ተጎንጭቻለሁ፡እንዴት ይጣፍጣል መስላችሁ”አለ፡፡ ዛሬም ይኸው ሙስሊሞች ነፃነታቸውንና ክብራቸው አጥተው “ባሪያ “ሁነው አንዲያድሩ ጦርነቱ ታውጃል፡፡የሀገሬም አምባገነኖች ይህን አዋጅ ሰምተው በዜጎቻቸው ላይ ጦርነቱን ከፍተዋል፡፡”ለምን ?እንዴት ? አይሆንም ?”የሚሉትን ለራሳቸው ክብር የሰጡትን በየእስር ቤቱ አጉረው መንፈሳቸውን ሊገድሉ ክብራቸውን ሊገፋ፡አንገታቸው ሊያሰደፋ ከዛም ብዙሀኑን “ባሪያ” አድርገው ሊገዙ ከንቱ ልፋት እየለፉነው፡፡ውድ ኮሚቴዎቻችን በመንፈሳዊ ጥንካሬ የተሞሉ፡ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ለራሳቸው ቦታና ክብር የሰጡ በመሆናቸው፡እነሱ ላይ በመጀመሪያ ፕሮፓጋንዳ፡ከዛም ዘለፋና ማሰፈራሪያ፡ይህ አልሳካ ሲላቸውም ለእስር ዳርገው፡ እጅግ አሰቃቂ ድብደባና ስቃይ፡የክብር ማዋረድና ዘለፋ አሳረፉባቸው፡፡በኮሚቴዎቻችንም ሳያበቃ ስለ ነፃነታቸን እና ስብዐዊ ክብራችን እንሟገታለን ያሉት ላይ ይህን በትራቸው አሳርፈዋል፡፡አልተሳካላቸውም እንጂ ፡፡አዎ እነዚህ ጀግኖች መንፈሳዊውን ትግል በድል ተወጥተውታል፡፡ ታስረው ነፃ ናቸው፡፡ አሁንም ይህ ዘመቻ አላቆመም በየጁመዐው ስለ ነፃነታቸው የሚጮሁት ላይ በትሩ አያረፈ ነው፡፡ፕሮፓጋንዳው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ይቀጥላልም፡፡በዚህ ትግል አሸናፊ ለመሆን ለራሳችን የምሰጠውን ግምት ና ክብር ማሳደግ ተገቢ ነው፡፡ አካላችንን እንጂ መንፈሳችን ሊጎዱት አይችልም፡፡ ክብራችንና ነፃነታችን ያለው በእጃችን ነው፡፡ነፃ ነን ብለን ካሰብን ምንም “ባሪያ” አያደርገንም፡፡ግና “ለምን ? አንዴት ? አይሆንም ? ”ማለት ስናቆም ፡ዱላውና እስራቱ በዛብኝ አሁንስ “አልችልም በቃኝ “ሰንል ያኔ “ባሪያ” አንሆናል፡፡ያኔ መንፈሳችንን ያሸንፉታል፡ስሜታችን ይገዙታል ክብራችንን ይቆጣጠሩታል፡፡ከዛ በኃላ አካላችን
ነፃ ቢሆንም እኛ ግን ————–


Image may be NSFW.
Clik here to view.
Image may be NSFW.
Clik here to view.

Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>