Quantcast
Channel: Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

ኢትዮጵያ በቀረርቶ ተደናግጣ ለሰከንድ የግድብ ግንባታዋን አታቆምም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

$
0
0

969694_588045714550673_1440883208_n

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ የግብፅ አንዳንድ ባለስልጣናት ፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የተለያዩ ማህበራት ሀላፊዎች ሲያካሂዱ የከረሙትን አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ በተመከለተ ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል ….

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ያላትን ገንቢ አቋም ገልፃ ነገር ግን በግብፅ በኩል የአገሪቱን አቋም በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደርን ከአንዴም ሁለት ጊዜ ጠርታ መጠየቋንና ለግብፅ መንግስት ጥያቄ ማቅረቧን ያስታውሳል ።

ኢትዮጵያ ከምንም በላይ ለትብብር ፣ ለወዳጅነትና ለጋራ ጥቅም ያላትንም ፅኑ እምነት በወቅቱ ግልፅ አድርጋለች ያለው መግለጫው ፥ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ብሄራዊ የናይል ጉባኤ በተሰኘው ስብሰባ ላይ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ሚኒስትሮችና ሌሎችም በተገኙበት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስመልክቶ አፍራሽ መልዕክቶች ሲተላለፉ መቆየታቸውን አንስቷል ።

የህዳሴ ግድብ በግብፅ ላይ አደጋ በመደቀኑ በኢትዮጵያ ላይ በተለያዩ መንገዶች ተፅእኖ የማሳረፍና የግድቡን ግንባታ እንድታቆም የማድረግ እንቅስቃሴ ስለ ማድረግ የሚገልፁ ፣ በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ፍላጎትና አድራጎት ውጪ እንዲሁም የህዳሴ ግድቡን እንዲያጠና ግብፅ ጭምር ያለችበት የዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያቀረበውን ሪፖርት ጭምር የሚያጣጥሉ ፀብ ጫሪ አስተያየቶች በመድረኩ ሲስተናገዱ መስተዋላቸውን ነው መግለጫው የጠቆመው ።

በዚህ ረገድ በግብፅም ሆነ በሌላ ማንኛውም ወገን የሚቀርብ የግድቡን ግንባታ የማዘግየት ወይም ከነአካቴው የማቋረጥ ነገር ፈፅሞ ተቀባይነት እንደማይኖረው ገልጿል ።

በህዳሴው ግድብ ሽፋን የውስጥ ችግርን ለማቃለል የሚደረገው ጥረት የግብፅን ዘላቂ ጥቅም አይጠብቅምም ብሏል ።

ጦርነትና ሌሎች አፍራሽ ስልቶችን ስለመጠቀም የሚቀርቡት ሀሳቦች ያረጁና ያፈጁ ፣ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ የማይሸከሙ ፣ ጤናማ ያልሆኑ አስተሳሰቦች እንደሆኑና ኢትዮጵያ በዚህ ቀረርቶ ተደናግጣ ግንባታውን ለሰኮንድም እንደማታቆም አረጋግጧል ።

የግብፅ ወገንም ከዚህ አፍራሽ ድርጊት ተቆጥቦ ለሁለቱ አገራት ግንኙነት መጠናከር የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል ።

በዚህ አጋጣሚ የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስትር የህዳሴ ግድቡን ግንባታ ጠቀሜታ አስመልክተው ያሰሙት ሀሳብ ገንቢ በመሆኑ አመስግኗል ፤ ሌሎች ከዚህ የሚቀስሙት ትምህርት እንዳለም አስታውቋል ።

በሌላ በኩል ይህ ግድብ ግብፅን ጭምር የሚጠቅም መሆኑን በማሳሰብ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር በወዳጅነትና በትብብር ለመስራት ፅኑ ፍላጎት እንዳላት ገልጿል ።

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)



Viewing all articles
Browse latest Browse all 931

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>