ኢትዮጵያ ከጎረቤት እና ከሌሎችም አገሮች ጋር በመከባበርና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ በጽናት ስታራምድ መቆየቷ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
በመሆኑም ዓባይ ግድብ ዙሪያ በግብጽ ዘንድ ሰፍኖ የቆየውን ጥርጣሬ ለማስወገድ ግድቡ ግብጽንም ሆነ ማንኛውንም የታችኛውን ተፋሰስ አገር እንዳይጎዳ የሚያረጋግጥ የግብጽ፣ የሱዳን፣ የኢትዮጵያ እና አለም አቀፍ ባለሙያዎች የሚገኙበት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋምና ሪፖርት እንዲያቀርብ ሃሳብ አቅርባ ስራው ሲሰራ የሚኒስቴሩ መግለጫ አስታውሷል፡፡
የአጣሪ ቡድኑ ስራውን ሰርቶ ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ላይ የሚፈጥረው ችግር እንደሌለ ባረጋገጠበት ማግስት አንዳንድ የግብጽ ባለስልጣናትና የፖለቲካ ድርጅቶች ተቀባይነት የሌለውና በሁለቱ አገሮች መካከል ተጀምሮ የነበረውን መልካም ግንኙነት የሚያሻክር ፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ማድረጋቸው የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስትንም ኣሳዝኗል ብሏል፡፡
ባለፉት ጥቂት ቀናት የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩ ወደተባባሰ ሁኔታ እንዳይገባ በትእግስት ለማለፍ ቢሞክርም ይህ ገንቢ ያልሆነ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አሁንም ቀጥሏል ያለው መግለጫው በመሆኑም በትላንትናው ግንቦት 27 / 2005 ዓ.ም የግብጽ አምባሳደር ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠርተው ስለዚህ ሁኔታ በአስቸኳይ የመንግስታቸውን አቋም ጠይቀው እንዲሰጡ ተነግሯቸው ምላሽ በመጠበቅ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አገራችን አሁንም ዋነኛ ትኩረቷ ድህነትን ማሸነፍ እና ለዚሁ አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር ከሩቅና ቅርብ አገሮች የወዳጅነት ግንኙነት መፍጠር በመሆኑ ከግብጽ ጋር የተጀመረውን የትብብር ግንኙነት በዚሁ መርህ መሰረት አጠናክራ መቀጠል ትሻለች፡፡
ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡ ለአገራችን እድገት መፋጠን ከሚያደርገው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ግብጽንም ጨምሮ ለሌሎች ጎረቤት አገሮች ያለውን ጠቀሜታ አሁንም በድጋሚ ማስታወስ ትፈልጋለች ማለቱን ኢሬቴድ ዘግቧል፡
Related articles
- ሰበር ዜና: በካይሮ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ (ethioandinet.wordpress.com)
- ሰበር ዜና: በካይሮ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ (addisuwond.wordpress.com)
- ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች (Ethiopian Muslims) – A Book by Ahmedin Jebel (አሕመዲን ጀበል) (ethioandinet.wordpress.com)
- መለስ ዜናዊ በአለማችን ላይ ሁለተኛው ሀብታም ጠቅላይ ሚኒስተር መሆኑን ምን ያህሎቻችን እናወቃለን? (addis12.wordpress.com)
- መለስ ዜናዊ በአለማችን ላይ ሁለተኛው ሀብታም ጠቅላይ ሚኒስተር መሆኑን ምን ያህሎቻችን እናወቃለን? (addisuwond.wordpress.com)
- የንጉሠ – ነገሥቱ ንግግር፣ የዛሬ ሃምሳ አመት (beaimero.wordpress.com)
