በአየር ሃይል አውሮፕላን ጥቃት ተሰዘነረ -አርአያ ተስፋማሪያም
ወያኔ ከትግራይ ተወላጆች ተቃዉሞ ገጠመዉ፡፡
ሰላማዊ ትግሉ ሲጠናከር ስርዓቱ ወደ አውሬነት ይቀየራል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ኣቶ ገብሩ ኣስራት የምርጫ ካርድ ተከለከሉ..!

ዓረና-መድረክ ወክለው በመቐለ ምርጫ ክልል ለፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ኣቶ ገብሩ ኣስራት የመራጭነት ካርድ ተጨርሰዋል በሚል ምክንያት ተከልክለዋል።
ይህ የሆነው እሁድ 01 / 06 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ 10 ስዓት በመቐለ ኣስራ 15 ቀበሌ እንዳባ ኣነንያ ምርጫ ጣብያ በኣካል ተገኝተው በጠየቁበት ወቅት ነው።
የምርጫ ካርድ በመቐለ ምርጫ ጣብያዎች ከሓሙስ 28 / 05 / 2007 ዓ/ም ጀምሮ ሲሆን ከዚህ ቀን በሗላ የመራጭነት ካርድ ማግኘት ኣልተቻለም።
የትግራይ ምርጫ ፅህፈት ቤት ችግሩ እንዳጋጠመ ያመነ ሲሆን ለችግሩ መፍትሄ ግን ሊያበጅ ኣልቻለው።
ይህ ችግር ያጋጠመው በየምርጫ ጣብያው “ከእቅድ በላይ በመቶዎች ካርድ በመወሰዳቸው መሆኑ” ያስረዳሉ የጣብያዎቹ ሰዎች።
ይህ የህወሓት ወጣትና ሴቶች ሊግ ኣባላት እስከ 3 የመራጭነት ካርድች በተለያዩ ቦታዎች እያውጡ መሆኑ ታውቋል።
የህወሓት መንግስት የትግራይ ሰዎች A.B.C.D ብሎ በመመደብ ካርዱ ለ A.B ቅድምያ በመስጠት እንዳስፈላጊነቱ ደግሞ C ለተሰጣቸው ሰዎች ካርዱ ይሰጣቸዋል።
D የተመደበው ዜጋ የተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት ካርድ እንዳይ ደርቸው እየተደረገ ነው።
በዚህ ለሚመርጥህ ሰው ለይተህ ካርድ በመስጠትና ለታማኝ የሊግ ኣባላት ከ3 በላይ ካርድ በማደል ከወዲሁ የምርጫው ውጤት ለመወሰን ጥረት እየተደረገ ነው ያለው።
ማንኛውም ሰው በኣቅራብያው ያለው የምርጫ ጣብያ ጠይቆ ካርድ መኖሩ ኣለመነሩ ማረጋግጥ ይችላል።
ይህ ማጭበርበርያ ዘዴ ለማውጣት የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት የትግራይ ህዝብ እንደማይመርጣቸው በማረጋገጣቸው ነው።
ኣሁንም ምርጫ ቦርድ የመራጭነት ካርድ እንዲልክና የህዝቡን ፍላጎት እንዲያከብር እንመክራለን።
ኣቶ ገብሩ ኣስርትም የመራጭነት ካርድ ሊሰጣቸው ይገባል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው..!
በ”አይ ኤስ ኤስ” (ISS) የታገቱት ሃያ አንድ የግብፅ ክርስቲያኖች በአሰቃቂ መንገድ መገደላቸው
የትናንቱ የ”አይ ኤስ ኤስ” በግብፅ ክርስቲያኖች ላይ የፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ አንፃር ምን ያመላክተናል? ትናንት የካቲት 8/2007 ዓም እኩለ ሌሊት ላይ ”ሮይተርስ” በሊብያ በ”አይ ኤስ ኤስ” (ISS) የታገቱት ሃያ አንድ የግብፅ ክርስቲያኖች በአሰቃቂ መንገድ መገደላቸውን፣የአገዳደሉንም ቪድዮ በአሸባሪው ድርጅት መለቀቁን እና የግብፅ ኮፕት ቤተ ክርስቲያንም ድርጊቱ መፈፀሙን ማረጋገጧን ጠቅሶ የዘገበው ዜና ብዙዎቻችንን አሳዝኗል..
አምባገነን ብሔር የለውም !! –አሌክስ አብርሃም
ሰሞኑን የህወሃት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመላው ኢትዮጲያ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በቅድሚያ እንኳን ለአርባኛው አመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ እላለሁ ….
በትጥቅ ትግሉም ወቅት ሆነ ከትጥቅ ትግሉ በኋላ ይህን ቀን ለማየት ሳይታደሉ ያለፉ ብዙዎች ናቸውና ምንም ይሁን ምን ለዚህ ቀን መብቃት ትልቅ ነገር እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡ ይህን ፅሁፍ የምፅፈው በተወለድኩባት ባደኩባትና አሁንም እየኖርኩባት ባለችው ኢትዮጲያ ከተመሰረተ ድፍን 40 ዓመት ያስቆጠረ ጎልማሳ የፖለቲካ ድርጅት ላይ እንደአንድ ዜጋ ያለኝን ቅሬታ ለማሳወቅ ነው ፡፡
ሰሞኑን የድርጅቱን 40ኛ ዓመት በዓል በቴሌቪዥን በሬዲዮ እንዲሁም ከመሃበራዊ ድረ ገፆች ላይ ስመለከት እንዲሁም አገሪቱ ላይ ያለውን ተጨባጭ ችግር ስታዘብ ሳልፈልገው አእምሮየ ታሪክ እየመዘዘ ይሞግተኛል ፡፡ ባጭሩ ይህ በዓል በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ምን ያህል ነው ብየ ሳስብ ከግራና ቀኝ ከህዝቡ የሚሰነዘረውን ትችት አስተያየትና ምሬት ስመለከት በዓሉን ለብቻችሁ እያከበራችሁት ነው የሚል ስጋት ፈጥሮብኛል ፡፡
ምንም እንኳን የህወሃት የትጥቅ ትግል የዛሬው የህወሃት ቀንደኛ ጠላት ሻእቢያን ጨምሮ በከፈሉት መስዋእትነት ባደረጉት ተጋድሎ አገራችንን ከደርግ አሰቃቂ አገዛዝ የታደጋት መሆኑን ሁሉም ኢትዮጲያዊ ቢያውቅም ከነፃነቱ በኋላ ግን ስርዓቱ በሚከተለው ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስመር ከፍ ያለ ቅሬታ አለው ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ህዝቡ የትም ሂዱ የት ይማረራል … መቸም ይሄ ሁሉ ህዝብ የሚማረረው የኢትዮጲያ ህዝብ ምስጋና የማያውቅ ስለሆነ አይመስለኝም ፡፡ እንደውም ከእግዜር ጀምሮ እስከአምባገነን መሪወቹ ድረስ ራቱን በልቶ ባደረ ቁጥር ከእልፍ ችግሩ ጋር ተጠቅልሎ በሚተኛባት መደብ ‹‹ተመስገን›› ብሎ የሚያድር ህዝብ እንደኢትዮጲያ ህዝብ ያለ አይመስለኝም ፡፡ ግን …… ብሶት ህወሃትን እንደወለደ ሁሉ አሁንም ተማራሪ ህዝብ እየፈለፈለ ምድሩን እየሞላው ነው ፡፡ እናንተም ለህዝብ ብሶትና ጥያቄ ጅራትና ቀንድ እየቀጠላችሁ ተናጋሪውን ሁሉ ባልሆነ መንገድ በመፈረጅ ከማሳቀቃችሁም በላይ የዝሆን ጆሮ ይስጠን እንዳላችሁ ይሄው ድፍን 40 ዓመት ፡፡
በእርግጥ በቴሌቪዥንም ሆነ በአካል ለህዝብ ንግግር ማድረግ ቀላል ነው … ከባዱ ከህዝብ ጋር መነጋገር ነው ፡፡ ይሁንና ንግግር ማድረግም ቢሆን ቀላልነቱ ለሚናገሩባት ቅፅበት እንጅ ሲቆይ ወደሰማይ እንደወረወሩት ድንጋይ ተመልሶ አናት ላይ መስፈሩ አይቀርም ፡፡አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው ፡፡ የተገባው ቃል ሁሉ ስንዝር አልተራመደም ፡፡ በርካታ የልማት ስራዎች ተሰርተዋል መንገድ የጤና እና የትምህርት ተቋማት ግንባታ ግድቦች ዩኒቨርስቲዎች እነዚህ ሁሉ እናተም በተደጋጋሚ እንዲነገርላችሁ የምትፈልጓቸው ስኬቶች ናቸው ፡፡ ይሁንና ህዝብ ያልተሟላለትን ነገር ሲናገር የተሰራለትን እንደካደ አድርጎ ማሰብ ትልቁ የአረዳድ ችግራችሁ ነው ፡፡ ሰው ኑሮ ተወደደብኝ ብሎ ሲያማርር ኑሮ የሚቃለልበት መንገድ ላይ መስራት ብቻ ነው መልሱ ሊሆን የሚችለው ! …‹‹ አይ ኑሮ ቢወደድብህም ዩኒቨርስቲ ግን ሰርተንልሃል›› የሚል ምላሽ መቸም ህዝብን ሊያረካ አይችልም !! አሁን እየሆነ ያለው ግን ይህ ነው ! ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ማስፈራሪያ ዛቻ እንዲሁም የተወሰኑ ሰዎችን ከህዝቡ እየመዘዙ ለብዙሃኑ ችግረኛ እንቆቅልሽ ማለትና የህዝቡን ቅሬታ ማድበስበስ የተለመደ የገዥው ፓርቲ ስራ ሁኗል ፡፡
በተለይም ኢቲቪ (EBC) ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ›› በማለት የሚያቀርባቸው ሰዎች ግራ እያጋቡን ነው ! እስቲ ኑሮ ተወዶብናል ስንል እነዚህ ‹‹አንዳንዶች ›› ኑሮ አልተወደደም የሚል በደፈናው ይዘው ህዝቡን ማበሳጨት ምን ይጠቅማል ?ለማንስ ነው የሚመሰክሩት …መብራት ጠፋብን ስንል አንዳንዶቹ ‹‹ኧረ በጭራሽ›› ይሉናል ፡፡ አንዳንዶች ብዙሃኑን ‹‹ውሸታም ነህ ›› ይሉታል ፡፡ይሄ ህዝብን መናቅ ነው …እንደውም በኑሮ ውድነት ከሚሰቃየው ህዝብ በመሰረተ ልማት አውታሮች እጥረት ፍዳውን ከሚበላው ህዝብ የሚፈጠሩ ህፃናት ወደፊት
‹‹ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ›› ሲባሉ
‹‹ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን መሆን እንፈልጋለን ›› እንዳይሉ እሰጋለሁ ፡፡ ….በአሁኑ ሰዓት ያለምንም ምሬት በተድላ እንደሚኖሩና ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ እንደሆነ የሚመሰክሩ ኢትዮጲያዊያን ቢኖሩ እነዚሁ ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች›› ብቻ ናቸውና ምኞቱ እንዲህ ቢሆን አይገርምም ፡፡ ብሄራዊ ቴሌቪዥናችን ‹‹ራበን ›› ብሎ ሰልፍ ለወጣው ህዝብ ‹‹ለምን ኬክ አይበሉም ›› እንዳለችው ልእልት ሁኖብናል ፡፡ ስራ አጣን ስንል ቴሌቪዥናችን ለምን ስራ አትፈጥሩም ይለናል …ኑሮ ለማሻሻል ተሰደድን ስንል …አይ ጥጋብ ፈንቅሏችሁ እንጅ አገራችን ማሩ ወተቱ ይለናል …እንኳን ማርና ወተት የግዜሩንም ውሃ በስንት ጉድ ጥበቃ እንደማንዳረስ ሁሉ !
ችግሩ ይሄ ብቻ አይደለም በመልካም አስተዳደር ላይ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግር ውስጥ ነን ፡፡ ሙስና ቁጥር አንድ ጠላታችን ሁኗል …ሙስና ደግሞ በባህሪው ስልጣናቸውን ገንዘብ ላለው ሰው የሚያከራዩ ባለስልጣናትና የስራ ሃላፊዎች ዘንድ የሚፈጠር አደገኛ ተግባር ነው ፡፡ መንግስት ህዝቡን ጠቁም አትጠቁም ጨዋታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ‹‹ደህንነት›› ተብሎ ለአገር ደህንነት ሲባል ጓዳ ጎድጓዳውን እሰልላለሁ እንደሚለው የመንግስት አካል በዚህም ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ‹‹የደህንነት አካል ›› ቢቋቋምና መዘረፋችን ባይቆም እንኳን አሟጠው እንዳይነጥቁን ሃይ ቢባሉ መልካም ነው ፡፡መቸም ሚስኪን ፀሃፊና ጋዜጠኞችን ከማሳደድ ይሄ የተሸለ ስራ ይመስለኛል ፡፡
ሌላው የህወሃት አስጊ ችግር በብሔሮች መሃል የፈጠረውና አሁንም እየፈጠረው ያለው ቁርሾ ነው ፡፡ በተለይ በትግራይ ህዝብና በሌላው ኢትዮጲያዊ መካከል …በተደጋጋሚ ህወሃት በጉድለቶቹ ሲወቀስ የራሱን ችግርና በድርጅቱ ላይ የሚሰነዘረውን ጥላቻም ይሁን ነቀፋ በትግራይ ህዝብ ላይ እንደተሰነዘረ በማስመሰል የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ የሚያደርገው ጥረት በተደጋጋሚ የሚታይ የአደባባይ ሚስጥር ነው !! ይህ ነገር የትግራይን ህዝብ ከእህትና ወንድሞቹ ጋር እያቃቃረው ከስርአቱ ልዩ ተጠቃሚ የሆነ እያስመሰለው ይገኛል ፡፡ የትግራይ ህዝብ በህወሃት የስልጣን ዘመን ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ የተለየ ተጠቃሚ ሁኗል አልሆነም የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ እንደሆነ አለ !!
ይህን ያልኩበት ምክንያት ደግሞ ህወሃት እራሱ እንደሚለው ኢፈርት ወይም ትእምት እጅግ በጣም ግዙፍ እና በኢትዮጲያ ውስጥ( አንዳንዶች እንደውም በአፍሪካም ይላሉ) በሀብት የሚወዳደረው የሌለ የንግድ ተቋም ነው ፡፡ ባለቤትነቱ ደግሞ በተለይ እንደተቀመጠው የትግራይ ህዝብ ነው ! እንግዲህ ይህን የሚያክል ትልቅ ተቋም በስሩ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፋብሪካዎች የማእድን ማውጫወች የኮንስትራክሽን ተቋማት የትራንስፖርት ድርጅቶች የእርሻ ድርጅቶች ያሉት ባለፀጋ ድርጅት ባለቤቱ የትግራይ ህዝብ ነው ከተባለና በትክክል ለትግራይ ህዝብ ገንዘቡ ከዋለ የትግራይ ህዝብ በደንብ ተጠቃሚ ነው ለማለት ያስደፍራል !! ይሁንና እዚሁ ፌስቡክ ላይ የኢፈርት ነገር ላም አለኝ በሰማይ ነው እንደሚሉን በርካታ የትግይ ወንድሞቻችን አባባል ከሆነ ግን የትግራይ ህዝብ በተለይ ከስልጣኑም ከበረከቱም የሌለበት ሚስኪን ነዋሪ ያው እንደሁሉም ኢትዮጲያዊ ነው !!
ዋናው ነገር ተጠቀሙም አልተጠቀሙም አሁን ባለው በርካታ ኢትዮጲያዊ አመለካከት በተለያየ መንገድ እንደምንሰማውም ህወሃትና የትግራይን ህዝብ አዳብሎ የማየት ነገር ጎልቶ ይታያል ፡፡ ህወሃትም ቢሆን የትግራይ ህዝብና ህወሃት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው አይነት ዳርዳርታ ማብዛቱ በቀሪው የኢትዮጲያ ህዝብ ልብ ውስጥ ጥሩ ነገር ይፈጥራል የሚል እምነት የለኝም ! ህወሃት የፖለቲካ ድርጅት ነው ሊጠላም ሊወደስም ይችላል፡፡ እራሱን ችሎ መቆምና ከህዝብ የሚሰነዘርበትን ጥላቻም ሙገሳም ህዝቦችን ሳያነካካ መቀበል ይኖርበታል ፡፡ መልካም አስተዳደር ያሰፈነ ገዥ ፓርቲ የዚህኛው ብሔር የዛንኛው ዘር ነው አይባልም ጥሩ ድርጅት የሚያስተዳድረው ሃገር ድርጅት ነው !! አምባገነን እና ፀረ ህዝብ መንግስት ግን ከማንም ይጠጋ በማንም ይጠለል ህዝባዊ አይደለምና ብሔር የለውም !! አዎ የመላውን የሰው ልጆች ነፃነት ሰበዓዊና ዲሞክራሲ መብት ገፋፊ ከሆነ አምባገነን ብሄር የለውም!!
ይሄ ህወሃትን የነካ የትግራይን ህዝብ ነካ ጨዋታ በ1993 እና 1997 ላይ በተለይ በአዲስ አበባ የተከሰቱትን ተቃውሞች ላይ ነህዝቦች መካከለል አስነስቶ የነበረውን ተገቢ ያልሆነ መዘዝ በማየት ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መታዘብ ይቻላል ፡፡ ያ ጊዜ የዚህ የጥላቻ ዘር ውጤት ፈጦ የታየበት ነበር ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂው ህወሃት ነው !! ለምን ቢባል በህዝቦቹ መካከል ወንድማማችነትን ለማጎልበት በቂ ስራ አልሰራም … (ፍላጎቱም ያለው አይመስልም) በመንግስት ስራ ውስጥም ሆነ በሌሎች ስራዎች የተሰማሩ አንዳንድ የአካባቢው ተወላጆች የትጥቅ ትግሉን ታሪክ የግል ጀብዷቸው ብቻ አድርገው ሲደነፉና ስለታገሉ ብቻ ልዩ ተጠቃሚ የመሆን መብት እንዳላቸው በተለያየ መንገድ ሲጠቅሱ መንግስት መስመር ለማስያዝ ያደረገው ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም !!
አንዳንዴ እኮ ተራ መጠጥ ቤት ውስጥ ሳይቀር በሚነሳ አምባጓሮ ‹‹ደሜን አፍስሸ ባቀናኋት አገር ›› የሚላችሁ እንጩጭ ብሔረተኛ ያጋጥማችኋል ፡፡ እዚህ ፌስቡክ ላይ በፀያፍ ስድብ ታሪክና ታላላቅ ሰዎችን በማጠልሸት ከእኛ በላይ አዋቂ የለም በማለትና አሳዛኝ ድርጊቶችን በመፈፀም የሚታወቁትም ተመሳሳይ ሰዎች ናቸው !! ይህ ከተጋነነ እውቀት ላይ ሳይሆን ትእቢት ላይ ከተመረኮዘ መጥፎ በራስ መተማመን የሚፈጠር በሽታ ከእኔ በላይ ላሳር የሚያስብላቸው እነዚሁ ሰዎች ናቸው !!
ለዚች አገር መሳሪያ አንስቶ የተዋጋው ብቻ ሳይሆን ግንበኛውም ሃኪሙም አስተማሪውም ላቡን አፍስሶላታል !! አበቃ !! ማንም ስለታገለ ደሙን ስላፈሰሰ ለህዝብ ነፃነት በጎ ነገር እንዳደረገ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንደተወጣ ያስብ እንጅ ለፈሰሰ ደሙ ከኢትዮጲያ ህዝብ ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳለው ወይም ልዩ ተጠቃሚ የሚደርገው የይለፍ ወረቀት እንደያዘ አድርጎ ማሰብ ነውርም አሳፋሪ አስተሳሰብም ነው !! ሚሊየኖች እየወደቁላት እዚህ የደረሰች አገር ለሟችም ለገዳይም ነፃነትን እንጅ ካሳን የከፈለችበት ዘመን የለም ! ደሜ ለፈሰሰበት ይከፈለኝ የሚል እሳቤ ያለው ዜጋ ቅጥረኛ ወታደር እንጅ በምንም መስፈርት ጀግና ሊባልና ሊሞካሽ አይገባም !! የመስዋእትነት ክፍያው ነፃነት ብቻ ነው !! ነፃነቱም ለሁሉም ህዝብ በእኩልነት !!
መንግስት ለምን የፃፉትን ሁሉ ያስራል .. ለምን በተናገሩት ቁጥር ያኮርፋል … ዜጎቹን አኩርፎ ከውጭ አገር ሽማግሌ እስኪመጣለት አለያም አስሮ የሚያሰቃያቸው ዜጎቹ ያውም በካርዳቸው ድምፃቸውን ሰጡኝ የሚላቸው …ይቅር በለን ብለው እግሩ ስር እስኪወድቁለት የሚጠብቅ ስርዓት ምን አይነት መንግስት ሊወጣው ይችላል …ሁልጊዜ ስለመንገድ አውሩ ሁልጊዜ ስለፋሲካ ብቻ አውሩ የሚል መንግስት እንዴት የህዝብ መንግስት ሊሆን ይችላል ! መፅሄት ላይ ኮሽ ሲል በህዝብ ላብ በህዝብ ግብር በተማሩ ወታደሮችና ደህንነቶች ዜጎቹን የሚያሳፍስ ዘመድ ወዳጅ እንዳይጎበኛቸው የሚከለክል መንግስት ማንን ነው የሚመራው ….
በዚች በአርባኛ አመት በዓል ላይ የሚታየው ሌላው አሳዛኝ ነገር ደግሞ የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ በላይ ጀግና አድርጎ የማቅረቡ ነገር ነው …እውነታውን ማስቀመጥ ይኖርብናል … ደርግን ለመጣል የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጲያዊያን ወገኖቹ በላይ መስዋእትነት ከፍሏል ይሄ የማይካድ ሃቅ ነው …. ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ከሰማየ ሰማያት የተለየ ጀግንነት ስለተቸረው ሳይሆን የትጥቅ ትግሉ በወቅቱ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ በሚመች መልኩ ስላልተደራጀ ነበር ፡፡ እንጅኮ ደርግ ሲወድቅ ከአስራ ስምንት በላይ ብረት ያነሱ ተፋላሚዎች በኢትዮጲያ ነበሩ ! ቀደም ብለን ካየነውም በርካታ ኢትዮጲያዊ ደርግ አፍንጫ ስር ቁሞ በመፋለም ለህወሃት ትጥቅ ትግል መንገድ ከፍቷል …ተማሪዎች ለነፃነት ደማቸውን አፍስሰውላታል … ግለሰቦች ጨካኙን ስርአት ፊት ለፊት ተቃውመው ተሰውተዋል ….
… ደግሞ በህወሃት የትጥቅ ትግል ውስጥ ‹‹አምስት ሁነው ትግሉን ጀመሩ›› የሚለው የታሪክ መነሻ አምስት ሁነው ትግሉን ጨረሱ ማለት አለመሆኑን ማወቅም ተገቢ ይመስለኛል !! ሁሉም ኢትዮጲያ አንጀቱ አሮ በየቤቱ በተቀመጠበት ሰአት እንኳን አምስት አንድ ሰውም ተከተሉኝ ቢል እልፍ ያኮበኮቡ ኢትዮጲያዊያን ስርዓቱን ለመፋለም ዝግጁ ነበሩ …. ነበሩ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት በፊት ብረት አንስተው ስርዓቱን እንቢ ያሌ ነበሩ ፡፡ ምሬት ፅዋዋ ሞልቶ ነበር ህዝብ አገዛዙን አክ እትፍ ብሎት ነበር … ህወሃት አሁን ቁጭ ብሎ ማሰብ ያለበት የሚመስለኝ አምስት ሁኖ የትጥቅ ትግሉን መጀመሩን ሳይሆን አሁን የኢትዮጲያ ህዝብ ባጠቃላይ አምስት የሚወዳቸው የሚምናቸው መሪዎች ህወሃት ውስጥ አሉ ወይ የሚለውን ነው !!
በነገራችን ላይ ህወሃት ባለፈበት ጎዳና ሁኑ መላው የኢትዮጲያ ህዝብ ከጎኑ ነበር !! የትግራይ ህዝብ ብቻው ከኢትዮጲያ ህዝብ የተለየ ጀግና ሊሆን አይችልም!! …ከወንድሞቹና ከእህቶቹ በላይ ጀብዱ እንዳለውም ማሰብ አይኖርበትም !! ይሄ እጅግ የተጋነነና የተዛነፈ እሳቤ ነው በኋላ ያልሆኑትን አድርጎ የማይገፉት ተራራ ጋር የሚያጋጨው …ሩቅ ሳንሄድ ሻእቢያ ከእኔ በላይ ጦርነት አዋቂ ከኔ በላይ ተኳሽ ላሳር ብሎ በእብሪት ከወረረን እኮ ገና አስራ አምስት አመት አልሞላውም … ይሁንና የቱንም ያህል ራሱን ጀግና ያድርግ የቱንም ያህል ራሱን ብልህና ጥበበኛ አድርጎ ያስብ ከመላው ኢትዮጲያ እንደአሸዋ የተዘረገፈው ህዝብ ነበር የከፈለውን ያህል መስዋእትነት ከፍሎ አገርን የታደጋት !! እውነቱን እናውራ ከተባለ የሻእቢያን ወረራ የትግራይ ህዝብ ብቻውን ይቋቋመው ነበር ?
መንግስት በቀረው እድሜ ሁሉ በብሔሮች መሃል በሃይማኖቶች መሃል እንዲሁም በፖለቲካ ድርጅቶች መሃል ታየም አልታየም ታወቀበትም አልታወቀበትም ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ባይኖረው መልካም ነው ፡፡ የፈለገ ቢከፋፈል ቢለያይ ገዥውን የጋራ ጥላት ያደረገ ህዝብ በአንድ ላይ መቆሙና መልሶ ችግር መሆኑ አይቀርም ! ዛሬ 40ኛ አመት በዓሉ ሲከበርም ይሄንኑ ታሳቢ ማድረጉ የሚበጅ ይመስለኛል !
ጉዳየን ስቋጭ እራሱ የህወሃት 40ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አከባበር ላይም ታሪካዊ ጥያቄ በማንሳት ነው …
1965 ዓ/ም የወሎ ህዝብ በእረሃብ ሲረግፍ ከታች ጀምሮ እስከላይ እስከንጉሱ ርሃቡን በመደበቅና በማድበስበስ ስለረሃቡ የተነፈሱትን ሁሉ በማሰር ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ የ80ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ለማክበር አዲስ አበባን በከፍተኛ ወጭ እያሽቆጠቆጧት ነበር ..የዜና አውታሮችም አገር ጥጋብ እንደሆነ ምርትም እንደተትረፈረፈ እየዘገቡ ነበር (እንዳሁኑ EBC) በዓሉም ሃምሌ 1965 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ ተከበረ … ይሄንና ይሄ የታፈነ ግፍና ሌላም የህዝብ በደል ተዳምሮ ንጉሱን በብርሃን ፍጥነት ከነዙፋናቸው አንኮታኮተ ኢትዮጲያንም ለሰሚው ወደሚዘገንን ወታደረዋ አገዛዝና ደም መፋሰስ ዳረጋት !!
ደርግ …በተመሳሳይ በርካታ ኢትዮጲያዊያን በተራቡበትና በእርሃብ በሚረግፉበት ወቅት የፓርቲ ምስረታ ገለመሌ በዓሉን መላዋን አዲስ አበባ በመብራትና በመፎክር አንዎጥቁጦ ሲያከብር ነበር ! ደርግም በተመሳሳይ ‹‹ጠላቶቸ …ሻእቢያ ገንይ ምናምን ከማለት ውጭ ስለውስጥ ችግሩ ትንፍሽ ሳይል ፌሽታውን አከበረ ….ዛሬስ ምን እያደረግን ነው … የእውነት ህዝባችን ፌሽታችንን ህዝባችን በዓላችንን የሚጋራበት የተረጋጋ ኢኮኖሚ ሰላም እና ዲሞክራሲ ላይ ነው …..? እንደኔ እንደኔ አዎ አገራችን በርካታ የልማትና የሰላም እምርታዎችን አስመዝግባለች ግን …በአደገኛ ሁኔታዎች ያሽቆለቆለችባቸው ሁነቶች ይበዛሉ … ስደቱ አሳሳቢ ነው …ከአገር ውጭ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ክፍለሃገራት ወደአዲስ አበባ የሚፈልሰው ህዝብ ሲታይ ‹‹እድገቱ የፈጠረው›› እያልን ማላገጡ መፍትሄ አይመስለኝም !!
አሁን ያለው የህዝብ ብሶት ቢዘረዘር ማለቂያ የለውም ግን ህወሃትን እንደአንድ ዜጋ የምጠይቀው …ቅን ብልህና ከቂምና በቀል የፀዳ ስርዓት ለመገንባት ይነሳ … በገፍ እየጓፈፈ በየምክንያቱ በየእስር ቤቱ ያጎራቸውን ጋዜጠኞች ጦማሪያን ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት አባላትና የሃይማኖት ሰዎችን ይፍታ ! መንግስት እንኳን ውሃ ቀጠነ ብሎ ያሰራቸውን ንፁሃን ቀርቶ በብዙ ጥፋት ውስጥ ያለፉ የህግ ታራሚዎችን በምህረት መልቀቁ ህዝባዊነት ሰበአዊነት ነው !! አዎ ‹‹ 40ኛ አመት የምስረታ በዓሉ ግማሹን አስሮ ግማሹን አስጨፍሮ ›› ሊሆን አይገባም !! ከየትኛውም ድግስ ከየትኛውም ጭፈራና ንግግር በላይ ሁሉም ኢትዮጲያዊ ከህወሃት ኢህአዴግ የሚጠብቀው መሰረታዊ የአገሪቱ ችግሮች ያለምንም ምክንያት ድርደራ እንዲፈቱለት እንዲሁም ሃሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ የተለያየ ስም ተለጥፎባቸው ያታሰሩ ልጆቹን ጓደኞቹን የስራ ባልደረቦቹንና ወንድምና እህቶቹን እንዲፈታለት ነው !!
Ethiopia’s Perfekt Elektion? Much Ado About Nothing!
Who knows about thiopia’s perfekt elektion in May 2015?It is the middle of February 2015 as I write this commentary. But I always remember in November.
I see some of my Ethiopian friends carrying long forlorn melancholy faces. A few lines from Shakespeare’s “Much Ado About Nothing” flash in my mind:
Why, what’s the matter,
That you have such a February face,
So full of frost, of storm and cloudiness?
A February face with Sturm und Drang in their hearts. They reply in gloomy resignation with questions. Did I know this or that about the “election”? “Election”, eh? I feign ignorance. Of course, they are asking me about the “election” set for May 24, 2015 by the Thugtatorship of the Tigrean Peoples Liberation Front (T-TPLF).
Am I aware the T-TPLF has jailed leaders and members of Semawayi (“Blue”) Party, the Unity for Democracy and Justice (UDJ), and the Arena Tigray Party? Did I know the T-TPLF police are busting open the heads of peaceful protesters? Did I know the “criminal case” of the Zone 9 Bloggers had been postponed for the umpteenth time? Did I know the T-TPLF is harassing and jailing activists and critics every day? What do I think of the support the T-TPLF is getting from the United States, the European Union, United Kingdom, the World Bank, the International monetary Fund and all the rest to steal the 2015 “election” like they did in 2010?
Do I think the T-TPLF is scared _ _ _ _less about the possibility of a spontaneous political combustion to its rule, election or no election? (That’s a no brainer. Why else would they jail young Facebook bloggers?) Do I “know” as much about the May “elections” as President Obama? (Well! I would like to ask President Obama if he knows a state that silences the opposition is a source of terror to all its citizens as did his predecessor Harry Truman. “Once a government is committed to the principle of silencing the voice of opposition, it has only one way to go, and that is down the path of increasingly repressive measures, until it becomes a source of terror to all its citizens and creates a country where everyone lives in fear”, cautioned Truman.)In late September 2014, Obama glibly remarked, “… the Prime Minister [Hailemariam Desalegn] and the government is going to be organizing elections in Ethiopia this year. I know something about that…” (Obama would have known “something” about the terror of living in a police state had he read my commentary the Republic of Dystopia Ethiopia!
I was so stunned, intrigued and outraged by Obama’s remark I wrote a full commentary demanding to know the “something” he knows about the May 2015 “election”? I made that demand out of an abundance of concern and caution. Did Obama “know” the “election” is going to be stolen? Did he “know” it was going to be rigged? Did he “know” opposition party leaders would be harassed and jailed? Did he “know” journalism and blogging in Ethiopia would be declared state crimes? Did he know…? Long story made short, I posted a list of interrogatories inquiring into President Obama’s “knowledge” of the Ethiopian “election” in my commentary “What Does President Obama “Know” About Ethiopia’s ‘Election’?
But who else “knows” about Ethiopia’s 2015 “election”?
The marionette and bumbling “Prime Minister” Hailemariam Desalegn knows the 2015 “election” will be “perfect”. The pitiful and hopelessly discombobulated Hailemaraim not long ago remarked, “We have to make the [election] process democratic, free, fair and credible in the eyes of our people.” He said his party could ensure a free and fair election because “Our institutional process and our laws and regulations are perfect. It is not the law that hinders but the implementation of these laws.”
True, it is not the laws but the T-TPLF that “hinders the implementation of these laws.” I also have no doubts that Hailemariam and his T-TPLF will “implement” (I did not say rig or manipulate) the “election laws” to deliver a “perfect election”. They damn near had a “perfect election” in 2010. They won by 99.6 percent! That is what I call a super duper close near miss or near hit. What’s four-tenths of a point away from 100 percent, anyway! A teeny weeny statistical error? (By the way, I want to be the first one to offer kudos to the T-TPLF for having won the “perfekt elektion” in May 2015 now. I guess Hailemariam will soon find out the meaning of the expression, “use him and lose him.) The last time such perfektion was achieved anywhere in the world was during the 2002 Iraqi election. Saddam Hussien won by 11 million-to-0.)
ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ሊወጡ ሲሉ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በደህንነቶች ተመለሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ሶስቱ ጄኔራሎች በሳሞራ ምላሽ በመበሳጨት ከስልጣናቸው ለማስነሳት በምስጢር ቢመክሩም መረጃው ባልታወቀ መንገድ አፈትልኰ ጄ/ል ሳሞራ ዘንድ በመድረሱ ጄ/ል ሰዓረ ከሰሜን ዕዝ አዛዥነታቸው፣ ጄ/ል ሞላ ከአየር ሃይል እንዲሁም ጄ/ል አበባው ከያዙት ስልጣን በሳሞራ በአስቸኳይ እንዲነሱ ሲደረግ በተለይ ጄ/ል አበባው ከ2 ወር በፊት ከመከላከያ እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮቹ አስረድተዋል። በጄ/ል ሰዓረ ቦታ ጄ/ል ገብራት አየለ ሲተኩ በጄ/ል ሞላ ደግሞ የአግአዚ ክ/ሰራዊት አዛዥ ጄ/ል አደም መሐመድ መተከታቸውን አስታውቀዋል።
ጄ/ል አበባው ታደሰ ወደ ውጭ ለመውጣት ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ በደህንነቶች እንዳይወጡ መደረጋቸውን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል።
ሰበር ዜና
መነበብ ያለበት-የወቅቱ የኢትዮጵያ ወጣት እና ህወሓትን የማስወገድ ትግል (ታደሰ ብሩ)
አገራችን ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪቃ ሁለተኛ ስትሆን በተባበሩት መንግሥታት መመዘኛ “ወጣት” ተብሎ በሚጠራው የኅብረተሰብ ክፍል ብዛት ግን አንደኛ ነች። እርግጥ ነው ወጣነት በእድሜ ብቻ የሚገለጽ የኅብረተሰብ ክፍል አይደለም። የሚከተለው የወጣት ትርጉም ሰፋ ያለ ተቀባይነት ያለው ይመስለኛል….
ወጣት፣ በማኅበረሰቡ አንኳር ጉዳዮች ላይ እየወሰነ ባለው “አዋቂ” ተብሎ በሚጠራው የኅብረሰተሰብ ክፍል እና ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ውሳኔዎች ለመስጠት ገና ባልተዘጋጀው ሕፃን መካከል ያለ የኅበረተሰብ ክፍል ነው።
በዚህ ትርጓሜ መሠረት ወጣትነት የማኅበራዊ ግኑኝነት መገለጫ ጽንሰ ሀሳብ ነው። ይህ ማኅበራዊ ግኑኝነት ወደ እድሜ እንመዝረው ስንል ችግር ውስጥ እንገባለን፤ ምክንያቱም ወጣቱ ወደ አዋቂነት የሚሸጋገርበት ጊዜ እንደየአገሩ ባህሉና እንደ እድገቱ ይለያያል። በዚህም ምክንያት ነው የወጣትነት የህግ ትርጓሜዎች በየአገሩና ባህል የተለያዩ የሆኑት። ለምሳሌ፣ የተባበሩት መንግሥታት ወጣት ማለት “እድሜው 15 እስከ 24 ዓመታት ድረስ ያለው ሰው ነው” ሲል ይተረጉማል፤ ይሁን እንጂ የራሱ አካል የሆነው UN Habitat “ወጣት ማለት እድሜው 15-32 ዓመት ያለው ሰው ነው” ይላል። በአገሮች ትርጓሜ መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ በጣም የተዘበራረቀ ነው። ዩጋንዳ ውስጥ እድሜው 12-30 የሆነ ዜጋ ወጣት ሲሰኝ ጎረቤትዋ ኬንያ ውስጥ 18-35 ነው። ስለዚህም አንድ የ16 ዓመት ወጣት ዩጋንዳዊ ድንበር ተሻግሮ ኬኒያ ሲገባ ሕፃን ይሆናል፤ አንድ የ 32 ዓመት ኬንያዊ ወጣት ዩጋንዳ ሲሻገር ጎልማሳ ይሆናል። ከአፍሪቃ ዝብርቅርቅ የወጣት ትርጓሜዎች ለአብነት ጥቂቶቹን ላንሳ: ሞውሪሸስ 14-29፣ ደቡብ አፍሪቃ 14-29፣ ናይጄሪያ 18-35፣ ጂቡቲ 16-30፣ ኬኒያ 18-35።
በ2004 ዓም የወጣው የኢትዮጵያ መንግሥት የወጣቶች ፓሊሲ ከ15 -29 ዓመታት ውስጥ የሚገኝን ኢትዮጵያዊን ዜጋን ወጣት ብሎ ይተረጉመዋል። በወጉ የሚያስተናግደው አላገኘም እንጂ ይህ ፓሊሲ በወጣበት ወቅት የኢትዮጵያ የወጣት ትርጓሜ እንደ ኬኒያና ናይጄሪያ 18- 35 መሆን ይገባዋል የሚል ሀሳብ ቀርቦ ነበር። የወጣቱ ከፓለቲካና ማኅበራዊ ውሳኔዎች መገለል መብዛትን በማጤን የላይኛው ጣራ እስከ 39 ከፍ ማለት አለበት የሚል ክርክርም ነበር። በበኩሌ ሥራአጥነትና ዘረኛ የህወሓት ፓሊሲ ያስፋፋው መድልዎና መገለል የወጣት የእድሜ ማዕቀፍ እንዲሰፋ አድርጓል ብዬ አምናለሁ። አርባ ዓመት አልፏቸው ከወላጆቻቸው ጥገኝነት ያልወጡ “ወጣቶች” ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው። እኔ በዚህ አጭር ጽሁፍ ውስጥ ስለወጣት ስናገር እድሜው በ 18 እና 39 ዓመታት መካከል ያለውን ዜጋ እያሰብኩ ነው።
የዘመናችን ወጣት
የዘመናችንን ወጣት የሚተቹ በርካታ ጽሁፎች የወጡ ቢሆንም እኔ ብዙዎቹ ትችቶች አግባብ መስለው አይታዩኝም። በአንድ በኩል ወጣቱ የማኅበረሰቡ አካል በመሆኑ በወጣቱ ውስጥ የሚታየው ክፉም ሆነ ደግ ከማኅበረሰቡ የወረሰው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ነገሮች ሁሉ ወጣቱ ላይ ይጎላሉ። በሌላው ዓለም ያለው የመብቶች መከበር እና የኑሮ ሁኔታ ከራሱ እውነታ ጋር ሲያመዛዝን የአንዳንዱ ወጣት ልብ በረሀ ለማቋረጥ፣ ባህር ለመሻገር እንዲደፍር ያደርገዋል፤ የአንዳንዱ ወጣት ልብ ደግሞ የማዕከላዊ እስር ቤትና በውስጡ ያለውን ቶርቸር እንዳይፈራ ያፀናዋል። የዘመናችን ወጣት ሊወደስባቸው የሚገቡ በርካታ ነጥቦች ቢኖሩም የሚከተሉት ግንባር ቀደም ናቸው ብዬ አምናለሁ።
የዘመናችን ወጣት ማሰብ ተከልክሎ ያደገ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ማሰብና መመራመርን የሚያበረታቱ ሁኔታዎች የሉም ማለት ሁኔታዉን አቅሎ መመልከት ይሆናል። ምርምር የሚጀምረው ከመጠራጠር ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ሥርዓቱ ትክክል ናቸው ያላቸውን ነገሮች መጠራጠር ወንጀል ነው። ኢትዮጵያዊ ወጣት “የምነግርህን ሳትጠራጠር አምነህ ተቀበል” ተብሎ ያደገ ነው። በዛሬቷ ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃዎችን ማፈላለግ፣ ማንበብ፣ ማዳመጥ፣ ሀሳብ መለዋወጥ ወንጀል ነው። ወሳኝ በሆነ የፓለቲካና የፍልስፍና ጉዳዮች ላይ አቋም ይዞ መከራከር አይቻልም። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም የሚሰጠው ትምህርት እንደ ርዕዮተ ዓለም ቅስቀሳ ሁሉ “ያለቀለት እውነት” እንጂ ተማሪዎች በራሳቸው መንገድ ሊያረጋግጡት የሚገባ ጥሬ ሀሳብ ተደርጎ አይደለም። እንዲህ ዓይነቱ የአዕምሮ ውርጅብኝ የወረደበት ትውልድ ሆኖ እያለ ፈጽሞ አለመደንዘዙ፤ ዛሬም በየእውቀት ዘርፉ ጎበዞች የሆኑ ወጣቶች መኖራቸው ድንቅ ነው። የዛሬ ወጣት አስተማሪም ትምህርት ቤትም ሳይኖረው – ያለ አስተማሪ እና ያለ ትምህርት ቤት – አሁን እደረሰበት ደረጃ ላይ መድረሱ ሊያስመሰግነው ይገባል።
ከሰማንያ በመቶ በላይ የሆነው ወጣት ከኢህአዴግ ሌላ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሮ አያውቅም። እድሜውን በሙሉ ኢህአዴግ እና መንግሥት አንድ ሆነው ነው ያደገው። ስለአገራዊ አንድነት ከሰማው ስለ “ብሔር”፣ “ብሔረሰቦች” የሰማው በእጅጉ ይበልጣል። የአሁኑ ወጣት የኢትዮጵያ ታሪክ ተብሎ እየተነገረው ያለው የቂምና የበቀል ታሪኮችን ነው። አንድ የሃያ አምስት ዓመት ወጣት ዛሬ ያሉት ክልሎች ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ቢመስሉት እንኳን ልንፈርድበት አይገባም። ከሬድዮና ከጋዜጣ ብቻ ሳይሆን ከወላጆቹ ጭምር ሲሰማው የኖረው ይህንኑ ነው። ዘረኝነት መንግሥታዊ ፓሊሲ በሆነበት፤ “አዋቂ” የሚባሉት ታላላቆቹ ራሳቸው ዘረኞች አሊያም በፍርሀት ተሸብበው ዝምተኞች በሆኑት አገር አድጎ ኢትዮጵያዊነትን ፈጽሞ አለመርሳቱ ይህንን ትውልድ በእጅጉ ያስመሰግነዋል።
የዛሬ ወጣቶች በተለምዶ “ያ ትውልድ” የሚባለው ትውልድ ልጆች ናቸው። “ያ ትውልድ” ደግሞ ብዙ አልሞ የትም ያልደረሰ፤ ሊያጠፋው ከተነሳው አውሬ የባሰ ጭራቅ – ህወሓትን – ያነገሰ ነው። የዛሬ ወጣት ወላጆች በወጣትነታቸው የነቃ የፓለቲካ ተሳትፎ የነበራቸው ሊሆን ይችላል፤ ምናልባትም ማርክሲስትና ሌኒኒስቶች ሆነው ለላብ አደራዊ ወይም ወዛደራዊ ዓለም ዓቀፋዊነት ሲታገሉ ኖረው ይሆናል፤ አሊያም ነፃ አውጭዎች የነበሩ ሊሆኑ ይችላሉ። እርግጥ እነሱ በጽናትና ቆራጥነት ታግለው ሊሆን ይችላል። ያንን ስሜትና ጽናት ግን ወደ ወጣቱ አላስተላለፉትም። እንዲያውም “እኛም በጊዜዓችን ሞክረን አልቻልነውም” እያሉ የአዲሱን ትውልድ ሀሞት የሚያፈሱ ሆነዋል። እንደ “ያ ትውልድ” ሁሉ ዛሬም እስርና ግርፋትን የማይፈሩ ወጣቶች መኖራቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። እንደ “ያ ትውልድ” አየር ላይ ለተንሳፈፈ ርዕዮተ ዓለም ሳይሆን ለራሳቸውና ለሀገራቸው ክብርና ነፃነት ሕይወታቸውን ለመስጠት የቆረጡ ወጣት ወንዶችና ሴቶችን ስናይ ተስፋችን ይለመልማል። እርግጥ ነው እንዲህ ዓይነት ወጣቶች ቁጥራቸው ጥቂት ነው፤ የታሪክን ቦይ የሚቀዱት ግን እነዚህ ጥቂቶች መሆናቸው ጥርጥር የለውም።
ስለዛሬው ወጣት ምግባረ ብሉሽነት ብዙ ይወራል። እኔ ይህ ትክክል አይመስለኝም። የሥራ አጥ ብዛት እንደ አሁን የተስፋፋበት ጊዜ የለም። ዘጠና በመቶ ያህሉ ሥራ አጥ በወጣትነት የእድሜ ክልል ያለ ነው። “ትምህርቱን ጨርሶ” የሙሉ ጊዜ ሥራ አጥ ሆኖ የተቀመጠ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የከተማ ወጣት አለ። ሥራ አጥነት ከኢኮኖሚ ችግርነቱ የባሰው ማኅበራዊ ችግርነቱ ነው። ሥራ አጥ ሆኖ ኃላፊነት የሚሰማው እና በማኅበረሰቡ የሚደመጥ ዜጋ መሆን ከባድ ነው። ሥራ አጡን ወጣት ወደ አጓጉል ልማዶች የሚስቡት ክሮች ብዙ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ስናይ ግን ሁኔታው በሚወራው መጠን ተስፋ አስቆራጭ አይደለም። ዛሬም ሥጋ ቤቶች በሽቦ አጥር አልታጠሩም፤ ወርቅ ቤቶች አርቲፊሻል ሳይሆን እውነተኛ ወርቅ በመስታወት ውስጥ ዘርግተው ይሸጣሉ፤ ብዙ ምግብ ቤቶች ዋጋ ሳይቀበሉ ያስተናግዳሉ። እነዚህ ነገሮች ስናስተውል የኢትዮጵያዊውን ወጣት ሥነምግባር ማድነቅ ይገባናል ብዬ አስባለሁ።
በከተሞች ተቀጥሮ የመሥራት እድል እየጠበበ ከመምጣቱ በላይ ያች ጠባብ እድልም በህወሓትና አጫፋሪዎቹ መዳፍ ውስጥ ናት። ህወሓት እና አጋፋሪዎቹ እያንዳንዱን የሥራ እድል “ሰው መግዣቸው” ሆኗል። በመንግሥት ሥራ ለመቀጠር ከትምህርትና ሙያ ይበልጥ የኢህአዴግ አባልነት ወሳኝ መሆኑ አገር ያወቀው ሀቅ ነው። ወጣቶች የራሳቸውን የግል ሥራ የሚፈጥሩበት ሁኔታም የለም። ነፃ አስተሳሰብ፣ ነፃ የንግድና የፍትህ ተቋማት በሌሉበት ስለ “ኢንተርፕሪነርሺፕ” መስበክ ባዶ ዲስኩር ነው። በአንድ በኩል የወጣቱ የፈጠራ ተነሳሽነት እንዲላሽቅ ተደርጓል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከመንግሥት ሥራ ያልተናነሰ የወያኔ ጥቃት በግሉ የሥራ ዘርፍ ውስጥም አለ። አፍቃሪ ወያኔ ያልሆኑ ነፃ ዜጎች የግል ቢዝነስ ቢጀምሩ እንኳ ሳንካዎች ይበዙባቸዋል፤ ሳንካዎችን ተቋቁመው አንገታቸውን ብቅ ካደረጉ በግብር እና በቫት ይኮረኩሟቸዋል፤ አቤቱታ ማሰሚያ ቦታ የለም።
በገጠር ያለውም ሀቅ ተመሳሳይ ነው። የህወሓት የመሬት ፓሊሲ ግንባር ቀደም ሰለባ የሆነው የገጠር ወጣት ነው። መሬት ተሸንሽኖ አልቋል፤ ዛሬ ግማሽ ሄክታር መሬት ያለው ቤተሰብ ሀብታም ነው። በብዙ የአገራችን ክፍሎች ወጣት ገበሬዎች ከሩብ ሄክታር ያነሰ መሬት ይዘው ነው የራሳቸውን ትዳር የሚጀምሩት። ሩብ ሄክታር ለጓሮ አትክልት መትከያነት ቢሆን እንጂ ለሰብል አይበቃም። በአንፃሩ ደግሞ ግብርናንና ገበሬን የሚጠሉ “ኢንቬስተሮች” የሚይዙት መሬት የሚለካው በ10 ሺዎች ሄክታር ነው። ድሮ የማይታወቀው የገበሬ ሩቅ አገር መሰደድ አንዱ ምክንያት ይህ ነው። በገጠር ዘርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች ከሚያባብሱ ነገሮች አንዱ ይህ የመሬት እጥረት ነው።
በገጠርም በከተማውም ያለው ሀቅ ይህ ሆኖ እያለ ዛሬም አገሩን ከልቡ የሚወድ ወጣት መኖሩ የሚገርም ነው።
አብዛኛው አዲስ ስደተኛ፣ ወጣት ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ስደተኛ ዓይነትና ስብጥር (demography) እና የስደተኛው መዳረሻ አገሮች ተቀይረዋል። ወደ ደቡብ አፍሪቃ፣ ሱዳን እና አረብ አገሮች ያለው ስደት “ፍልሰት” በሚባል መጠን ነው። ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች የማይታዩባቸው የገጠር መንደሮች ሞልተዋል፤ ወደ አረብ አገሮች አሊያም ደቡብ አፍሪቃና ሱዳን ነጉደዋል። አሜሪካ፣ አውሮፓና አውስትራሊያ የሚደርሰው ከስደተኛው ብዛት አንፃር ከቁጥር የማይገባው በጣም ትንሹ ነው። ታድያ በፓለቲካውም በኢኮኖሚውም ተደብድቦ፣ ተገፍቶ የወጣው ስደተኛ ወጣት ለአገሩ፣ ሕዝቡ፣ ባህሉና ታሪኩ ያለው ፍቅር የሚደንቅ ነው።
የኢትዮጵያ ፓለቲካና ኢኮኖሚ አንድ መለያ ባህርይ “እጦት” deprivation ነው። የፍትህ እጦት፣ የነፃነት እጦት፣ የመረጃ እጦት፣ የሚዛናዊ ትምህርት እጦት፣ የመሠረታዊ የጤና አገልግሎት እጦት፣ የመብራት ኃይል እጦት፣ የማገዶ እጦት፣ የመኖሪያ ቤት እጦት፣ የሥራ እድል እጦት፣ የኔት ዎርክ እጦት፣ የታክሲ እጦት፣ የእለት ጉርስ እጦት …. እጦት … እጦት … እጦት … ። ህወሓት እጦቶችን ተጠቅሞ ነው ወጣቱን እመዳፉ ውስጥ ለማስገባት እየጣረ ያለው። (ህወሓት እና እጦት የረዥም ጊዜ ወዳጅነት እንዳላቸው የታወቀ ነው፤ በድርቅ ለተጎዳው ሕዝብ በመጣ እርዳታ ራሱን ያደራጀ እጅግ ክፉና መሠሪ ድርጅት ነው) በእጦቶች የተጎዳ ሕዝብ ለእጦቶቹ ደረጃ ያወጣላቸዋል። መሠረታዊ እጦቶችን (ለምሳሌ የእለት ጉርስ፣ ኮንዶሚኒየም) ለማሟላት “ትላልቅ” እጦቶች (ለምሳሌ የፍትህና የመብት እጦቶችን) ይታገሳል።
አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ግን እጦቶችን በመሣሪያነት የሚጠቀም ፋሽስታዊ አገዛዝ ውስጥ አድገው እያለ ስለፍትህ፣ ስለነፃነት፣ ስለእኩልነት፣ ስለመብቶች የሚያሰላስሉ፣ የሚጽፉ፣ የሚታገሉ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ወጣቶች ያሉን መሆኑ መታደል ነው። ዛሬ ይህንን ማስታወሻ በምጽፍበት ወቅት በቃሊቲ፣ በቂሊንጦ፣ በዝዋይ እና በማይታወቁ በርካታ እስር ቤቶች ውስጥ በርካታ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለሰብዓዊ ክብርና ነፃነት ዋጋ እየከፈሉ ነው። እነሱን የመሰሉ በርካታ ወጣቶች ከእስር ቤቶች አጥሮች ውጭ በከተሞችም በገጠሮችም መኖራቸውን ሳስብ ደግሞ በዚህ ትውልድ ወጣቶች እኮራለሁ። ከዚህ አልፎ በእጦቶች መታሰር መሯቸው ወደ ተራራዎች ያቀኑ ወጣቶች መኖራቸው እና ቁጥራቸውም እያደር እየበዛ መሆኑ ስሰማ በዚህ ትውልድ ላይ መቅናት ያምረኛል።
ኅብረት መፍጠር ቀላል የሚሆነው በቃላት ነው። “ተባበሩ” ብሎ መስበክ እና “እንዴት መተባበር አቃታችሁ” ብሎ መዝለፍ በጨለማ ሌሊት ወደ ሰማይ አንጋጦ ከዋክብትን የመቁጠር ያህል አዝናኝ ነው። መተባበር የትም አገር ቢሆን ከባድ ነው። እኛ አገር ደግሞ ይበልጥ ከባድ የሚያደርጉት ሁኔታዎች አሉ። (በነገራችን ላይ ህወሓት፣ ኢህአዴግ ላይ እንዳደረገው ዓይነት የአፈና ጥርነፋን “ኅብረት” ብለው የሚጠሩ ሰዎች አሉ) የመተባበር ችግራችን ዛሬ የተጀመረ አይደለም። መተባበር ያስቸገረን በፓለቲካው መስክ ብቻም አይደለም። ሌላው ቀርቶ ስለ ኅብረት ሲሰብኩ ውለው ሲሰብኩ የሚያድሩ የሃይማኖት አባቶችም እርስ በርሳቸው መተባበር አልቻሉም።
የመተባበር ችግር ለህወሓት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮለታል፤ ልዩነቶችን እያራገበ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ እየተሳለቀ ተዝናንቶ ይገዛል። ዉጣ ውረድ የበዛበት አስቸጋሪ መንገድ ቢሆንም እንኳን በዚህም ረገድ የተስፋ ጭላንጭል እየታየኝ ነው። ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ወጣቶች ወደ ፓለቲካ አመራር እየመጡ ነው። ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምሥራቅ፣ ከምዕራብና ከመሀል አገር የተወጣጡ ወጣቶች ለጋራ ኢትዮጵያ ሲሰለፉ፤ ያንንም ትግል በጋራ ሲመሩ ማየት የሚያኮራ ነው። የተለያዩ እምነቶች ተከታዮች የሆኑ ወጣቶች በፓለቲካ ድርጅት አመራርነት ተመርጠው በጋራ ሲሰሩ ማየት ተስፋ ሰጪ ነው። ለአንድ የጋራ ዓላማ ጉልበትን በማስተባበር ረገድ ብዙ ይቀረናል፤ ተግዳሮቶቹ በርካታ ናቸው፤ ያም ሆኖ ግን በወጣቱ በኩል እየታየው ያለው መናበብ ተስፋ ሰጭ ነው። የዛሬ ወጣት ውብ ኢትዮጵያን ከምናቦቻችን አውጥቶ በእውን ሊፈጥራት የታደለ ትውልድ ነው፤ ይህን ለማድረግ ደግሞ ብቃት አለው ብዬ አምናለሁ።
ቁጭት
ከላይ የዘረዘርኳቸው ስምንት መልካም ነገሮችን አዳብረናቸው፤ የወጣቱን ጉልበትና ተነሳሽነት በሚገባ ተጠቅመንበት ቢሆን ኖሮ እስካሁን የት በደረስን?
እነዚህን ስምንት አበረታች ነገሮች በሚገባ አሳድገናቸው ቢሆን ኖሮ:
ሰዎች ለመናገር፣ ለማንበብ፣ ለመስማት፣ ለመፃፍ የሚሸማቀቁበት አገር ዜጎች ባልሆንም ነበር፣
በራስ መተማመንን ያዳበሩ በርካታ ድንቅ የተፈጥሮና የማኅበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች፣ የፈጠራ ሰዎች በሕዝብ የተወደዱ ወጣት መሪዎች፣ በጥረታቸው የተሳካላቸው የቢዝነስ ሰዎች፣ … ወዘተ በኖሩን ነበር፣
ትምህርት፣ አዕምሮን ማደንቆሪያ መሆኑ ቀርቶ የምርምን አድማስን ማስፊያ፣ አዕምሮን ማበልፀጊያ እና ሙያ መቅሰሚያ ይሆን ነበር፣
ኢትዮጵያችን እንደአሁን የተማረው የሚሸሻት ሳይሆን የወጣው የሚመለስባት አገር ትሆን ነበር፣
የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሓት መጫወቻ፤ የአገሪቱ ሀብት ደግሞ የሹማምንቱ መድለቢያ ባልሆነ ነበር፣
የዘር ፓለቲካ መንግሥታዊ ፓሊሲ ሆኖ እርስ በርሳችን መግባባት እስከሚያቅተን ድረስ ለራሳችን ወንድሞችና እህቶች ባዕዶች ባልሆንም ነበር፣
ገበሬው ከማሳው ባልተፈናቀለ፤ በድህነት፣ በስደተኛና በእስረኛ ብዛት ብዛት ዓለምን መምራታችን ይቀርልን ነበር፣
በሀገራችንም በውጭ አገራትም ወጣቶቻችን አንገታቸውን ቀና፣ ደረታቸውን ነፋ አድርገው በሄዱ ነበር፤ እህቶቻችን በአረብ ጎረምሶች ከሚደርስባቸው ስቃይ በተገላገሉ ነበር፣
አገሪቱን የሚመሯት እኛው ፈልገንና ፈቅደን የመረጥናቸው፤ ካልተስማሙን የምንሽራቸው፤ የምናከብራቸው እንጂ የማንፈራቸው፤ በፓሊስና በወታደር የማያስደበድቡን “የኛ” የምንላቸው ሰዎች በሆኑ ነበር፣
ሌሎችም ብዙ መልካም ነገሮችን ባየን ነበር፣
ምልከታ ባለፈው መቆጨት መልካም የሚሆነው ለወደፊቱ ምልከታ ሲያገለግል ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ በፍጥነት እንዲመጣ የወጣቱ ተሳትፎ አሁን ካለበት በጣም መጨመር ይኖርበታል። ይህን ማድረግ ደግሞ ይቻላል፤ ወጣቱ፣ አቅም፣ ችሎታውና ተነሳሽነቱ አለው። ወጣቱ በራሱና በአገሩ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ አዎንታዊ ሚና እንዲኖረው በራሱ ላይ ያለውን መተማመን ማዳበር ይኖርበታል፤ አፈናን በሚሰብር መልኩ ራሱን ማደራጀት ይጠበቅበታል። እንዲህ በተጠና መንገድ የሚንቀሳቀስ ከሆነ ትናንንሽ የሚመስሉ ጥረቶች ተብላልተው ትልቅ ሕዝባዊ ማዕበልን መፍጠር ይችላሉ። ይህንን ትግል አሁን በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ በተለያዩ ስልቶች በሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ድርጅቶች ውስጥ በአመራር ጭምር በመሳተፍ ሊደረግ ይችላል። ይህ በማይመችበት ጊዜ ደግሞ የተለያዩ የአደረጃጀት ስልቶችን መጠቀም ይገባል።
የኢትዮጵያ ወጣት ሁሉ አንድ ዓይነት አመለካከት ወይም የተቀራረበ አመለካከት ይኖረዋል የሚል ብዥታ የለብኝም። ሆኖም ግን ከዚህ በታች ያለው ጽሁፍ የሚያተኩረው ተስፋው በህወሓት የተነጠቀው አብዛኛውን ወጣት እያሰብኩ ነው።
የኢትዮጵያ ወጣትን ትግል ለማገዝ ሶስቱ የመዳረሻ (tipping point) ህግጋትን በሚገባ መረዳት እና በሥራ ላይ ማዋል ይጠቅማል ብዬ አምናለሁ። ሶስቱ የመዳረሻዎች ህግጋት (1) የአናሳዎች ህግ (Law of the Few)፣ (2) መጣበቅ (Stickiness Factor) እና (3) የሁኔታዎች ህግ (The Law of Context) ናቸው።
የአናሳዎች ህግ፣ በሚገባ የተደራጁ ጥቂት ሰዎች ትልቅ ሕዝባዊ ማዕበልን ማስነሳት ይችላሉ የሚለው መርህ ነው። ይህ በማኔጅመንት ውስጥ “መርህ 80/20″ (The 80/20 Principle) ከሚባለው ጋር ይዛመዳል። ለምሳሌ በ 20% ጥረት 80% ውጤት እንደሚገኘው ማለት ነው። በአንድ የሥራ ቦታ 100 ሠራተኞች ቢኖሩ አብዛኛውን ጊዜ 80% ያህሉ የሥራ ሸክምና ኃላፊነት የሚወድቀው ከ 20 ባልበለጡ ሠራተኞች ላይ ነው። እነዚህ 20 ለይቶ ማወቅ፣ መሸለም፣ ማሰልጠንና ማበረታታት የጥሩ ማኔጀር ሥራ ነው። በማኅበራዊ ንቅናቄዎችም እንደዚሁ ነው። ጥቂቶች ናቸው ወሳኙን ሥራ የሚሰሩት – ወሳኝ ጥቂት ሰዎች (the vital few).
ከእነዚህ ጥቂት ሰዎች መካከል በወጣቱና በማኅበረሰቡ ተሰሚነት ያገኙ፤ ሲናገሩ የሚደመጡ፤ ንቅናቄውን ወደ በጎ ነገር ይመሩታል ብለው ተከታዮቻቸው እምነት የሚጥሉባቸው “አውራዎች” ወይም የኔታዎች (Mavens) ያስፈልጋሉ። በእድሜ ከወጣትነት የዘለሉ ዜጎች አንዱ ገንቢ ሚና ይህንን ቦታ መሙላት ነው። ሌላው እጅግ አስፈላጊ ነገር የግኑኝነት መረብ (Network) መዘርጋት ነው። እያንዳንዱ የትግሉ ተሳታፊ ከበርካታ ሰዎች ጋር በመገናኘት አድማሱን ማስፋት ይገባል። ግኑኝነት ለመፍጠር ወጣቱ የሚወዳቸውንና የሚያዘወትርባቸው መስኮች ማወቅና አክብሮት ለሚገባቸው አክብሮት መስጠት ያስፈልጋል። ስፓርት፣ ኪነ ጥበብ፣ የእምነት ተቋማት፣ ት/ቤቶች … ሊዳሰሱ ይገባል። አንዳንድ ወጣቶች በተፈጥሮዓቸው ብዙ ኔትዎርክ አላቸው። እንዲህ ዓይነቶቹን ወጣቶች የንቅናቄው አካል ማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው፤ ያለ ብዙ ድካም ወጣቱን የማገናኘቱን ሥራ ያቀላጥፉታል። በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ የቀስቃሾች መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው። ቀስቃሾች ንግግርን፣ ሙዚቃን፣ ስዕልን … ወዘተ በመጠቀም ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ ሕዝብን በአንድ መስመር ውስጥ ማስገባት ዋነኛው ሥራቸው መሆን ይኖርበታል።
መሰብሰብ ወንጀል በሆነበት አገር እነዚህ ‘ጥቂቶች’ እንዴት ይገናኛሉ? እንዴትስ ይደራጃሉ?” የሚል ጥያቄ እንደሚነሳ እገምታለሁ። ስለወጣት ድርጅቶች ስናስብ በሃሳባችን መምጣት ያለባቸው አባላትን መዝግበው፣ መዋቅር አዘጋጅተው ተመዝግበውም ሆነ ሳይመዘገቡ የሚሠሩ መደበኛ ድርጅቶችን ብቻ አይደለም። አፈና በበዛበት ሥርዓት ውስጥ ኢመደበኛ ድርጅቶች (informal organisations) ከመደበኛዎቹ የተሻለ ሊያገለግሉ ይችላሉ። የስፓርት ቡድን ደጋፊዎች፣ የመፃህፍት አፍቃሪያን ስብስቦች፣ የአገርህን እወቅ ክበባት፣ የአካባቢ ጥበቃ ማኅበራት፣ የቴኳንዶና ማርሻል አርት ክበባት፣ የሙዚቃ ክበባት፣ የማርያም፣ የሥላሴ፣ የገብሬል … ጽዋ ማኅበራት፣ ደብተሮች፣ እርሳስና እስክሪብቶዎችን ለድሆች ተማሪዎች አሰባሳቢ ክበባት፣ በረንዳ አዳሪዎችን አልባሽ ማኅበራት፣ እቁቦችና ትናንሽ እድሮች እና የመሳሰሉት ሁሉ የመደበኛ የወጣት ድርጅት ምትክ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ።
መጣበቅ (Stickiness Factor)፤ ይህ ህግ የመልዕክቱ ይዘትና አቀራረብን የሚመለከት ነው። መልዕክቱ በቀላሉ መዳረስ ብቻ ሳይሆን ከተቀባዩ ጋር “መጣበቅ” አለበት። መልዕክት በብዛት ቢዳረስም ሆነ በተከበሩ ሰዎች አንደበት ቢነገርም እንኳን አድማጩ አዕምሮ ውስጥ የማይቀር ከሆነ ማዕበል የማስነሳት አቅም አይኖረውም። የመልዕክቱ ይዘት ደግሞ ቀላልና ግልጽ ብቻ ሳይሆን ወደሌሎች ለማዳረስም የሚያጓጓ መሆን ይኖርበታል።
ወጣቱ የትግሉን ግብ በግልጽ ቢያስቀምጥ ይጠቅማል ባይ ነኝ። መልዕክቶች አጭርና ቀላል ሆነው ወደ ተግባር የሚመሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ለምሳሌ የወጣቱ እንቅስቃሴ ዓላማ በሚከተለው አኳኋን በአጭሩ ማቅረብ ይቻላል።
ህወሓት በሕዝባዊ እምቢተኝነትና አመጽ ይወገዳል፤ ሰፊ ውክልና ያለው የሽግግር መንግሥት ይመሠረታል። የዜጎች፣ የሃይማኖቶች፣ የብሄር/ብሄረሰቦች፣ የቋንቋዎች እኩልነት ይከበራል፤ ገለልተኛ ተቋማት ተመሥርተው በሁሉም እርከኖች የመንግሥት ሥልጣን በነፃ የሕዝብ ምርጫ ይወሰናል። አዲሱ ሥርዓት ለሁላችንም የሚበጅ ስለሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጎናችን ይቁም። በተለይ የመከላከያ ሠራዊትና ፓሊስ ከሕዝብ ጋር ወግኑ፤ የኢህአዴግ አባላትም በሕዝብ ጎን በመቆም ታሪክ ስሩ።
መልዕክቶችን በምስል፣ በተረት፣ በምሳሌ፣ በቀልድ ወዘተ ማስተላለፍ መለመድ ይኖርበታል። !!
የሁኔታዎች ህግ (The Law of Context)፤ አካባቢያዊ ሁኔታዎች በእንቅስቃሴዎቻችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳላቸው ማመን ተገቢ ነው። የትግል ስትራቴጂና ስልት በአብዛኛው የሚወሰኑት በሁኔታዎች ነው። እኛ በሁኔታዎች ላይ ሙሉ ቁጥጥር የለንም። በዚህም ምክንያት ከአንድ ዓይነት የትግል ስልት ጋር “መቁረብ” በጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ወጣት መሪዎች ሁኔታዎችን እያጠኑ ተስማሚ ስትራቴጂዎችንና ስልቶችን መቀየስ መልመድ ይኖርባቸዋል። በአንዱ ቦታ የሠራው በሌላ ቦታ ላይሰራ እንደሚችል፤ የነጠረ፣ ብቸኛ የሚባል ስትራቴጂ እንደሌለ መገንዘብ ይጠቅማል።
አጣዳፊ ሥራዎች
ሁሉንም ሥራዎች በአንድ ጊዜ መፈፀም የማንችል በመሆኑ ቅደም ተከተል ማውጣት ግድ ነው። በኔ ግምት አሁን የለውጥ ዋዜማ ውስጥ እንገኛለን። በዚህ ወቅት በስፋት መሠራት ያለባቸው ሁለት ነገሮች ወጣቶችን ማንቃትና ለለውጥ ማዘጋጀት እና ኔትዎርኮችን ማስፋት ናቸው። በሌላ አነጋገር መቀስቀስ እና ማደራጀት የወቅቱ ሁለት አጣዳፊ ሥራዎች ናቸው።
ወጣቱን ለመቅስቀስ ያሉት የመቀስቀሻ መሣሪያዎችን ሁሉ – ቴሌቪዥን፣ ሬድቶ፣ ጋዜጣ፣ ማኅበራዊ ሚዲያዎች፣ በራሪ ጽሁፎች፣ ስብሰባዎች፣ የሰው ከሰው ንግግሮች እና ሌሎችም መንገዶች ሁሉ መጠቀም አለብን። ለማደራጀት ደግሞ ከላይ እንደተገለፀው መደበኛ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን ኢመደበኛ ድርጅቶችን መጠቀም መልመድ አለብን።
ከኢትዮጵያ ወጣት 10% እንኳን በዚህ ሁኔታ ቢዘጋጅ የህወሓት አገዛዝ ሊሰነብት አይችልም፤ ይህ ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊፈፀም የሚችል ነው።
የ9ኝ ፓርቲዎች ትብብር በ15 ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ
‹‹ነጻነትለፍትሃዊምርጫ›› በሚል መርህ የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የካቲት 22 ቀን 2007 ዓም በ15 ከተሞች እንደሚካሄድ ትብብሩ አስታውቋል። የሙስሊም ማህበረሰቡ ታህሳስ 10፣ 2007 ዓም በኑር መስጂድ ….
የካቲት 6፣ 2007 ዓም ደግሞ በአንዋር መስኪድ ያደረገው ተቃውሞ እንዲሁም የባህርዳር ከተማ ህዝብ ታህሳስ 10፣ 2007 ዓም ያሳየው ህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል በሃይል ሊዳፈን ቢችልም እንደማይጠፋ ትምህርት ሰጥቷል የሚለው የትብብሩ መግለጫ፣ ገዢው ፓርቲ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፣ የሙስና መስፋፋትና የመልካም አስተዳደር እጦት የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት እንዳሳደገው ገልጿል። ትብብሩ ገዢው ፓርቲ ለመድብለ ፓርቲ ስርአት ግንባታ ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት እንደሌለው በመግለጽ፣ ምርጫ ቦርድን በቁጥጥር ስር በማዋል ጠንካራ ፓርቲዎችን ከመጪው ምርጫ ለማግለል እየሰራ መሆኑን የአንድነትና መኢአድን ጉዳይ በመግለጽ አብራርታል። ከሰሞኑ ኢቢሲ ያቀረበው የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የመኖር ትርጉም ዋጋ የሚያሳጣው ‹‹መንግስትንና የመንግስት አስፈጻሚዎችን ከተቻችሁ፣ ካላከበራችሁ ወይም ጸጥ ለጥ ብላችሁ የምርጫ አጃቢ ካልሆናችሁ እስከ 15 ዓመት ትታሰራላችሁ›› የሚል አንድምታ ያለው በ ‹‹ባለሙያዎች ትንታኔ ›› ሥም የተላከው የማስፈራሪያ መልዕክትና የሌሉ የፈጠራ ክሶችን ለመፈብረክ በአባል ፓርቲዎቻችን ላይ ‹‹የሞተ ጉዳይን ከመቃብር በመቀስቀስ›› እና በአዲስ መልክ የተጀመረው የሚዲያ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በግልጽ ያስተላለፈው ገዢው ፓርቲ የመድብለ ፓርቲ ስርአት እንዳይኖር መፈለጉን ነው ሲል አክሏል።
የእኛ፣ የአገራችንና ዜጓቿ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሁለት አማራጮች ላይ የተንጠለጠለ ነው የሚለው ትብብሩ አንድም ያለውን አምባገነናዊ ሥርዓት ተቀብለን፣የአገራችን ሉዓላዊነት በጥያቄ ውስጥ ባለበት፣ የጭቆና ቀንበር ተሸክመን በከፋ ውርደት ሥር ሰጥ- ለጥ ብሎ መገዛት፤ አሊያም– አምባገነንነትና ጭቆናን ‹‹በቃ›› በማለት በሕዝባዊ የተቀናጀ ሰላማዊ ትግል ለአገራችን ሉዓላዊነትና የዜግነት ክብራችንን ለማስመለስ በህገ መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን ትግላችንን እስከማይቀረው ለውጥ/ ድል ደጃፍ ድረስ በቆራጥነት መቀጠል፣ ናቸው ብሎአል፡፡
ሁሉን አቀፍ የነጻነትና ክብርን የማስመለስ ሰላማዊ ትግል ለ9ኙ ፓርቲዎች ብቸኛ አማራጭ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ፓርቲዎቹ በመጨረሻም በሚደረገው አገራዊ፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል በማይቀረው የሥርዓት ለውጥ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በአንድነትና በቆራጥነት ህዝቡ እንዲነሳና በየካቲት 22 የተቃውሞ ሰልፍ ላይ እንዲገኝ በመግለጫቸው ጥሪ አቅርበዋል።
አምባገነን ብሔር የለውም!! (አሌክስ አብርሃም)
ሰሞኑን የህወሃት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመላው ኢትዮጲያ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በቅድሚያ እንኳን ለአርባኛው አመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ እላለሁ ፡፡ በትጥቅ ትግሉም ወቅት ሆነ ከትጥቅ ትግሉ በኋላ ይህን ቀን ለማየት ሳይታደሉ ያለፉ ብዙዎች ናቸውና ምንም ይሁን ምን ለዚህ ቀን መብቃት ትልቅ ነገር እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡ ይህን ፅሁፍ የምፅፈው በተወለድኩባት ባደኩባትና አሁንም እየኖርኩባት ባለችው ኢትዮጲያ ከተመሰረተ ድፍን 40 ዓመት ያስቆጠረ ጎልማሳ የፖለቲካ ድርጅት ላይ እንደአንድ ዜጋ ያለኝን ቅሬታ ለማሳወቅ ነው ..
ሰሞኑን የድርጅቱን 40ኛ ዓመት በዓል በቴሌቪዥን በሬዲዮ እንዲሁም ከመሃበራዊ ድረ ገፆች ላይ ስመለከት እንዲሁም አገሪቱ ላይ ያለውን ተጨባጭ ችግር ስታዘብ ሳልፈልገው አእምሮየ ታሪክ እየመዘዘ ይሞግተኛል ፡፡ ባጭሩ ይህ በዓል በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ምን ያህል ነው ብየ ሳስብ ከግራና ቀኝ ከህዝቡ የሚሰነዘረውን ትችት አስተያየትና ምሬት ስመለከት በዓሉን ለብቻችሁ እያከበራችሁት ነው የሚል ስጋት ፈጥሮብኛል ፡፡
ምንም እንኳን የህወሃት የትጥቅ ትግል የዛሬው የህወሃት ቀንደኛ ጠላት ሻእቢያን ጨምሮ በከፈሉት መስዋእትነት ባደረጉት ተጋድሎ አገራችንን ከደርግ አሰቃቂ አገዛዝ የታደጋት መሆኑን ሁሉም ኢትዮጲያዊ ቢያውቅም ከነፃነቱ በኋላ ግን ስርዓቱ በሚከተለው ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስመር ከፍ ያለ ቅሬታ አለው ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ህዝቡ የትም ሂዱ የት ይማረራል … መቸም ይሄ ሁሉ ህዝብ የሚማረረው የኢትዮጲያ ህዝብ ምስጋና የማያውቅ ስለሆነ አይመስለኝም ፡፡ እንደውም ከእግዜር ጀምሮ እስከአምባገነን መሪወቹ ድረስ ራቱን በልቶ ባደረ ቁጥር ከእልፍ ችግሩ ጋር ተጠቅልሎ በሚተኛባት መደብ ‹‹ተመስገን›› ብሎ የሚያድር ህዝብ እንደኢትዮጲያ ህዝብ ያለ አይመስለኝም ፡፡ ግን …… ብሶት ህወሃትን እንደወለደ ሁሉ አሁንም ተማራሪ ህዝብ እየፈለፈለ ምድሩን እየሞላው ነው ፡፡ እናንተም ለህዝብ ብሶትና ጥያቄ ጅራትና ቀንድ እየቀጠላችሁ ተናጋሪውን ሁሉ ባልሆነ መንገድ በመፈረጅ ከማሳቀቃችሁም በላይ የዝሆን ጆሮ ይስጠን እንዳላችሁ ይሄው ድፍን 40 ዓመት ፡፡
በእርግጥ በቴሌቪዥንም ሆነ በአካል ለህዝብ ንግግር ማድረግ ቀላል ነው … ከባዱ ከህዝብ ጋር መነጋገር ነው ፡፡ ይሁንና ንግግር ማድረግም ቢሆን ቀላልነቱ ለሚናገሩባት ቅፅበት እንጅ ሲቆይ ወደሰማይ እንደወረወሩት ድንጋይ ተመልሶ አናት ላይ መስፈሩ አይቀርም ፡፡አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው ፡፡ የተገባው ቃል ሁሉ ስንዝር አልተራመደም ፡፡ በርካታ የልማት ስራዎች ተሰርተዋል መንገድ የጤና እና የትምህርት ተቋማት ግንባታ ግድቦች ዩኒቨርስቲዎች እነዚህ ሁሉ እናተም በተደጋጋሚ እንዲነገርላችሁ የምትፈልጓቸው ስኬቶች ናቸው ፡፡ ይሁንና ህዝብ ያልተሟላለትን ነገር ሲናገር የተሰራለትን እንደካደ አድርጎ ማሰብ ትልቁ የአረዳድ ችግራችሁ ነው ፡፡ ሰው ኑሮ ተወደደብኝ ብሎ ሲያማርር ኑሮ የሚቃለልበት መንገድ ላይ መስራት ብቻ ነው መልሱ ሊሆን የሚችለው ! …‹‹ አይ ኑሮ ቢወደድብህም ዩኒቨርስቲ ግን ሰርተንልሃል›› የሚል ምላሽ መቸም ህዝብን ሊያረካ አይችልም !! አሁን እየሆነ ያለው ግን ይህ ነው ! ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ማስፈራሪያ ዛቻ እንዲሁም የተወሰኑ ሰዎችን ከህዝቡ እየመዘዙ ለብዙሃኑ ችግረኛ እንቆቅልሽ ማለትና የህዝቡን ቅሬታ ማድበስበስ የተለመደ የገዥው ፓርቲ ስራ ሁኗል ፡፡
በተለይም ኢቲቪ (ኢቢኤስ ) ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ›› በማለት የሚያቀርባቸው ሰዎች ግራ እያጋቡን ነው ! እስቲ ኑሮ ተወዶብናል ስንል እነዚህ ‹‹አንዳንዶች ›› ኑሮ አልተወደደም የሚል በደፈናው ይዘው ህዝቡን ማበሳጨት ምን ይጠቅማል ?ለማንስ ነው የሚመሰክሩት …መብራት ጠፋብን ስንል አንዳንዶቹ ‹‹ኧረ በጭራሽ›› ይሉናል ፡፡ አንዳንዶች ብዙሃኑን ‹‹ውሸታም ነህ ›› ይሉታል ፡፡ይሄ ህዝብን መናቅ ነው …እንደውም በኑሮ ውድነት ከሚሰቃየው ህዝብ በመሰረተ ልማት አውታሮች እጥረት ፍዳውን ከሚበላው ህዝብ የሚፈጠሩ ህፃናት ወደፊት
‹‹ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ›› ሲባሉ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን መሆን እንፈልጋለን ›› እንዳይሉ እሰጋለሁ ፡፡ ….በአሁኑ ሰዓት ያለምንም ምሬት በተድላ እንደሚኖሩና ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ እንደሆነ የሚመሰክሩ ኢትዮጲያዊያን ቢኖሩ እነዚሁ ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች›› ብቻ ናቸውና ምኞቱ እንዲህ ቢሆን አይገርምም ፡፡ ብሄራዊ ቴሌቪዥናችን ‹‹ራበን ›› ብሎ ሰልፍ ለወጣው ህዝብ ‹‹ለምን ኬክ አይበሉም ›› እንዳለችው ልእልት ሁኖብናል ፡፡ ስራ አጣን ስንል ቴሌቪዥናችን ለምን ስራ አትፈጥሩም ይለናል …ኑሮ ለማሻሻል ተሰደድን ስንል …አይ ጥጋብ ፈንቅሏችሁ እንጅ አገራችን ማሩ ወተቱ ይለናል …እንኳን ማርና ወተት የግዜሩንም ውሃ በስንት ጉድ ጥበቃ እንደማንዳረስ ሁሉ !
ችግሩ ይሄ ብቻ አይደለም በመልካም አስተዳደር ላይ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግር ውስጥ ነን ፡፡ ሙስና ቁጥር አንድ ጠላታችን ሁኗል …ሙስና ደግሞ በባህሪው ስልጣናቸውን ገንዘብ ላለው ሰው የሚያከራዩ ባለስልጣናትና የስራ ሃላፊዎች ዘንድ የሚፈጠር አደገኛ ተግባር ነው ፡፡ መንግስት ህዝቡን ጠቁም አትጠቁም ጨዋታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ‹‹ደህንነት›› ተብሎ ለአገር ደህንነት ሲባል ጓዳ ጎድጓዳውን እሰልላለሁ እንደሚለው የመንግስት አካል በዚህም ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ‹‹የደህንነት አካል ›› ቢቋቋምና መዘረፋችን ባይቆም እንኳን አሟጠው እንዳይነጥቁን ሃይ ቢባሉ መልካም ነው ፡፡መቸም ሚስኪን ፀሃፊና ጋዜጠኞችን ከማሳደድ ይሄ የተሸለ ስራ ይመስለኛል ፡፡
ሌላው የህወሃት አስጊ ችግር በብሔሮች መሃል የፈጠረውና አሁንም እየፈጠረው ያለው ቁርሾ ነው ፡፡ በተለይ በትግራይ ህዝብና በሌላው ኢትዮጲያዊ መካከል …በተደጋጋሚ ህወሃት በጉድለቶቹ ሲወቀስ የራሱን ችግርና በድርጅቱ ላይ የሚሰነዘረውን ጥላቻም ይሁን ነቀፋ በትግራይ ህዝብ ላይ እንደተሰነዘረ በማስመሰል የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ የሚያደርገው ጥረት በተደጋጋሚ የሚታይ የአደባባይ ሚስጥር ነው !! ይህ ነገር የትግራይን ህዝብ ከእህትና ወንድሞቹ ጋር እያቃቃረው ከስርአቱ ልዩ ተጠቃሚ የሆነ እያስመሰለው ይገኛል ፡፡ የትግራይ ህዝብ በህወሃት የስልጣን ዘመን ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ የተለየ ተጠቃሚ ሁኗል አልሆነም የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ እንደሆነ አለ !!
ይህን ያልኩበት ምክንያት ደግሞ ህወሃት እራሱ እንደሚለው ኢፈርት ወይም ትእምት እጅግ በጣም ግዙፍ እና በኢትዮጲያ ውስጥ( አንዳንዶች እንደውም በአፍሪካም ይላሉ) በሀብት የሚወዳደረው የሌለ የንግድ ተቋም ነው ፡፡ ባለቤትነቱ ደግሞ በተለይ እንደተቀመጠው የትግራይ ህዝብ ነው ! እንግዲህ ይህን የሚያክል ትልቅ ተቋም በስሩ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፋብሪካዎች የማእድን ማውጫወች የኮንስትራክሽን ተቋማት የትራንስፖርት ድርጅቶች የእርሻ ድርጅቶች ያሉት ባለፀጋ ድርጅት ባለቤቱ የትግራይ ህዝብ ነው ከተባለና በትክክል ለትግራይ ህዝብ ገንዘቡ ከዋለ የትግራይ ህዝብ በደንብ ተጠቃሚ ነው ለማለት ያስደፍራል !! ይሁንና እዚሁ ፌስቡክ ላይ የኢፈርት ነገር ላም አለኝ በሰማይ ነው እንደሚሉን በርካታ የትግይ ወንድሞቻችን አባባል ከሆነ ግን የትግራይ ህዝብ በተለይ ከስልጣኑም ከበረከቱም የሌለበት ሚስኪን ነዋሪ ያው እንደሁሉም ኢትዮጲያዊ ነው !!
ዋናው ነገር ተጠቀሙም አልተጠቀሙም አሁን ባለው በርካታ ኢትዮጲያዊ አመለካከት በተለያየ መንገድ እንደምንሰማውም ህወሃትና የትግራይን ህዝብ አዳብሎ የማየት ነገር ጎልቶ ይታያል ፡፡ ህወሃትም ቢሆን የትግራይ ህዝብና ህወሃት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው አይነት ዳርዳርታ ማብዛቱ በቀሪው የኢትዮጲያ ህዝብ ልብ ውስጥ ጥሩ ነገር ይፈጥራል የሚል እምነት የለኝም ! ህወሃት የፖለቲካ ድርጅት ነው ሊጠላም ሊወደስም ይችላል፡፡ እራሱን ችሎ መቆምና ከህዝብ የሚሰነዘርበትን ጥላቻም ሙገሳም ህዝቦችን ሳያነካካ መቀበል ይኖርበታል ፡፡ መልካም አስተዳደር ያሰፈነ ገዥ ፓርቲ የዚህኛው ብሔር የዛንኛው ዘር ነው አይባልም ጥሩ ድርጅት የሚያስተዳድረው ሃገር ድርጅት ነው !! አምባገነን እና ፀረ ህዝብ መንግስት ግን ከማንም ይጠጋ በማንም ይጠለል ህዝባዊ አይደለምና ብሔር የለውም !! አዎ የመላውን የሰው ልጆች ነፃነት ሰበዓዊና ዲሞክራሲ መብት ገፋፊ ከሆነ አምባገነን ብሄር የለውም!!
ይሄ ህወሃትን የነካ የትግራይን ህዝብ ነካ ጨዋታ በ1993 እና 1997 ላይ በተለይ በአዲስ አበባ የተከሰቱትን ተቃውሞች ላይ ነህዝቦች መካከለል አስነስቶ የነበረውን ተገቢ ያልሆነ መዘዝ በማየት ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መታዘብ ይቻላል ፡፡ ያ ጊዜ የዚህ የጥላቻ ዘር ውጤት ፈጦ የታየበት ነበር ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂው ህወሃት ነው !! ለምን ቢባል በህዝቦቹ መካከል ወንድማማችነትን ለማጎልበት በቂ ስራ አልሰራም … (ፍላጎቱም ያለው አይመስልም) በመንግስት ስራ ውስጥም ሆነ በሌሎች ስራዎች የተሰማሩ አንዳንድ የአካባቢው ተወላጆች የትጥቅ ትግሉን ታሪክ የግል ጀብዷቸው ብቻ አድርገው ሲደነፉና ስለታገሉ ብቻ ልዩ ተጠቃሚ የመሆን መብት እንዳላቸው በተለያየ መንገድ ሲጠቅሱ መንግስት መስመር ለማስያዝ ያደረገው ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም !!
አንዳንዴ እኮ ተራ መጠጥ ቤት ውስጥ ሳይቀር በሚነሳ አምባጓሮ ‹‹ደሜን አፍስሸ ባቀናኋት አገር ›› የሚላችሁ እንጩጭ ብሔረተኛ ያጋጥማችኋል ፡፡ እዚህ ፌስቡክ ላይ በፀያፍ ስድብ ታሪክና ታላላቅ ሰዎችን በማጠልሸት ከእኛ በላይ አዋቂ የለም በማለትና አሳዛኝ ድርጊቶችን በመፈፀም የሚታወቁትም ተመሳሳይ ሰዎች ናቸው !! ይህ ከተጋነነ እውቀት ላይ ሳይሆን ትእቢት ላይ ከተመረኮዘ መጥፎ በራስ መተማመን የሚፈጠር በሽታ ከእኔ በላይ ላሳር የሚያስብላቸው እነዚሁ ሰዎች ናቸው !!
ለዚች አገር መሳሪያ አንስቶ የተዋጋው ብቻ ሳይሆን ግንበኛውም ሃኪሙም አስተማሪውም ላቡን አፍስሶላታል !! አበቃ !! ማንም ስለታገለ ደሙን ስላፈሰሰ ለህዝብ ነፃነት በጎ ነገር እንዳደረገ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንደተወጣ ያስብ እንጅ ለፈሰሰ ደሙ ከኢትዮጲያ ህዝብ ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳለው ወይም ልዩ ተጠቃሚ የሚደርገው የይለፍ ወረቀት እንደያዘ አድርጎ ማሰብ ነውርም አሳፋሪ አስተሳሰብም ነው !! ሚሊየኖች እየወደቁላት እዚህ የደረሰች አገር ለሟችም ለገዳይም ነፃነትን እንጅ ካሳን የከፈለችበት ዘመን የለም ! ደሜ ለፈሰሰበት ይከፈለኝ የሚል እሳቤ ያለው ዜጋ ቅጥረኛ ወታደር እንጅ በምንም መስፈርት ጀግና ሊባልና ሊሞካሽ አይገባም !! የመስዋእትነት ክፍያው ነፃነት ብቻ ነው !! ነፃነቱም ለሁሉም ህዝብ በእኩልነት !!
መንግስት ለምን የፃፉትን ሁሉ ያስራል .. ለምን በተናገሩት ቁጥር ያኮርፋል … ዜጎቹን አኩርፎ ከውጭ አገር ሽማግሌ እስኪመጣለት አለያም አስሮ የሚያሰቃያቸው ዜጎቹ ያውም በካርዳቸው ድምፃቸውን ሰጡኝ የሚላቸው …ይቅር በለን ብለው እግሩ ስር እስኪወድቁለት የሚጠብቅ ስርዓት ምን አይነት መንግስት ሊወጣው ይችላል …ሁልጊዜ ስለመንገድ አውሩ ሁልጊዜ ስለፋሲካ ብቻ አውሩ የሚል መንግስት እንዴት የህዝብ መንግስት ሊሆን ይችላል ! መፅሄት ላይ ኮሽ ሲል በህዝብ ላብ በህዝብ ግብር በተማሩ ወታደሮችና ደህንነቶች ዜጎቹን የሚያሳፍስ ዘመድ ወዳጅ እንዳይጎበኛቸው የሚከለክል መንግስት ማንን ነው የሚመራው ….
በዚች በአርባኛ አመት በዓል ላይ የሚታየው ሌላው አሳዛኝ ነገር ደግሞ የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ በላይ ጀግና አድርጎ የማቅረቡ ነገር ነው …እውነታውን ማስቀመጥ ይኖርብናል … ደርግን ለመጣል የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጲያዊያን ወገኖቹ በላይ መስዋእትነት ከፍሏል ይሄ የማይካድ ሃቅ ነው …. ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ከሰማየ ሰማያት የተለየ ጀግንነት ስለተቸረው ሳይሆን የትጥቅ ትግሉ በወቅቱ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ በሚመች መልኩ ስላልተደራጀ ነበር ፡፡ እንጅኮ ደርግ ሲወድቅ ከአስራ ስምንት በላይ ብረት ያነሱ ተፋላሚዎች በኢትዮጲያ ነበሩ ! ቀደም ብለን ካየነውም በርካታ ኢትዮጲያዊ ደርግ አፍንጫ ስር ቁሞ በመፋለም ለህወሃት ትጥቅ ትግል መንገድ ከፍቷል …ተማሪዎች ለነፃነት ደማቸውን አፍስሰውላታል … ግለሰቦች ጨካኙን ስርአት ፊት ለፊት ተቃውመው ተሰውተዋል ….
ደግሞ በህወሃት የትጥቅ ትግል ውስጥ ‹‹አምስት ሁነው ትግሉን ጀመሩ›› የሚለው የታሪክ መነሻ አምስት ሁነው ትግሉን ጨረሱ ማለት አለመሆኑን ማወቅም ተገቢ ይመስለኛል !! ሁሉም ኢትዮጲያ አንጀቱ አሮ በየቤቱ በተቀመጠበት ሰአት እንኳን አምስት አንድ ሰውም ተከተሉኝ ቢል እልፍ ያኮበኮቡ ኢትዮጲያዊያን ስርዓቱን ለመፋለም ዝግጁ ነበሩ …. ነበሩ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት በፊት ብረት አንስተው ስርዓቱን እንቢ ያሌ ነበሩ ፡፡ ምሬት ፅዋዋ ሞልቶ ነበር ህዝብ አገዛዙን አክ እትፍ ብሎት ነበር … ህወሃት አሁን ቁጭ ብሎ ማሰብ ያለበት የሚመስለኝ አምስት ሁኖ የትጥቅ ትግሉን መጀመሩን ሳይሆን አሁን የኢትዮጲያ ህዝብ ባጠቃላይ አምስት የሚወዳቸው የሚምናቸው መሪዎች ህወሃት ውስጥ አሉ ወይ የሚለውን ነው !!
በነገራችን ላይ ህወሃት ባለፈበት ጎዳና ሁኑ መላው የኢትዮጲያ ህዝብ ከጎኑ ነበር !! የትግራይ ህዝብ ብቻው ከኢትዮጲያ ህዝብ የተለየ ጀግና ሊሆን አይችልም!! …ከወንድሞቹና ከእህቶቹ በላይ ጀብዱ እንዳለውም ማሰብ አይኖርበትም !! ይሄ እጅግ የተጋነነና የተዛነፈ እሳቤ ነው በኋላ ያልሆኑትን አድርጎ የማይገፉት ተራራ ጋር የሚያጋጨው …ሩቅ ሳንሄድ ሻእቢያ ከእኔ በላይ ጦርነት አዋቂ ከኔ በላይ ተኳሽ ላሳር ብሎ በእብሪት ከወረረን እኮ ገና አስራ አምስት አመት አልሞላውም … ይሁንና የቱንም ያህል ራሱን ጀግና ያድርግ የቱንም ያህል ራሱን ብልህና ጥበበኛ አድርጎ ያስብ ከመላው ኢትዮጲያ እንደአሸዋ የተዘረገፈው ህዝብ ነበር የከፈለውን ያህል መስዋእትነት ከፍሎ አገርን የታደጋት !! እውነቱን እናውራ ከተባለ የሻእቢያን ወረራ የትግራይ ህዝብ ብቻውን ይቋቋመው ነበር ?
መንግስት በቀረው እድሜ ሁሉ በብሔሮች መሃል በሃይማኖቶች መሃል እንዲሁም በፖለቲካ ድርጅቶች መሃል ታየም አልታየም ታወቀበትም አልታወቀበትም ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ባይኖረው መልካም ነው ፡፡ የፈለገ ቢከፋፈል ቢለያይ ገዥውን የጋራ ጥላት ያደረገ ህዝብ በአንድ ላይ መቆሙና መልሶ ችግር መሆኑ አይቀርም ! ዛሬ 40ኛ አመት በዓሉ ሲከበርም ይሄንኑ ታሳቢ ማድረጉ የሚበጅ ይመስለኛል !
ጉዳየን ስቋጭ እራሱ የህወሃት 40ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አከባበር ላይም ታሪካዊ ጥያቄ በማንሳት ነው …
1965 ዓ/ም የወሎ ህዝብ በእረሃብ ሲረግፍ ከታች ጀምሮ እስከላይ እስከንጉሱ ርሃቡን በመደበቅና በማድበስበስ ስለረሃቡ የተነፈሱትን ሁሉ በማሰር ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ የ80ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ለማክበር አዲስ አበባን በከፍተኛ ወጭ እያሽቆጠቆጧት ነበር ..የዜና አውታሮችም አገር ጥጋብ እንደሆነ ምርትም እንደተትረፈረፈ እየዘገቡ ነበር (እንዳሁኑ Ebc ) በዓሉም ሃምሌ 1965 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ ተከበረ … ይሄንና ይሄ የታፈነ ግፍና ሌላም የህዝብ በደል ተዳምሮ ንጉሱን በብርሃን ፍጥነት ከነዙፋናቸው አንኮታኮተ ኢትዮጲያንም ለሰሚው ወደሚዘገንን ወታደረዋ አገዛዝና ደም መፋሰስ ዳረጋት !!
ደርግ …በተመሳሳይ በርካታ ኢትዮጲያዊያን በተራቡበትና በእርሃብ በሚረግፉበት ወቅት የፓርቲ ምስረታ ገለመሌ በዓሉን መላዋን አዲስ አበባ በመብራትና በመፎክር አንዎጥቁጦ ሲያከብር ነበር ! ደርግም በተመሳሳይ ‹‹ጠላቶቸ …ሻእቢያ ገንይ ምናምን ከማለት ውጭ ስለውስጥ ችግሩ ትንፍሽ ሳይል ፌሽታውን አከበረ ….ዛሬስ ምን እያደረግን ነው … የእውነት ህዝባችን ፌሽታችንን ህዝባችን በዓላችንን የሚጋራበት የተረጋጋ ኢኮኖሚ ሰላም እና ዲሞክራሲ ላይ ነው …..? እንደኔ እንደኔ አዎ አገራችን በርካታ የልማትና የሰላም እምርታዎችን አስመዝግባለች ግን …በአደገኛ ሁኔታዎች ያሽቆለቆለችባቸው ሁነቶች ይበዛሉ … ስደቱ አሳሳቢ ነው …ከአገር ውጭ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ክፍለሃገራት ወደአዲስ አበባ የሚፈልሰው ህዝብ ሲታይ ‹‹እድገቱ የፈጠረው›› እያልን ማላገጡ መፍትሄ አይመስለኝም !!
አሁን ያለው የህዝብ ብሶት ቢዘረዘር ማለቂያ የለውም ግን ህወሃትን እንደአንድ ዜጋ የምጠይቀው …ቅን ብልህና ከቂምና በቀል የፀዳ ስርዓት ለመገንባት ይነሳ … በገፍ እየጓፈፈ በየምክንያቱ በየእስር ቤቱ ያጎራቸውን ጋዜጠኞች ጦማሪያን ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት አባላትና የሃይማኖት ሰዎችን ይፍታ ! መንግስት እንኳን ውሃ ቀጠነ ብሎ ያሰራቸውን ንፁሃን ቀርቶ በብዙ ጥፋት ውስጥ ያለፉ የህግ ታራሚዎችን በምህረት መልቀቁ ህዝባዊነት ሰበአዊነት ነው !! አዎ ‹‹ 40ኛ አመት የምስረታ በዓሉ ግማሹን አስሮ ግማሹን አስጨፍሮ ›› ሊሆን አይገባም !! ከየትኛውም ድግስ ከየትኛውም ጭፈራና ንግግር በላይ ሁሉም ኢትዮጲያዊ ከህወሃት ኢህአዴግ የሚጠብቀው መሰረታዊ የአገሪቱ ችግሮች ያለምንም ምክንያት ድርደራ እንዲፈቱለት እንዲሁም ሃሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ የተለያየ ስም ተለጥፎባቸው ያታሰሩ ልጆቹን ጓደኞቹን የስራ ባልደረቦቹንና ወንድምና እህቶቹን እንዲፈታለት ነው !!
Breaking News (በዛሬው ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ በወያኔ ኤንባሲ ፊት ለፊትባንዲራ(የወያኔ መለያ) ተቃጠለ)
ምርጫ ቦርድ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ሰረዘ
‹ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ እንዲቆይ አይፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ እንደተሰረዙበት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ…
፡ ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በጋሞጎፋ፣ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ጎንደርና ጉጅን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ አንድን ዕጩ ለመሰረዝ የሚያበቃ ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር ‹‹ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ታዘናል›› በማለት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለክልል ምክር ቤቶች ያስመዘገብናቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎቹን በመሰረዝ ከምርጫው ውድድር ውጪ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡
በየክፍለ ሀገሩ የተሰረዙት ዕጩዎች ‹‹ፓርቲው ትብብር የሚባል ህገ ወጥ አደረጃጀት መስርቷል፣ የሌሎች ፓርቲዎች አባላት ናችሁ›› የመሳሰሉ ምክንያቶችና ደብዳቤ የተሰጣቸው ሲሆን በአንጻሩ በአዲስ አበባ የተሰረዙት ዕጩዎች ከምርጫ አስፈጻሚዎች ምንም አይነት ምክንያትና ደብዳቤ እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዕጩዎቹ ‹‹የተሰረዝንበትን ምክንያት ንገሩን፣ ደብዳቤ ልትሰጡን ይገባል›› ቢሉም የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ‹‹እኛ እናንተን ለመመዝገብ ችግር የለብንም፡፡ ግን ከበላይ አካል እንዳንመዘግብ ተነግሮናል፡፡ ደብዳቤም ልንሰጣችሁ አንችልም፡፡›› የሚል መልስ እንደሰጧው ተግልጾአል፡፡
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች መሰረዛቸውን ተከትሎ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የቦርዱን ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃናን ለማግኘት ቢጥሩም ‹‹ከከተማ ውጭ ናቸው፡፡ አሁን አታገኟቸውም›› የተባሉ ሲሆን ፕ/ር መርጋ የህወሓትን 40ኛ አመት ለማክበር መቀሌ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በትናንትናው ዕለት በጉዳዩ ላይ ከቦርዱ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጋ ዱፌሳ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን አቶ ነጋ ‹‹ማመልከቻ አስገቡ›› ከማለት ውጭ ዕጩዎቹ ለመሰረዛቸው ተጨባጭ ምክንያት መስጠት እንዳልቻሉ ኢ/ር ይልቃል ገልጸውልናል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ያለ አግባብ የሚሰርዙት ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ ጫና መፍጠር ስለሚችል በሂደቱ እንዲቆ ስለማይፈልጉ ነው›› ያሉት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፤ ሆኖም ይህ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ለነጻነት የሚያደርጉትን ትግል ትክክለኛ እንደሆነ እንዳስረገጠላቸው፣ ይህን የነጻነት ትግልም አጠናክረው እንደሚቀጥሉና የካቲት 22 ፓርቲያቸው ከትብብሩ ፓርቲዎች ጋር በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ በ15 ከተሞች የሚያደርገው ሰልፍ የዚሁ የነጻነት ትግል አካል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡
ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች ጥፋተኞች አይደለንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡
ፍ/ቤቱም የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ካደመጠ በኋላ የሚቀጥለውን ቀጠሮ ለመጋቢት 21-23 ሠጥቶ ተበትኗል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ የተመሰረተባቸው ጥር 28 ቀን 2007 ሲሆን ተከሳሾቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት እድል ያገኙት ግን በዛሬው ዕለት ነው፡፡
በተያያዘ ዜና የመሀል ዳኛው የነበሩት አቶ ሸለመ በቀለ ተከሳሾቹ ይቀየሩልን ባሉት መሰረት ሐሙስ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ራሳቸውን በፈቃደኝነት ከችሎቱ ያገለሉ ቢሆንም በዛሬው ችሎት ላይ ግን ቀርበው እንደነበር በፍርድ ቤት ጉዳዩን የተከታተሉት የተከሳሽ ጓደኞችና ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡
የዛሬ የቂሊንጦ አጭር ቆይታ አብርሃን መጠየቅ ከጀርባ ሰው ያስከትላል (ከኤልያስ ገብሩ ጎዳና )
‹‹ዕድሜያችንን መቼ ሰራንበት፣ ልደት ማክበርም ያስፈራኛል፡፡
እንኳን ተወለድክ ላላችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ›› ( ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ)
ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ከወዳጄ አቤል አለማየሁ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አምርተን ነበር፡፡ አካሄዳችን በዞን ሁለት የሚገኙትን አብርሃ ደስታን፣ ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉንና ጦማሪ አጥናፍ ብርሃንን ለመጠየቅ ነው…
…
የቃሊቲ እና የቂሊንጦ ጸሐይ ከረር ያለች ብትሆንም በቦታው ደርሰን ወደፖሊሶች ለምዝገባ ተጠጋን፡፡ ጠያቂና ተጠያቂ መዝጋቢ የሆነችው ሴት ፖሊስ ‹‹ማንን ነው የምትጠይቀው?›› ብላ አቤልን ጠየቀችው፡፡ በፍቃዱን እና አጥናፍን መሆንኑ ነገራት፡፡ መዘገበችውና ሂድ አለችው፡፡ ‹‹አንተስ ማንን ነው?›› ስትል ጠየቀችኝ፤ ‹‹አብርሃ ደስታን›› አልኳት፡፡ ቀና ብላ አየችኝና ‹‹ቆይ፣ ቁጭ በል›› የሚል መልስ መለሰች፡፡ ሌሎች ሰዎችን መመዝገቧን ቀጠለች፡፡ ‹‹ሰዓት እየሄደ ነው፣ ችግር አለ ወይ?›› አልኳት፡፡ ‹‹አይ ችግር የለም›› ካለች ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ሌላ መዝገብ አምጥታ ፓስፖርቴን መዘገበችው፡፡ (መታወቂያዬ አልታደሰም) ከመዘገበች በኋላም ሌላ የፎርም መሙያ አውጥጣ በድጋሚ መዘገበች፡፡ ይሄንን ስትመዘግብ እኔ እንዳይባት ስላልፈለገች ስትደብቀው አስተውያታለሁ፡፡ከሌላ ወንድ ፖሊስ ጋር ከተነጋገረች በኋላ ግባ አለችኝ፡፡
የጸሐይ መነጽር ማውለቅ ግድ ነበር፡፡ ያው ፍተሻውን አልፌ ወደዞን ሁለት አመራሁ፡፡ ከኋላዬ አንድ ሲቪል የለበሰ ወንድ በቅርብ ርቀት እየተከተለኝ ነበር፡፡ አብርሃን አስጠራሁት፡፡ ከኋላዬ የሚከተለኝ ሰው ከጎኔ ሆኖ ሌሎች ጠያቂዎችን ለመጠየቅ ማስመሰል ሞከረ፡፡ በውስጤ ፈገግ መጣ፡፡
አስተናባሪዎቹ ‹‹አብርሃ እዚህ የለም፤ የዞን ሁለት መጠየቂያ ተቀይሯል›› አሉኝ፡፡ በእርግጥም ዞን አንድ ታስሬ በነበረበት ጊዜ የማውቃቸውን እስረኞች ተመለከትኳቸውና ሰላም ተባባልን፡፡ ልወጣ ስል ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በርቀት አይቶኝ ሰላም አለኝ፡፡ በደስታ ሰላም አልኩት፡፡ ነገር ግን ተመልሼ በእጄ ሰላም እንዳልለው ያ ከጀርባዬ ያለ ሰው ነበር፡፡ ከዚህ ቀደምም ‹‹አቡበከርን ለምን ጠየከው?›› ተብዬ የተፈጠረውን ግርግር አስታወስኩኝ፡፡ አብበከርም ይሄ ስለገባው በርቀት ሰላም ብሎኝ በእጁ ሂድ አለኝ፡፡
የዞን አንድ መጠየቂያ ለዞን ሁለት ታሳሪዎች፤ የዞን ሁለት ደግሞ ለዞን አንድ ታሳሪዎች መጠየቂያ ሆኗል፡፡ አቤል በፍቄንና አጥናፍን አስጠርቷል፡፡ እኔም አብርሃን አስጠራሁ፡፡ በፍቄና አጥናፍ ወዲያው መጡ፡፡
ያ ከጀርባዬ የነበረ ሲቪል ኮፍያ ለባሽ ከጎኔ ቆሟል፡፡ ለአጥነፍ ‹‹በቃ እናንተ ከአቤል ጋር አውሩ፡፡ እኔ አብርሃን ስላጠራሁ ልጠብቀው፡፡ ከአንድ ሰው በላይ መጠየቅ አይቻልም ብለዋል›› አልኩት፡፡ አጥናፍ ከዚህ ቀደም የደረሰብኝን አስታውሶ ‹‹አብርሃ አሁን ጠበቃ ተማንን ሊያገኝ ሄዷል፤ ከጎንህ የቆመው የግቢው ደህንነት ነው፡፡ ይሄን ንገረውና እስከዚያው ከእኛ ጋር ሁን›› አለኝ፡፡ ያን ሰውዬ ትከሻውን ስነካው ደንገጥ ብሎ ዞር አለ፡፡ ስለሁኔታው ነገርኩት፡፡ ‹‹እሱ (አብርሃ) እስኪመጣ ብቻህን ተቀምጠህ ጠብቅ›› አለኝ፡፡ ‹‹እስኪዚያ እነሱን ላናግራቸው›› አልኩት፡፡ ‹‹ብቻህን ብትቀመጥ ይሻልሃል አለኝ›› ተናድጄ ወደውጪ ወጥቼ ሌሎች ፖሊሶችን ስለሁኔታው አስረዳኋቸው፡፡ ኃላፊነት የሚወስድ ጠፋ፡፡ በመጨረሻም አንዱ ፖሊስ ‹‹እሱ አስኪመጣ ውስጥ ጠብቀው›› የሚል ምላሽ ሰጠኝ፡፡ የመጣው ይምጣ በሚል ገብቼ ከበፍቄ ጋር ማውራት ጀመርኩ፡፡
‹‹በፍቄ እንኳን ተወለድክ›› አልኩት፡፡ አሜን ካለኝ በኋላ ‹‹ዕድሜያችንን መቼ ሰራንበት፡፡ ልደት አክብሬ አላውቅም፡፡ ልደት ማክበርም ያስፈራኛል፡፡ ግን እንኳን ተወለድክ ላላችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ››ሲል እየሳቀ መለሰልኝ፡፡
አቤል እና አጥናፍ ጋር የጦፈ ጨዋታ ይዘዋል፡፡ እኔም ከበፍቄ ጋር ባለችን አጭር ደቂቃ ስለሀገር ጉዳይ፣ ስለዘንድሮ ምርጫ፣ ስለአልጀዚራ ዘስትሪም የሰሞኑ ዘገባ፣ ስለ ክሳቸው እና እስራቸው ጉዳይ፣ ስለእኔ የክስ ሁኔታ፣ በአንድነት ፓርቲ ስለደረሰው ሁነትና አደጋ …በጥቂቱ አወጋን፡፡የመለያያ ደወል ተደወለ፡፡ አብርሃም ሳይመጣ ቀረ፡፡ ያው፣ ቻው ብሎ መለያየት ግድ ነበርና ተለያየን!!!
Documentary:U.S Policy:ETHIOPIA A FAILED STATE!
To our viewers that raised the concern of Oromos, it was not and it is not our intent to leave out the Oromo issues. In fact, we have been researching the Oromo issue along with the other ethnic groups…
We are well aware that Oromos are the majority ethnic group within Ethiopia and that they have been prosecuted relentlessly by the current government. The mass incarceration of Oromo students and illegal land appropriations the government has been doing, particularly in 2014, is one aspect we have been researching.
The committee for this documentary felt that it was prudent to have enough research and data analysis on the Oromo issue before it was included in the documentary. Therefore, it will be included in a second edition that we will release soon, so please bear with us and be patient.
by E – Veracity
Ethiopia is at a crossroad. The internal social-economic and religious inter-relationship is in turmoil. Much of the conflict is along ethnic lines that have been ever growing since the current government’s grasp to power. The current government in Ethiopia has been in power U.S Policy: Ethiopia a Failed State (Documentary)
“To our viewers that raised the concern of Oromos…” Please read below the video.
for a total of almost 24 years, and it is based on a single ethnic minority group. The government has made sure to control all sectors of the country with its own ethnic group. The military, religious, and economic composition has always and still continues to revolve around the Tigray ethnic group.To prolong its grasp on power, the Tigray government has been using the age-long known strategy of divide-conquer. It has pitted several ethnic groups against each other and particularly the major ethnic groups, the Amhara and Oromo. There have been several genocides, massacres, and ethnic cleansings that have taken place throughout the country, and not one individual has been held accountable for all those killings and massacres.
Political parties are not allowed to exist unless they serve the Tigray government’s interests. Private and independent Medias are not allowed to function, and those that do are intimidated and abused on a regular basis to point where they are exiled. Several hundred Journalists have been exiled and many more have been put in prison to serve decade long sentences that were based on tramped up bogus charges.
Religious tension within the Ethiopian Orthodox Tewhado is another factor where the Tigray government has practically cleared all other ethnic groups and put its own ethnic groups in control of all Church matters creating two Church leaderships. The Tigray government has also split Muslim community by illegal appointing its own Muslim leaders as opposed to those chosen by the community.
The western policy and particularly that of the U.S has been complete deliberate ignorance to promote its Al-Shabab interests. The U.S has not done anything other than give lip service to the Ethiopian people. This deliberate ignorance, however, could be costly for the U.S as Ethiopia is heading on to full-fledged failed state, and its own reports confirm this; and yet still support the Tigray government. The disintegration of Ethiopia will inevitably lead to the disintegration of the horn. Time is of the essence and the issue needs to be immediately confronted
ሰበር ዜና: ሽመልስ ከማል አሜሪካ ገባ
የኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ የመጣው በግሉ እንደሆነ አስታውቀዋል…
በዲሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ወንድሙ ዘንድ ያቀናው ሽመልስ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ለመቅረት ሃሳብ እንዳለውና እንደሚፈልግ ምንጮቹ አጋልጠዋል።
ሽመልስ ከማል – አፋኙን የፕሬስ ህግ በማርቀቅ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከህትመት ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች ላይ የሞት ቅጣት እንዲበየን በመጠየቅ፣ እነእስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት እንዲፈረድባቸው በማድረግ፣ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች እስር ቤት እንዲገቡና በሽብርተኝነት እንዲከሰሱ በማድረግ እንዲሁም ሙስሊሙንና ተቃዋሚዎችን በጅምላ በመስደብና በማንጓጠጥ፣ ብርቱካን ሚዴቅሳ ለ2 አመት በጨለማ እስር ቤት እንድትማቅቅ በመፍረድ..ወዘተ የመብት ረገጣ ያካሄደና በበርካታ ወገኖች ህይወት ላይ የጭካኔ ፍርድ ያሳለፈ እንደሆነ ይታወቃል።
አንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ
እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል…
በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡
ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን፡፡ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ስራ ሲወስን የአገራችንን የረጅም ሠላም አይተው ሣይሆን በአገዛዙ ቁንጮ ሰዎች በመታዘዝ በተቋም ስም የሚሠሩት የማደናገር የድንቁርና ተግባራቸዉ አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ማህበራችን ይህን ድርጊት እጅጉን ያወግዛል። በመሆኑም ድርጊቱን በጋራ እንቃወማለን።
በምርጫ ቦርድ ስም የተወሰነው ህገ-ወጥ ውሣኔ ምክንያት መላ የአንድነትና የመኢአድ አባላት የፖለቲካ እንቅስቃሴአቸው ተገድቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለአገራቸው ካላቸው ፅኑ ፍቅር አኳያ ትግሉን ለማስቀጠል ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የአባልነት ፎርም በመሙላት ትግሉን ቀጥለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የአባላት ቆራጥ ውሣኔ ሊበረታታና ሞራል ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን! እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሁለቱ የድጋፍ ማህበራት ሙሉ በሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡
ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአንድነትና የሠማያዊ የድጋፍ ማህበራት በጋራ በኮሜቴ ደረጃ ተዋቅረን በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ ማለትም በፋይናንስ፤ በእስረኞች ጉዳይ እና በዲኘሎማሲው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ በትብብር አብረን እየሠራን የሰማያዊ ፓርቲንና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሣኔ አሣልፈናል፡፡ በቀጣይም በጋራ የኮሚቴ ውይይቶችን እያደረግን ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስፈልጉ የሞራልና የማቴሪያል ርዳታ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡
የሰማያዊና የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበራት
የካቲት 19 2007 ዓ/ም
ኢህአዴግ 98ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!!
ታላቅ ሥራ ተሰርቷል! እናመሰግናለን!” ኦባንግ ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡

ይህ ለመሠረታዊ ልማት እንዲውል በዓለም ባንክ በኩል የሚሰጠውን ገንዘብ የሚደጉሙት ምዕራባውያን አገራት ሲሆኑ አንዷ ተጠቃሽ አገር እንግሊዝ ናት፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከምዕራባውያን በዓለም ባንክ በኩል የሚያገኘውን ገንዘብ ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እያዋለው መሆኑ ለዓለም ባንክ ተደጋጋሚ መረጃዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በተለይ ሟቹ መለስ በቀጥታ በሰጡት ትዕዛዝ 424 የአኙዋክ ተወላጆች ከተገደሉ በኋላ ኢህአዴግ በቦታው ያሰማራው የመከላከያ ሠራዊት በሥፍራው የሚኖሩትን ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል እምቢ ያሉትን በግድ በማስነሳት፣ በመግደል፣ አስገድዶ በመድፈር፣ በማሰቃየት፣ ወዘተ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱ በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ባገኙ ዘገባዎች ሲነገር ቆይቷል፡፡ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ ልማት በማለት የሚሰጠው ገንዘብ ኢህአዴግ ወታደሮቹን የግፍ ሥራ ላይ በማሰማራት ደመወዝ የሚከፍልበት መሆኑን በመጥቀስ ወደ ኬኒያ የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎች አቤቱታ አቅርበው እንደነበር ጎልጉል በወቅቱ የዘገበው ዜና ነበር፡፡ ““ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”፤ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል” በሚል ርዕስ የተጻፈውን ዜና ለማንበት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ “ሚስተር ኦ” በመባል የሚጠሩት አኙዋክ ተወላጅ ኢህአዴግ የዕርዳታ ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣና ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እንዳዋለው በመጥቀስ የእንግሊዝ መንግሥት ከግብር ከፋይ ዜጎቹ የሚያገኘውን ገንዘብ አምባገነንነት እየደገፈበት መሆኑን በተለይም የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ተጠያቂ ስለሆነ ከዚህ እንዲታቀብ ክስ መመሥረታቸው ይታወቃል፡፡ የክሱ ሒደት እየተካሄደ ባለበት ባሁኑ ወቅት ሚስተር ኦ በተደጋሚ እንደመሰከሩት ኢህአዴግ ነዋሪዎችን በግዳጅ ከቀያቸው በማፈናቀል የሚያካሂደው የግዳጅ ሰፈራና የመንደር ምሥረታ ሕገወጥ መሆኑ በመቃወማቸው በተደጋጋሚ ከፍተኛ ድብደባ እንደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ብዙዎች ለአካላዊ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፣ ሴቶች ክብረንጽህናቸው ተደፍሯል፣ አዛውንትና ህጻናት ለአሰቃቂ መከራ ተዳርገዋል፤ ይህንንም እርሳቸው እንዳዩ ሚስተር ኦ ይመሰክራሉ፡፡
የሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ወደ ውሳኔ ሊደርስ ባለበት ወቅት የልማት መ/ቤቱ ይህንን ዓይነት ውሳኔ መውሰዱ ከፍርድ ቤቱ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ፡፡ የልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ግን የመ/ቤታቸው ውሳኔ ከሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ጋር ያልተያያዘ እንደሆነ መናገራቸውን የእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ መ/ቤቱ ለዚህ ውሳኔ የደረሰው ኢትዮጵያ “የዕድገት ስኬት” እያስመዘገበች በመምጣቷ የመሠረታዊ ልማት አገልግሎት የገንዘብ ዕርዳታ የማያስፈልጋት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ይህ መጠኑ እጅግ ከፍተኛ የተባለውና ለኢህአዴግ ንጹህ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሚያስገኝ ገንዘብ እንደነጠፈበት መሰማቱን አስመልክቶ ጋዜጣው የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን ሬድዋን ሁሴን በጠየቃቸው ወቅት የመለሱት አልነጠፈብንም የሚል እንድምታ ያለው ነው፡፡ “እነርሱ ያሉት ዕርዳታውን አንሰጥም ወይም እናቆማለን ሳይሆን ዕርዳታ አሰጣጡ እንደገና ይዋቀራል ነው” በማለት ሬድዋን ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) ዕርዳታ ለመስጠት ከዓለምባንክ ጋር ስምምነት የነበረው የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት “ኢትዮጵያ አድጋለች” በማለት በ2015/2016 በፓውንድ 256ሚሊዮን ብቻ (5በመቶ) ዕርዳታ ለመስጠት መወሰኑን የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊው ሬድዋን ሁሴን አላብራሩም፡፡
ኢህአዴግ ለዕርዳታ የሚሰጠውን ገንዘብ ዜጎችን ለማሰቃየት፣ ወታደር ለመቀለብ፣ ወዘተ እንደሚጠቀምበት በተደጋጋሚ ዘገባዎች እና ማስረጃዎች ሲወጡበት የከረመ ቢሆንም ማስረጃዎቹን ተከትሎ የዓለም ባንክ በዕርዳታ አሠጣጡ ላይ አንዳች ውሳኔ እንዳያደርግ ብዙ ሲደክም ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ጉዳዩ ውሳኔ ሳይሰጥበት እንዲስተጓጎል በማድረግ ለሁለት ዓመታት ያህል እንዲጓተት ማድረጉን ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይመሰክራሉ፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኦባንግ ሜቶ ጉዳዩን ገና ከጅምሩ የሚያውቁትና ድርጅታቸው ለዓመታት ሲሰራበት የነበረ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በመሆኑንም ይህንን የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት ውሳኔ የጋራ ንቅናቄያቸው ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን ያገኘው ድል እንደሆነ በፌስቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡ “ገና ከጅምሩ ከጋራ ንቅናቄያችን ጋር በመሆን ይህንን ሥራ በመደገፍ የተባበራችሁንን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፤ ታላቅ ሥራ ተሰርቷል፤ እናመሰግናለን” ብለዋል “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ኦባንግ በተለይ ከጎልጉል ለቀረበላቸው አጭር ጥያቄ በሰጡት አስተያየት የጋራ ንቅናቄያቸው ደስታውን የገለጸው የልማት ገንዘብ በመቋረጡ ሳይሆን በልማት ስም የሚሰጠው ዕርዳታ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ በመዋሉና ለዚህም ደግሞ ከበቂ በላይ ማስረጃ ድርጅታቸው ያለው በመሆኑ ነው፡፡ “አገር ብትለማ የሁሉም ደስታ ነው” ያሉት ኦባንግ አገርን በማልማት ሽፋን ደጋፊና ተቆርቋሪ የሌላቸውን ንጹሃን መበደልና የመኖር መብታቸውን መንፈግ ግን በየትኛውም መልኩ እርሳቸውም ሆነ አኢጋን የሚቀበለው እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
ኢህአዴግ በቅርቡ አካሂዳለው ለሚለው ምርጫ እንደ ዕቁብ ዕጣ በማውጣትና በማስወጣት “አልደረሳችሁም” እያለ የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮችን ከምርጫ እያስወገደ ባለበት፤ ሌሎችንም ሕጋዊ አይደላችሁም እያለ በተለጣፊ ድርጅት በማስበት ኅልውናቸውን እያሳጣ ባለበት ባሁኑ ወቅት በዜጎቹ ላይ የሚያካሂደውን መረን የለቀቀ የመብት ገፈፋ ለሥልጣን ያበቁትን ምዕራባውያንን ያስደሰተ እንዳልሆነ ይነገራል፡፡ የአውሮጳ ኅብረት ምርጫውን አልታዘብም ከማለቱ በተጨማሪ በሚዲያ ላይ የተጫነው አፈና በዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ይፋ ከሆነ ወዲህ ማነቆው በኢህአዴግ ላይ እየከረረ መምጣቱን ያሳያል፡፡ ኢህአዴግን ለሥልጣን ከማብቃት አልፋ ነፍጥ አንጋቢዎቹን የህወሃት መሪዎች ጸጉርና ጺም ከርክማ፤ ልብስ አልብሳ፤ ቋንቋ አስተምራ፤ የከተማ አኗኗር እንዴት እንደሆነ አሠልጥና፣ ቶሎ ባይገባቸውም ፕሮቶኮል አስተምራ፣ እስካሁንም ተንከባክባ እዚህ ድረስ ያቆየቻቸው እንግሊዝ እንዲህ ያለውን የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ስታደርቅ “ቀጣዩስ ምን ይሆን?” የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል፡፡ “ምዕራባውያን መግደልም ማንሳትም ያውቁበታል” በማለት አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች እንደሚሉት ቀጣዩ የኢህአዴግ ጉዞ በከፍተኛ ሁኔታ ለህወሃት ሲቀጥል ለኢህአዴግ አስጊ ከመሆን ባሻገር በውጭ ምንዛሪ እጥረት በየጊዜው የሚፈጠረውን ግሽበት በዕርዳታ ገንዘብ የሚያስተካክለው ኢህአዴግ እንዲህ ያለው የገንዘብ ማዕቀብ ክፉኛ ያነጥፈዋል ሲሉ ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሙስናው መረን በለቀቀባት አገር ከሕዝብ እየተዘረፈ በተለያዩ አገራት ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚከማቸውን ገንዘብ በሚካፈሉትም ላይ የድርሻ ቅነሳ የማስከተሉ ጉዳይ አብሮ የሚታይ እንደሆነ ይነገራል፡፡
ከዚህ ዜና ጋር ተያያዥነት ያለውን ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) ያተምነውን ዜና ከዚህ በታች እንደሚከተለው እንደገና አትመነዋል፡፡
ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!
ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!
ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።
ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል።
የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል።
አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡
በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት
ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
የጎልጉል የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።
በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል። (የመግቢያው ፎቶ የተወሰደው: ዘጋርዲያን)
90 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫነ የአየር ሃይል አንቶኖቭ አውሮፕላን ከመጋየት መትረፉን የቅርብ ምንጮች ያደረሱኝ መረጃ ያመለክታል። ዛሬ ጠዋት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት አቆጣጠር 90 የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪዎችን አሳፍሮ ደቡብ ሱዳን – ሃዲጉሊ የተባለች ግዛት የደረሰው አንቶንቭ አውሮላን ወደ መሬት እየወረደ ባለበት ወቅት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በዲሽቃ በተተኮሰ ሁለት ጥይት በጎን በኩል እንደተመታ ምንጮቹ ጠቁመዋል። በአብራሪዎቹና ወታደሮቹ ድንጋጤ ተፈጥሮ እንደነበረ ያመለከቱት ምንጮቹ የተተኮሰው ጥይት ሞተሩ አካባቢ ቢያርፍ ኖሮ አውሮፕላኑ ሊነድ ይችል እንደነበረ አስታውቀዋል። አንቶኖቭ አውሮፕላኑ ባላፈው ሳምንት በአንዱ የሞተር ክፍል ብልሽት ገጥሞት ለሰባት ቀናት በጥገና ላይ እንደሰነበተ ምንጮቹ አስታውቀዋል። በደቡብ ሱዳን በየጊዜው ከሚሰማራው የመከላከያ ሰራዊትና ሰላም አስከባሪ ሃይል የመከላከያ ጄኔራሎች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከሰራዊቱ እየዘረፉ ኪሳቸው እንደሚያስገቡ የሚታወቅ ሲሆን ዝርዝር መረጃውን በቅርቡ የምንመለስበት ይሆናል።
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ተቃውሞ






![Shimelis_Kemal_etio_478490b[1]](http://ethioandinet.files.wordpress.com/2014/01/shimelis_kemal_etio_478490b1.jpg?w=300&h=169)
