ባፈው ሰሞን ወሬና “ሚስጢር” አሹላኪው ዊኪሊክስ ከአሜሪካው የደህንነት ድርጅት ስትራትፎር ሾልኮ እጄ የገባው የበየነ መረብ መልዕክት መሰረት ግብጽ….. በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች የምፈልገውን በእነ ኢትዮጵያ ላይ ካልጫንኩ በሚሳኤልም፣ በኮማንዶም፣ በጄትም በመጠቀም በሰዓታት ልታጠቃን አንዳሰበች በሊባኖስ የሚኖሩ ዲፕሎማቷን ጠቅሶ ገልጾልናል፡፡
የግብፃውያን ከአባይ ጋር በተያያዘ ዋናው ችግራቸው በማስፈራራት እና ኃይል በመጠቀም የራሳቸው የሚያደርጉት ይመስላቸዋል፡፡ ይህም የሆነው በዋናነት የአባይ ወንዝ መነሻና ብዙውን ውሃ አበርካች የሆነችው ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ በጦርነት በመኖሯ እና አቅሟን የማጠናከር ጉዞዋ ያልተስተካከለ በመሆኑ ለውስጥ የደህንነት ጉዳዮች ትኩረት መስጠቷ ውሃውን እንዳትጠቀም እንቅፋት መሆኑ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ግብጽ ሱዳንን በመዛት ማስበርገግ መቻሏ እና ከካምፕ ዴቪድ ስምምነት በኋላ ከአሜሪካ የሚጎርፍላት ረብጣ ዶላር እና ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ልቧ እንዲያብጥ ስላደረገው ነው፡፡ ከላይ እንዳየነው የጦርነት ክዋኔ በዘመናት ይለያያል እንጅ ባህሪው ባለመለወጡ ምንም መሳሪያ ብታከማች ግብጽ በታሪኳ አትዮጵያን አንድም ጦርነት አሸነፍ አታውቅም፡፡ ከዚህ አንጻር ስንመለከተው በዊኪሊክስ በኩል የሾለከው ጦማር ተራ ወሬ ሊባል የሚችል ነው፡፡ ሆኖም ግን ስንገጣጥማቸው ሙሉ ትርጉም የሚሰጡን ክስተቶችን ስላየን ይህን ጦማር ማቅለል ዋጋ ሊያስከፍል ስለሚችል በአንክሮ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ምንአልባት ምንአልባት አንዳች ክፉ ነገር የህዳሴ ግድቡ ላይ ብታደርስ የማያቋርጥ የውሃ ጥማትን ለሚመጣው የግብጽ ትውልድ ትተዋለች፡፡ እጅግ በጣም ውስብስብ በሆነው መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ እየኖረች የእስራኤል እና የአረቦች ጉዳይ ባልለየለት ሁኔታ እንዲህ አይነት እስጣ ገባ ውስጥ መግባት የሚበላው ራሷን ግብጽን ነውና፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዊኪሊክስ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው ግብጽ ኢትዮጵያን በሽርክ ለማጥቃት ኩርሲ በተባለች ዳርፉር ሱዳን ውስጥ በምትገኝ ቦታ የሚስጢራዊ ወታደራዊ ማዘዣ እያቋቋመች እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ይህ ምን ያክል እውነት ነው? ወደፊት የምናየው ጉዳይ ይሆናል፡፡
Related articles
- ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች (Ethiopian Muslims) – A Book by Ahmedin Jebel (አሕመዲን ጀበል) (ethioandinet.wordpress.com)
- ሰበር ዜና: በካይሮ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ (ethioandinet.wordpress.com)
- ሰበር ዜና: በካይሮ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ (addisuwond.wordpress.com)
- መለስ ዜናዊ በአለማችን ላይ ሁለተኛው ሀብታም ጠቅላይ ሚኒስተር መሆኑን ምን ያህሎቻችን እናወቃለን? (addisuwond.wordpress.com)
- ኦባንግ ለኬሪ የጥሪ ደብዳቤ ላኩ! (yourfreedomvoice.wordpress.com)
- መለስ ዜናዊ በአለማችን ላይ ሁለተኛው ሀብታም ጠቅላይ ሚኒስተር መሆኑን ምን ያህሎቻችን እናወቃለን? (kendilmagazine.wordpress.com)
