የውጭ ባለሀብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወስደው እያለሙ እንጂ፣ መሬት ለመቀራመት ብለው ወደ ኢትዮጵያ አልገቡም ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ…
-ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንቶች እንደታሰቡት ውጤታማ አልሆኑም
ሚኒስትሩ የመሥሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማው ማክሰኞ ዕለት ሲያቀርቡ , ሰፋፊ መሬቶች ወስደው በግብርና ላይ ኢንቨስት እያደረጉ ስለሚገኙ የውጭ ባለሀብቶች ትክክለኛ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተጠየቁበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት .
በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ ለሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ , የውጭ ኩባንያዎች ሰፋፊ መሬቶች አንዳንዶቹ እንደሚሉት ቤልጂየምን የሚያህል መሬት ተሰጥቶ እየተካሄደ ስላለው ኢንቨስትመንት በቂ ማብራሪያ በሪፖርቱ ስላልተካተተ እውነቱ ሊብራራ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል .
በሰፋፊ መሬቶች ላይ የሚካሄድ የግብር ኢንቨስትመንት ችግር የለውም ያሉት አቶ ግርማ , በመንግሥት ላይ እየቀረበ ያለው ክስ አርሶ አደሮች እንዲፈናቀሉ ማድረጉ አንዱ ነው ብለዋል .
የውጭ ኩባንያዎቹ ብድር የሚያገኙት ከኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን የመገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ መሆኑን በማስታወስ , << በኢትዮጵያ ገንዘብና በኢትዮጵያ መሬት ለምንድን ነው የውጭ ኩባንያዎች መጥተው የሚያለሙት ? >> በማለት ጥያቄ አቅርበዋል .
<< ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው የውጭ ገበሬዎች የሚያስፈልጓቸው ? ምንድን ነው ይዘውልን የሚመጡት ? >> በማለት አቶ ግርማ የሚኒስትሩን ማብራሪያ ጠይቀዋል .
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥያቄ ያቀረቡት ብቸኛው የግል ተመራጭና የምክር ቤት አባል ዶ / ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ሲሆኑ , በሰፋፊ የግብርና መሬት ላይ በሚካሄደው ኢንቨስትመንት የምዕራባዊያን ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ለምን የማስተዋወቅ ሥራ አይሠራም በማለት , የህንድና የቻይና ( የምሥራቁ የዓለም አገሮች ) ኩባንያዎች የጐላ ተሳትፎ ሚዛኑን መጠበቅ ይገባዋል የሚል መልዕክት ያለው ጥያቄያዊ አስተያየታቸውን አቅርበዋል .
በጉዳዩ ላይ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች በጋራ ምላሽ የሰጡ ሲሆን , ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ወንድይራድ ማንደፍሮ በሰፋፊ መሬቶች ላይ ለሚካሄድ የግብርና ኢንቨስትመንት ሲባል አንድም ሰው ከቀዬው እንዲፈናቀል አልተደረገም ብለዋል .
<< የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት የሆኑ ነፃ መሬቶችን ብቻ ነው ለሰፋፊ የግብርና ኢንቨስትመንት የምንሰጠው ማንም ከቀዬው አልተፈናቀለም ; . >> በማለት አስረድተዋል .
በሰፋፊ መሬቶች ላይ የሚደረግ የግብር ኢንቨስትመንት ከፍተኛ የገንዘብ አቅም እንደሚጠይቅ የተናገሩት ማኒስትር ዴኤታው , ከዚህ ጋር የተያያዙ ችግሮች መኖራቸውን ግን አልሸሸጉም .
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ሆነ በባለሀብቶቹ ቀደም ብሎ ተይዞ የነበረው እምነት ኢንቨስትመንቱ ቀላል እንደነበር , ነገር ግን በተግባር ሲታይ ጊዜ የሚወስድና አቅም የሚጠይቅ እንደነበር ገልጸዋል .
በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለባለሀብቶቹ የሚሰጠውን የመሬት መጠን እየቀነሰ እንደሚገኝ , በአጠቃላይ ግን ትልቅ አቅም የሚፈጥር ዘርፍ እንደሚሆን አብራርተዋል .
በዚህ ዘርፍ በፌዴራል መንግሥት ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሀብቶች 43 መሆናቸውን አስረድተው , ከእነዚህ ውስጥ 15 የሚሆኑት ብቻ የውጭ ኩባንያዎች ናቸው ብለዋል . በመሆኑም በዘርፉ በአብዛኛው እየተሳተፉ የሚገኙት የአገር ውስጥ ባለሀብቶች መሆናቸውን አስረድተዋል .
ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ መሬት መቀራመት የለም ብለዋል .
አሁን ባለው የዓለም የዕድገት ሁኔታ የገንዘብ አቅም ያለው በምሥራቃውያን አካባቢ መሆኑን , ምዕራባውያኑ በዘርፉ ያልተሳተፉት የአቅም ችግር ስላለባቸው እንደሆነ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል .
<< የመሬት መቀራመት ጉዳይ እየተነሳ ያለው ከዚሁ የዓለም ጂኦ ፖለቲካ አካባቢ ነው ከምሥራቅ የዓለም አገሮች ወደ አፍሪካ እየመጣ ያለ ኢንቨስትመንት ስለማይወደድ ነው ; . >> ብለዋል .
ሚኒስትሩም ሆነ የሥራ ባልደረቦቻቸው የውጭ ኩባንያዎቹ እያገኙ ስላለው ከፍተኛ ብድር ግን ማብራሪያ ሳይሰጡበት ታልፏል .
የግብርና ሚኒስቴር የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም እንደሚያስረዳው , በ 2006 ዓ.ም. የመኸር ወቅት 253 ሚሊዮን 805 ሺሕ 340 ኩንታል ምርት ሊገኝ እንደሚችል , ይህም ካለፈው ዓመት ዘጠኝ በመቶ መጨመሩን ነው
