ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የአመራር አካላት፣ የመንግስት ተቋማት እና የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የማሕበራዊ ድረ ገጽን እንዲጠቀሙ መከረ..
ዳንኤል ብርሃኔ በብሎጉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጠቅሶ እንደዘገበው ዶ/ር ቴዎድሮስ በማሕበረዊ ድረ ገጽ እያደረጉትን ያለውን የመረጃ አጠቃቀም በተመለከተ በስፋት የሚወራው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን አስነብቧል።
ዶክተር ቴዎድሮስ ለብሎጉ በሰጡት አስተያየት፤ “በሶሻል ሚዲያ ድረ ገጽ በመጠቀሜ አንድም የተከፋ ጓድ የለም። በርግጥ በቅርቡ በከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በተደረገ ስብሰባ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደተቋም እንዲሁም በከፍተኛ የስራ ኃላፊዎቹ በኩል የማሕበራዊ ድረ ገጽ አጠቃቀማቸው በጥሩ ምሳሌ የሚነሳ መሆኑ ተነግሯል” ማለታቸውን አስነብቧል።
አያይዘውም ከሳዑዲ ተመላሽ በሆኑ ዜጎች ጉዳይ ላይ የሰነዘሩት ሃሳብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተመሳሳይ መሆኑንም አክለዋል።
የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ወጣቶች ሊግ ከወራቶች በፊት በከፍተኛ ሁኔታ ማሕበራዊ ድረ ገጽ እየተጠቀሙ መሆናቸውን ብሎጉ ገልጿል።
በተመሳሳይም የገዢው ፓርቲ ጽ/ቤት የማሕበራዊ ድረ ገጽ ክፍል ማቋቋሙን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ በተለይ በማኅበራዊ ድረገጾች (በቲዊተርና ፌስቡክ) እያደረጉ ያሉትን ተሳትፎ ራሳቸውን ለመሸጥ ተጠቅመውበታል በሚል በፓርቲያቸው መገምገማቸውን በተለይ የማኅበራዊ ድረገጾች መወያያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወስ ነው።
ሀገር ወዳድ ኢትዮዽያን ይህን የወያኔ ስርሀት እስክናስውግድ ድረስ ትግላችንን በሁሉም መስክ አጠናክረን መቀጠል ይገባናል። በሶሻል ሚዲያና ብሎግ እያሳየን ያለነው ትግል የኢትዮዽያ ህዝብ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከቱና ዘረኛውን የወያኔ ጉጂሌን ኢሰባዊ ድርጊቱን በማጋለጥ እየተወጣነው ያለው ተግባር በጣም ስላሳሰባቸው የወያኔ ባለስልጣናትና የወጣቶች ሊግ የሚባለው ሆድ አደሮች ስራችንንና ትግላችንን ሊያቆሙት አይገባም እዲያውም በተጠናከረ መልኩ ልንታገላቸው ይገባል እላለው።
Related articles
- የመለስ ዜናዊ የመጀመሪያ ልጅ ሰመሃል መለስ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኝ አንድ ባንክ ውስጥ 5 ቢሊዮን ዶላር በ2011 ኣስገብታለች። (ethioandinet.wordpress.com)
- ሰበር ዜና: በካይሮ ኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ (ethioandinet.wordpress.com)
- በኖርዌይ የወያኔ ጀሌዎች ሲደነብሩ ሲባረሩ የሚያሳየውን ፎቶ (addis12.wordpress.com)
- ናሳ ተመራማሪ የዶክተር ጥላዬ የህይወት ጉዞ – “ከእረኝነት ወደ ናሳ ተመራማሪነት” (autonomousoromia.wordpress.com)
- አስደንጋጭ ዜና There Are 15 Million Mentally Ill People In Ethiopia (addisuwond.wordpress.com)
